መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ካልእ 17

17
የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ሆሴዕ
1የይ​ሁዳ ንጉሥ አካዝ በነ​ገሠ በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ዓመት የኤላ ልጅ ሆሴዕ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በሰ​ማ​ርያ ዘጠኝ ዓመት ነገሠ። 2በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ ነገር አደ​ረገ፤ ነገር ግን ከእ​ርሱ አስ​ቀ​ድሞ እንደ ነበ​ሩት እንደ እስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት አል​ሆ​ነም። 3የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ስል​ም​ና​ሶር በእ​ርሱ ላይ ዘመተ፤ ሆሴ​ዕም ተገ​ዛ​ለት፤ ግብ​ርም አመ​ጣ​ለት። 4የአ​ሦ​ርም ንጉሥ በሆ​ሴዕ ላይ ዐመፅ አገኘ፤ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ች​ን ወደ ግብፅ ንጉሥ ወደ ሴጎር ልኮ ነበ​ርና፤ እንደ ልማ​ዱም በየ​ዓ​መቱ ለአ​ሦር ንጉሥ ግብር አል​ሰ​ጠ​ምና፤ ስለ​ዚህ የአ​ሦር ንጉሥ ተዋ​ጋው፤ ይዞም በወ​ህኒ ቤት አሰ​ረው።
የዐ​ሥሩ ነገድ መን​ግ​ሥት መው​ደቅ
5የአ​ሦ​ርም ንጉሥ በም​ድር ሁሉ ላይ ወጣ፤ ወደ ሰማ​ር​ያም ወጥቶ ሦስት ዓመት ከበ​ባት። 6በሆ​ሴ​ዕም በዘ​ጠ​ነ​ኛው ዓመት የአ​ሦር ንጉሥ ሰማ​ር​ያን ያዘ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ወደ አሶር አፈ​ለሰ፤ በአ​ላ​ሔና በአ​ቦር፤ በጎ​ዛ​ንም ወንዝ፤ በሜ​ዶ​ንም ከተ​ሞች አኖ​ራ​ቸው።
7የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከግ​ብፅ ንጉሥ ከፈ​ር​ዖን እጅ፥ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ቸ​ውን አም​ላ​ካ​ቸ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በድ​ለው ነበ​ርና፥ ሌሎ​ች​ንም አማ​ል​ክት አም​ል​ከው ነበ​ርና፤ 8እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት በአ​ሳ​ደ​ዳ​ቸው በአ​ሕ​ዛብ ሥር​ዐት፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ነገ​ሥ​ታት ባደ​ረ​ጓት ሥር​ዐት ሄደው ነበ​ርና እን​ደ​ዚህ ሆነ። 9የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በአ​ም​ላ​ካ​ቸው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ቅን ያል​ሆ​ነን ነገር በስ​ውር አደ​ረጉ፤ በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ ከዘ​በ​ኞች ግንብ ጀምሮ እስከ ተመ​ሸ​ገች ከተማ ድረስ በከ​ፍ​ታ​ዎች ላይ መስ​ገ​ጃ​ዎ​ችን ሠሩ። 10በረ​ጃ​ጅሙ ኮረ​ብታ ሁሉ ላይ፥ በለ​መ​ለ​መ​ውም ዛፍ ሁሉ በታች ሐው​ል​ቶ​ች​ንና የማ​ም​ለ​ኪያ ዐም​ዶ​ችን ተከሉ፤ 11እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከፊ​ታ​ቸው ያወ​ጣ​ቸው አሕ​ዛብ እን​ዳ​ደ​ረ​ጉት፥ በኮ​ረ​ብ​ቶቹ መስ​ገ​ጃ​ዎች ሁሉ ላይ ያጥኑ ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ያስ​ቈጡ ዘንድ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዶ​ች​ንና ሐው​ል​ቶ​ችን አደ​ረጉ፤ 12እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ይህን አታ​ድ​ርጉ” ብሎ የከ​ለ​ከ​ላ​ቸ​ውን ጣዖ​ቶች አመ​ለኩ። 13እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ከክፉ መን​ገ​ዳ​ችሁ ተመ​ለሱ፤ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም እን​ዳ​ዘ​ዝ​ሁት፥ በባ​ሪ​ያ​ዎቼ በነ​ቢ​ያት የላ​ክ​ሁ​ላ​ች​ሁን ትእ​ዛ​ዜ​ንና ሥር​ዐ​ቴን፥ ሕጌ​ንም ሁሉ ጠብቁ” ብሎ በነ​ቢዩ ሁሉና በባለ ራእዩ አፍ ሁሉ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በይ​ሁዳ መሰ​ከረ። 