የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ካልእ 13

13
አም​ኖ​ንና ትዕ​ማር
1ከዚ​ህም በኋላ እን​ዲህ ሆነ፤ ለዳ​ዊት ልጅ ለአ​ቤ​ሴ​ሎም አን​ዲት የተ​ዋ​በች እኅት ነበ​ረ​ችው፤ ስም​ዋም ትዕ​ማር ነበረ፤ የዳ​ዊ​ትም ልጅ አም​ኖን ወደ​ዳት። 2አም​ኖ​ንም ከእ​ኅቱ ከት​ዕ​ማር የተ​ነሣ እስ​ከ​ሚ​ታ​መም ድረስ እጅግ ተከዘ፤ ድን​ግ​ልም ነበ​ረ​ችና አን​ዳች ነገር ያደ​ር​ግ​ባት ዘንድ በዐ​ይኑ ፊት ጭንቅ ሆኖ​በት ነበር። 3ለአ​ም​ኖ​ንም የዳ​ዊት ወን​ድም የሳ​ምዓ ልጅ ኢዮ​ና​ዳብ የሚ​ባል ወዳጅ ነበ​ረው፤ ኢዮ​ና​ዳ​ብም እጅግ ብልህ ሰው ነበረ። 4እር​ሱም፥ “የን​ጉሥ ልጅ ሆይ፥ ስለ​ምን በየ​ቀኑ እን​ዲህ ከሳህ? አት​ነ​ግ​ረ​ኝ​ምን?” አለው። አም​ኖ​ንም፥ “የወ​ን​ድ​ሜን የአ​ቤ​ሴ​ሎ​ምን እኅት ትዕ​ማ​ርን እወ​ድ​ዳ​ታ​ለሁ” አለው። 5ኢዮ​ና​ዳ​ብም አለው፦“ ታም​ሜ​አ​ለሁ ብለህ በአ​ል​ጋህ ላይ ተኛ፤ አባ​ት​ህም ሊያ​ይህ ይመ​ጣል፦ እኅቴ ትዕ​ማር እን​ድ​ት​መ​ጣና እኔ የም​በ​ላ​ውን እን​ጀራ እን​ድ​ት​ሰ​ጠኝ፥ መብ​ሉ​ንም እኔ እያ​የሁ እን​ድ​ታ​በ​ስ​ል​ልኝ፥ ከእ​ጅ​ዋም እን​ድ​በ​ላው እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ በለው።” 6እን​ዲ​ሁም አም​ኖን፥ ታም​ሜ​አ​ለሁ ብሎ ተኛ፤ ንጉ​ሡም ሊያ​የው መጣ፤ አም​ኖ​ንም ንጉ​ሡን፥ “እኅቴ ትዕ​ማር እን​ድ​ት​መ​ጣና እኔ እያ​የሁ ሁለት እን​ጎቻ እን​ድ​ታ​በ​ስ​ል​ልኝ፥ ከእ​ጅ​ዋም እን​ድ​በላ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ” አለው።
7ዳዊ​ትም፥ “ወደ ወን​ድ​ምሽ ወደ አም​ኖን ቤት ሂጂ፤ መብ​ል​ንም አዘ​ጋ​ጂ​ለት” ብሎ ወደ ትዕ​ማር ቤት ላከ። 8ትዕ​ማ​ርም ወደ ወን​ድ​ምዋ ወደ አም​ኖን ቤት ሄደች፤ ተኝ​ቶም ነበር፤ ዱቄ​ትም ወስዳ ለወ​ሰች፤ በፊ​ቱም እን​ጎቻ አደ​ረ​ገች፤ ጋገ​ረ​ችም። 9ምጣ​ዱ​ንም ወስዳ በፊቱ ገለ​በ​ጠች፤ እርሱ ግን ይበላ ዘንድ እንቢ አለ። አም​ኖ​ንም፥ “ሰውን ሁሉ ከእኔ ዘንድ አስ​ወጡ” አለ፤ ሰውም ሁሉ ከእ​ርሱ ዘንድ ወጣ። 