14ነገር ግን አም​ላ​ካ​ቸ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዳ​ላ​መኑ ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው አን​ገት ይልቅ አን​ገ​ታ​ቸ​ውን አደ​ነ​ደኑ እንጂ አል​ሰ​ሙም። 15የገ​ባ​ላ​ቸ​ው​ንም ቃል ኪዳን ሁሉ አል​ጠ​በ​ቁም። ከንቱ ነገ​ር​ንም ተከ​ተሉ፤ ከን​ቱም ሆኑ፤ እንደ እነ​ር​ሱም እን​ዳ​ይ​ሠሩ ያዘ​ዛ​ቸ​ውን በዙ​ሪ​ያ​ቸው ያሉ​ትን አሕ​ዛብ ተከ​ተሉ። 16የአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ው​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ሁሉ ተዉ፤ ቀል​ጠው የተ​ሠ​ሩ​ት​ንም የሁ​ለ​ቱን እን​ቦ​ሶች ምስ​ሎች አደ​ረጉ፤ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ድ​ንም ተከሉ፤ ለሰ​ማ​ይም ሠራ​ዊት ሁሉ ሰገዱ፤ በዓ​ል​ንም አመ​ለኩ። 17ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት ሥዉ​አ​ቸው፤ ምዋ​ር​ተ​ኞ​ችና አስ​ማ​ተ​ኞ​ችም ሆኑ፤ ያስ​ቈ​ጡ​ትም ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ነገር ለማ​ድ​ረግ ራሳ​ቸ​ውን ሸጡ። 18ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ እጅግ ተቈጣ፤ ከፊ​ቱም ጣላ​ቸው፤ ከይ​ሁ​ዳም ነገድ ብቻ በቀር ማንም አል​ቀ​ረም።
19ይሁ​ዳም ደግሞ እስ​ራ​ኤል ባደ​ረ​ጋት ሥር​ዐት ሄደ እንጂ የአ​ም​ላ​ኩን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ አል​ጠ​በ​ቀም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ተዉት። 20እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ዘር ሁሉ ተቈጣ፤ አስ​ጨ​ነ​ቃ​ቸ​ውም፤ ከፊ​ቱም እስ​ኪ​ጥ​ላ​ቸው ድረስ በበ​ዝ​ባ​ዦች እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው። 21እስ​ራ​ኤ​ልም ከዳ​ዊት ቤት ተለዩ፤ የና​ባ​ጥ​ንም ልጅ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምን አነ​ገሡ፤ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከመ​ከ​ተል እስ​ራ​ኤ​ልን መለሰ፤ ታላ​ቅም ኀጢ​አት አሠ​ራ​ቸው። 22የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ኢዮ​ር​ብ​ዓም ባደ​ረ​ገው ኀጢ​አት ሁሉ ሄዱ፤ 23እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በባ​ሪ​ያ​ዎቹ በነ​ቢ​ያት ሁሉ አፍ እንደ ተና​ገ​ረው እስ​ራ​ኤ​ልን ከፊቱ እስ​ኪ​ያ​ወጣ ድረስ ከእ​ር​ስዋ አል​ራ​ቁም። እስ​ራ​ኤ​ልም እስከ ዛሬ ድረስ ከም​ድሩ ወደ አሦር ፈለሰ።
24የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ከባ​ቢ​ሎ​ንና ከኩታ፥ ከአ​ዋና ከሐ​ማት፥ ከሴ​ፌ​ር​ዋ​ይም ሰዎ​ችን አመጣ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ፋንታ በሰ​ማ​ርያ ከተ​ሞች አኖ​ራ​ቸው፤ ሰማ​ር​ያ​ንም ወረ​ሱ​አት፤ በከ​ተ​ሞ​ች​ዋም ተቀ​መጡ። 25በዚ​ያም መቀ​መጥ በጀ​መሩ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አይ​ፈ​ሩ​ትም ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አን​በ​ሶ​ችን ሰደ​ደ​ባ​ቸው፤ ይገ​ድ​ሉ​አ​ቸ​ውም ነበር። 26ስለ​ዚ​ህም ለአ​ሦር ንጉሥ፥ “ያፈ​ለ​ስ​ኻ​ቸው፥ በሰ​ማ​ር​ያም ከተ​ሞች ያኖ​ር​ኻ​ቸው ሕዝ​ቦች የሀ​ገ​ሩን አም​ላክ ሕግ አላ​ወ​ቁም፤ የሀ​ገ​ሩን አም​ላክ ሕግ አላ​ወ​ቁ​ምና አን​በ​ሶ​ችን ሰድ​ዶ​ባ​ቸ​ዋል፤ እነ​ሆም፥ እየ​ገ​ደ​ሉ​አ​ቸው ነው” ብለው ተና​ገ​ሩት።