10አም​ኖ​ንም ትዕ​ማ​ርን፥ “በእ​ጅሽ እበላ ዘንድ መብ​ሉን ወደ እል​ፍኙ አግ​ቢው” አላት፤ ትዕ​ማ​ርም የሠ​ራ​ች​ውን እን​ጎቻ ወስዳ ወን​ድ​ምዋ አም​ኖን ወዳ​ለ​በት እል​ፍኝ አገ​ባ​ችው። 11ይበ​ላም ዘንድ መብ​ሉን አቀ​ረ​በ​ች​ለት። እር​ሱም ያዛ​ትና፥ “እኅቴ ሆይ፥ ነዪ ከእኔ ጋር ተኚ” አላት። 12እር​ስ​ዋም አለ​ችው፥ “ወን​ድሜ ሆይ፥ አታ​ዋ​ር​ደኝ፤ እን​ዲህ ያለ ነገር በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ አይ​ገ​ባ​ምና ይህን ነው​ረኛ ሥራ አታ​ድ​ርግ። 13እኔም ነው​ሬን ወዴት እጥ​ላ​ታ​ለሁ? አን​ተም በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ከሰ​ነ​ፎች እንደ አንዱ ትሆ​ና​ለህ፤ እን​ግ​ዲ​ያስ ለን​ጉሡ ንገ​ረው፥ እኔ​ንም አይ​ነ​ሣ​ህም” አለ​ችው። 14አም​ኖ​ንም ቃል​ዋን አል​ሰ​ማም፤ ይዞም አደ​ከ​ማት፤ ከእ​ር​ስ​ዋም ጋር ተኛ።
15ከዚ​ያም በኋላ አም​ኖን ፈጽሞ ጠላት፤ አስ​ቀ​ድሞ ከአ​ፈ​ቀ​ራት ፍቅር ይልቅ በኋላ የጠ​ላት ጥል በለጠ። አም​ኖ​ንም፥ “ተነ​ሥ​ተሽ ሂጂ” አላት። 16ትዕ​ማ​ርም፥ “ቀድሞ ከሠ​ራ​ኸው ክፋት ይልቅ እኔን በማ​ው​ጣ​ትህ የበ​ለጠ ክፋት ትሠ​ራ​ለህ” አለ​ችው፤ አም​ኖን ግን ቃል​ዋን አል​ሰ​ማ​ትም። 17በበር ቁሞ የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ለ​ው​ንም ብላ​ቴና ጠርቶ፥ “ይህ​ችን ሴት ከፊቴ አስ​ወ​ጥ​ተህ በሩን ዝጋ​ባት” አለው። 18ብዙ ኅብር ያለ​ው​ንም ልብስ ለብሳ ነበር፤ የን​ጉሡ ልጆች ደና​ግሉ እን​ዲህ ያለ​ውን ልብስ ይለ​ብሱ ነበ​ርና፤ አገ​ል​ጋ​ዩም አስ​ወ​ጥቶ በሩን ዘጋ​ባት። 19ትዕ​ማ​ርም አመድ ወስዳ በራ​ስዋ ላይ ነሰ​ነ​ሰች፤ በላ​ይዋ የነ​በ​ረ​ው​ንም ብዙ ኅብር ያለ​ውን ልብ​ስ​ዋን ቀደ​ደ​ችው፤ እጅ​ዋ​ንም በራ​ስዋ ላይ ጭና እየ​ጮ​ኸች ሄደች።
20ወን​ድ​ም​ዋም አቤ​ሴ​ሎም፥ “ወን​ድ​ምሽ አም​ኖን ከአ​ንቺ ጋር ነበ​ርን? እኅቴ ሆይ፥ አሁን ግን ዝም በዪ፤ ወን​ድ​ምሽ ነውና፤ ይህን ነገር ትና​ገሪ ዘንድ በል​ብሽ አታ​ስቢ” አላት። ትዕ​ማ​ርም በወ​ን​ድ​ምዋ በአ​ቤ​ሴ​ሎም ቤት መበ​ለት ሆና ተቀ​መ​ጠች። 21ንጉ​ሡም ዳዊት ይህን ነገር ሁሉ ሰማ፤ እጅ​ግም ተቈጣ፥ ነገር ግን የበ​ኵር ልጁ ነበ​ረና ስለ ወደ​ደው የል​ጁን የአ​ም​ኖ​ንን ነፍስ አላ​ሳ​ዘ​ነም። 22አቤ​ሴ​ሎ​ምም አም​ኖ​ንን ክፉም ሆነ መል​ካም አል​ተ​ና​ገ​ረ​ውም። እኅ​ቱን ትዕ​ማ​ርን ስላ​ስ​ነ​ወ​ራት አቤ​ሴ​ሎም አም​ኖ​ንን ጠል​ቶ​ታ​ልና።
አቤ​ሴ​ሎም አም​ኖ​ንን እንደ ገደለ
23ከሁ​ለት ዓመ​ትም በኋላ አቤ​ሴ​ሎም በኤ​ፍ​ሬም አቅ​ራ​ቢያ ባለ​ችው በቤ​ላ​ሶር በጎ​ቹን በሚ​ያ​ሸ​ል​ት​በት ጊዜ አቤ​ሴ​ሎም የን​ጉ​ሡን ልጆች ሁሉ ጠራ። 24አቤ​ሴ​ሎ​ምም ወደ ንጉሡ መጥቶ፥ “እነሆ፥ አገ​ል​ጋ​ይህ በጎ​ቹን ያሸ​ል​ታል፤ ንጉሡ ከአ​ገ​ል​ጋ​ይህ ጋር ይሂድ፤ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም ይሂዱ” አለው። 25ንጉ​ሡም አቤ​ሴ​ሎ​ምን፥ “ልጄ ሆይ፥ አይ​ሆ​ንም፤ እን​ከ​ብ​ድ​ብ​ሃ​ለ​ንና ሁላ​ችን አን​ሄ​ድም” አለው። የግ​ድም አለው፤ እርሱ ግን መረ​ቀው እንጂ ለመ​ሄድ እንቢ አለ። 26አቤ​ሴ​ሎ​ምም፥ “አንተ እንቢ ካልህ ወን​ድሜ አም​ኖን ከእኛ ጋር እን​ዲ​ሄድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ” አለ። ንጉ​ሡም፥ “ከአ​ንተ ጋር ለምን ይሄ​ዳል?” አለው። 27አቤ​ሴ​ሎ​ምም የግድ አለው፤ አም​ኖ​ን​ንና የን​ጉ​ሡ​ንም ልጆች ከእ​ርሱ ጋር ላከ። 28አቤ​ሴ​ሎ​ምም እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ግብዣ አደ​ረገ፤ አቤ​ሴ​ሎ​ምም አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን፥ “አም​ኖን የወ​ይን ጠጅ ጠጥቶ ልቡን ደስ ባለው ጊዜ እዩ፦ አም​ኖ​ንን ግደሉ ባል​ኋ​ችሁ ጊዜ ግደ​ሉት። አት​ፍ​ሩም፤ ያዘ​ዝ​ኋ​ች​ሁም እኔ ነኝና በርቱ፤ ጽኑም” ብሎ አዘ​ዛ​ቸው። 29የአ​ቤ​ሴ​ሎ​ምም አገ​ል​ጋ​ዮች አቤ​ሴ​ሎም እን​ዳ​ዘ​ዛ​ቸው በአ​ም​ኖን ላይ አደ​ረ​ጉ​በት። የን​ጉ​ሡም ልጆች ሁሉ ተነ​ሥ​ተው በየ​በ​ቅ​ሎ​ዎ​ቻ​ቸው ተቀ​ም​ጠው ሸሹ።