27የአ​ሦ​ርም ንጉሥ፥ “ከዚያ ካመ​ጣ​ኋ​ቸው ካህ​ናት አን​ዱን ውሰዱ፤ ሄዶም በዚያ ይቀ​መጥ፤ የሀ​ገ​ሩ​ንም አም​ላክ ሕግ ያስ​ተ​ም​ራ​ቸው” ብሎ አዘዘ። 28ከሰ​ማ​ር​ያም ካፈ​ለ​ሱ​አ​ቸው ካህ​ናት አን​ዱን ወስ​ደው በቤ​ቴል አኖ​ሩት፤ ያም ካህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዴት እን​ደ​ሚ​ፈ​ሩት ያስ​ተ​ም​ራ​ቸው ነበር። 29በየ​ሕ​ዝ​ባ​ቸ​ውም አም​ላ​ኮ​ቻ​ቸ​ውን አደ​ረጉ፤ ሳም​ራ​ው​ያ​ንም በሠ​ሯቸው በኮ​ረ​ብ​ታው መስ​ገ​ጃ​ዎች ሕዝቡ ሁሉ በሚ​ኖ​ሩ​ባቸው ከተ​ሞ​ቻ​ቸው አኖ​ሩ​አ​ቸው። 30የባ​ቢ​ሎ​ንም ሰዎች ሴኬ​ቤ​ቴ​ና​ሆ​ምን ሠሩ፤ የኩ​ታም ሰዎች ኤር​ጌ​ትን ሠሩ፤ 31የሐ​ማ​ትም ሰዎች አሲ​ማ​ትን ሠሩ፤ አዋ​ው​ያ​ንም ኤል​ባ​ዝ​ር​ንና ተር​ታ​ቅን ሠሩ፤ የሴ​ፌ​ር​ዋ​ይም ሰዎች ለሴ​ፌ​ር​ዋ​ይም አማ​ል​ክት ለአ​ድ​ራ​ሜ​ሌ​ክና ለአ​ኔ​ሜ​ሌክ ልጆ​ቻ​ቸ​ውን በእ​ሳት ይሠዉ ነበር። 32እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ይፈሩ ነበር፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ በሚ​ኖ​ሩ​በት ከተማ በሰ​ማ​ርያ በሠ​ሩት በከ​ፍ​ታው ቦታ ጣዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን አኖሩ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ይፈሩ ነበር፤ ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ለኮ​ረ​ብ​ታው መስ​ገ​ጃ​ዎች ካህ​ና​ትን አደ​ረጉ፤ በኮ​ረ​ብ​ታ​ውም መስ​ገ​ጃ​ዎች ይሠዉ ነበር። 33እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሲፈሩ ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው እንደ ፈለ​ሱት እንደ አሕ​ዛብ ልማድ አም​ላ​ካ​ቸ​ውን ያመ​ልኩ ነበር።
34እስከ ዛሬም ድረስ እንደ ልማ​ዳ​ቸው ያደ​ር​ጋሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ይፈ​ራሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እስ​ራ​ኤል ብሎ የጠ​ራ​ውን የያ​ዕ​ቆ​ብን ልጆች እን​ዳ​ዘ​ዛ​ቸው ሥር​ዐ​ትና ፍርድ፥ ሕግና ትእ​ዛ​ዝም ያደ​ር​ጋሉ።#ዕብ. “አይ​ፈ​ሩም ፤ አያ​ደ​ር​ጉም” ይላል። 35እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደ​ረገ፤ እን​ዲ​ህም ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፥ “ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት አት​ፍ​ሩ​አ​ቸው፤ አት​ስ​ገ​ዱ​ላ​ቸ​ውም፤ አታ​ም​ል​ኩ​አ​ቸ​ውም፤ አት​ሠ​ዉ​ላ​ቸ​ውም። 36ነገር ግን በታ​ላቅ ኀይል በተ​ዘ​ረ​ጋ​ችም ክንድ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እር​ሱን ፍሩ፤ ለእ​ር​ሱም ስገዱ፤ ለእ​ር​ሱም ሠዉ። 37የጻ​ፈ​ላ​ች​ሁ​ንም ሥር​ዐ​ትና ፍርድ፥ ሕግና ትእ​ዛ​ዝም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ታደ​ርጉ ዘንድ ጠብቁ፤ ሌሎ​ች​ንም አማ​ል​ክት አት​ፍሩ። 38ከእ​ና​ን​ተም ጋር ያደ​ረ​ገ​ውን ቃል ኪዳን አት​ርሱ፤ ሌሎ​ች​ንም አማ​ል​ክት አት​ፍሩ። 39ነገር ግን አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍሩ፤ እር​ሱም ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸሁ ሁሉ እጅ ያድ​ና​ች​ኋል። 40ነገር ግን እነ​ርሱ እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ር​ጉት ልማ​ዳ​ቸ​ውን አት​ስሙ። 41እነ​ዚ​ህም አሕ​ዛብ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይፈሩ ነበር፤ ደግ​ሞም የተ​ቀ​ረጹ ምስ​ሎ​ቻ​ቸ​ውን ያመ​ልኩ ነበር፤ ልጆ​ቻ​ቸ​ውም፥ የልጅ ልጆ​ቻ​ቸ​ውም አባ​ቶ​ቻ​ቸው እን​ዳ​ደ​ረጉ እስከ ዛሬ ድረስ እን​ዲሁ ያደ​ር​ጋሉ።”

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