30ገናም በመ​ን​ገድ ሲሄዱ ለዳ​ዊት፥ “አቤ​ሴ​ሎም የን​ጉ​ሡን ልጆች ሁሉ ገደ​ላ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም አንድ አል​ቀ​ረም” የሚል ወሬ መጣ። 31ንጉ​ሡም ተነ​ሥቶ ልብ​ሱን ቀደደ፤ በም​ድር ላይም ወደቀ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ቁመው የነ​በሩ ብላ​ቴ​ኖቹ ሁሉ ልብ​ሳ​ቸ​ውን ቀደዱ። 32የዳ​ዊ​ትም ወን​ድም የሳ​ምዓ ልጅ ኢዮ​ና​ዳብ መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “ጌታዬ ጐል​ማ​ሶቹ የን​ጉሡ ልጆች ሁሉ እንደ ሞቱ አያ​ስብ፤ እኅ​ቱን ትዕ​ማ​ርን በግድ ካስ​ነ​ወ​ራት ጀምሮ በአ​ቤ​ሴ​ሎም ዘንድ የተ​ቈ​ረጠ ነገር ነበ​ረና የሞተ አም​ኖን ብቻ ነው። 33አሁ​ንም የሞተ አም​ኖን ብቻ ነው እንጂ የን​ጉሥ ልጆች ሁሉ ሞቱ ብሎ ጌታዬ ንጉሡ ይህን ነገር በልቡ አያ​ስብ።”
34አቤ​ሴ​ሎ​ምም ኰበ​ለለ። ጕበ​ኛ​ውም ጐል​ማሳ ዐይ​ኑን ከፍ አደ​ረገ፤ እነ​ሆም፥ ብዙ ሰዎች በኋ​ላው በተ​ራ​ራው አጠ​ገብ በመ​ን​ገድ ሲመጡ አየ። ጕበ​ኛ​ውም መጥቶ ለን​ጉሡ እን​ዲህ ብሎ ነገ​ረው፥ “ብዙ ሰዎች በተ​ራ​ራው ጎን ባለው በአ​ር​ኖን መን​ገድ ሲመጡ አየሁ።” 35ኢዮ​ና​ዳ​ብም ንጉ​ሡን፥ “እነሆ፥ የን​ጉሡ ልጆች መጥ​ተ​ዋል፤ አገ​ል​ጋ​ይህ እን​ዳ​ለው እን​ዲሁ ሆኖ​አል” አለው። 36ተና​ግ​ሮም በጨ​ረሰ ጊዜ እነሆ፥ ወዲ​ያው የን​ጉሥ ልጆች ገቡ፤ ድም​ፃ​ቸ​ው​ንም ከፍ አድ​ር​ገው አለ​ቀሱ፤ ደግ​ሞም ንጉ​ሡና ብላ​ቴ​ኖቹ ሁሉ እጅግ ታላቅ ልቅሶ አለ​ቀሱ።
37አቤ​ሴ​ሎም ግን ኰብ​ልሎ ወደ መአክ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ማካድ” ይላል። ሀገር ወደ ጌድ​ሶር ንጉሥ ወደ አሚ​ሁድ ልጅ ወደ ቶል​ማ​ይዮ ሄደ። ዳዊ​ትም ሁል ጊዜ ለልጁ ያለ​ቅስ ነበር። 38አቤ​ሴ​ሎ​ምም ኰብ​ልሎ ወደ ጌድ​ሶር ሄደ፤ በዚ​ያም ሦስት ዓመት ያህል ተቀ​መጠ። 39ንጉ​ሡም ዳዊት አቤ​ሴ​ሎ​ምን መከ​ታ​ተ​ልን ተወ፤ ስለ ሞተው ልጁ ስለ አም​ኖን ተጽ​ና​ንቶ ነበ​ርና።#ዕብ. “ስለ አም​ኖን ሞት ተጽ​ና​ንቶ ወደ አቤ​ሴ​ሎም ይሄድ ዘንድ እጅግ ናፈቀ” የሚል ይጨ​ም​ራል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