የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ካልእ 14

14
የይ​ሁዳ ንጉሥ አሜ​ስ​ያስ
(2ዜ.መ. 25፥1-24)
1በእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ በኢ​ዮ​አ​ካዝ ልጅ በዮ​አስ በሁ​ለ​ተ​ኛው ዓመት የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​አስ ልጅ አሜ​ስ​ያስ ነገሠ። 2መን​ገ​ሥም በጀ​መረ ጊዜ ዕድ​ሜው ሃያ አም​ስት ዓመት ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሃያ ዘጠኝ ዓመት ነገሠ። እና​ቱም ዮአ​ድም የተ​ባ​ለች የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሴት ነበ​ረች። 3በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ቅን ነገር አደ​ረገ፤ ነገር ግን አባቱ ኢዮ​አስ እን​ዳ​ደ​ረገ ሁሉ እንጂ እንደ አባቱ እንደ ዳዊት አላ​ደ​ረ​ገም። 4ነገር ግን በኮ​ረ​ብ​ቶቹ ላይ ያሉ​ትን መስ​ገ​ጃ​ዎች አላ​ስ​ወ​ገ​ደም፤ ሕዝ​ቡም ገና በኮ​ረ​ብ​ቶቹ ላይ ባሉት መስ​ገ​ጃ​ዎች ይሠ​ዋና ያጥን ነበር። 5መን​ግ​ሥ​ቱም በእጁ በጸ​ና​ለት ጊዜ አባ​ቱን የገ​ደ​ሉ​ትን አገ​ል​ጋ​ዮች ገደለ። 6በሙሴ ሕግ መጽ​ሐ​ፍም እንደ ተጻፈ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ሁሉ በኀ​ጢ​አቱ ይሙት እንጂ አባ​ቶች ስለ ልጆች አይ​ሙቱ፤ ልጆ​ችም ስለ አባ​ቶች አይ​ሙቱ” ብሎ እን​ዳ​ዘዘ የነ​ፍሰ ገዳ​ዮ​ቹን ልጆች አል​ገ​ደ​ላ​ቸ​ውም። 7እር​ሱም በጨው ሸለቆ ከኤ​ዶ​ም​ያስ ዐሥር ሺህ ሰው ገደለ፤ ሴላ​ንም በጦ​ር​ነት ወስዶ ስም​ዋን እስከ ዛሬ ድረስ “ዮቅ​ት​ኤል” ብሎ ጠራት።
8በዚ​ያን ጊዜም አሜ​ስ​ያስ፥ “ና እርስ በር​ሳ​ችን ፊት ለፊት እን​ተ​ያይ” ብሎ ወደ እስ​ራ​ኤል ንጉሥ ወደ ኢዩ ልጅ ወደ ኢዮ​አ​ካዝ ልጅ ወደ ዮአስ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ። 9የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ዮአስ፥ “የሊ​ባ​ኖስ ኵር​ን​ችት፦ ልጅ​ህን ለልጄ ሚስት አድ​ር​ገህ ስጠው ብሎ ወደ ሊባ​ኖስ ዝግባ ላከ፤ የሊ​ባ​ኖ​ስም አውሬ አልፎ ኵር​ን​ች​ቱን ረገጠ። 10ኤዶ​ም​ያ​ስን በእ​ው​ነት መታህ፤ ልብ​ህ​ንም ከፍ ከፍ አደ​ረ​ግህ፤ በዚያ ተመካ፤ በቤ​ት​ህም ተቀ​መጥ፤ አንተ፥ ይሁ​ዳም ከአ​ንተ ጋር ትወ​ድቁ ዘንድ ስለ ምን መከ​ራን ትሻ​ለህ?” ብሎ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሜ​ስ​ያስ ላከ።
11አሜ​ስ​ያስ ግን አል​ሰ​ማም፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ዮአስ ዘመተ፤ እር​ሱና የይ​ሁዳ ንጉሥ አሜ​ስ​ያ​ስም በይ​ሁዳ ባለች በቤ​ት​ሳ​ሚስ ፊት ለፊት ተያዩ። 12ይሁ​ዳም በእ​ስ​ራ​ኤል ፊት ተመታ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ወደ ድን​ኳኑ ሸሸ። 13የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ዮአስ የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ የአ​ካ​ዝ​ያ​ስን ልጅ የኢ​ዮ​አ​ስን ልጅ አሜ​ስ​ያ​ስን በቤ​ት​ሳ​ሚስ ይዞ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጣ፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ቅጥር ከኤ​ፍ​ሬም በር ጀምሮ እስከ ማዕ​ዘኑ በር ድረስ አራት መቶ ክንድ አፈ​ረሰ። 14ወር​ቁ​ንና ብሩን ሁሉ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤትና በን​ጉሥ ቤተ መዛ​ግ​ብት የነ​በ​ሩ​ትን ዕቃ​ዎች ሁሉ፤ በመ​ያ​ዣም የተ​ያ​ዙ​ትን ልጆች ወስዶ ወደ ሰማ​ርያ ተመ​ለሰ።
15የቀ​ረ​ውም ያደ​ረ​ገው የዮ​አስ ነገር፥ ኀይ​ሉም፥ ከይ​ሁ​ዳም ንጉሥ ከአ​ሜ​ስ​ያስ ጋር እንደ ተዋጋ፥ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን? 16ዮአ​ስም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በሰ​ማ​ር​ያም ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት ጋር ተቀ​በረ፤ ልጁም ኢዮ​ር​ብ​ዓም በፋ​ን​ታው ነገሠ።
17የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​አስ ልጅ አሜ​ስ​ያስ ከእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ከኢ​ዮ​አ​ካዝ ልጅ ከዮ​አስ ሞት በኋላ ዐሥራ አም​ስት ዓመት ኖረ። 18የቀ​ረ​ውም የአ​ሜ​ስ​ያስ ነገር፥ ያደ​ረ​ገ​ውም ሁሉ፥ እነሆ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን? 19በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የዐ​መፅ መሐላ አደ​ረ​ጉ​በት፤ እር​ሱም ወደ ለኪሶ ኮበ​ለለ፤ ወደ ለኪ​ሶም ተከ​ተ​ሉት፤ በዚ​ያም ገደ​ሉት። 20በድ​ኑ​ንም በፈ​ረስ ጭነው አመ​ጡት፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም በዳ​ዊት ከተማ ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ቀበ​ሩት። 21የይ​ሁ​ዳም ሕዝብ ሁሉ የዐ​ሥራ ስድ​ስት ዓመት ልጅ የነ​በ​ረ​ውን ዓዛ​ር​ያ​ስን ወስ​ደው በአ​ባቱ በአ​ሜ​ስ​ያስ ፋንታ አነ​ገ​ሡት። 22ንጉ​ሡም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ከአ​ን​ቀ​ላፋ በኋላ፥ ኤላ​ትን ሠርቶ ወደ ይሁዳ መለ​ሳት።
የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ዳግ​ማዊ ኢዮ​ር​ብ​አም
23በይ​ሁዳ ንጉሥ በኢ​ዮ​አስ ልጅ በአ​ሜ​ስ​ያስ በዐ​ሥራ አም​ስ​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ የዮ​አስ ልጅ ኢዮ​ር​ብ​ዓም በሰ​ማ​ርያ መን​ገሥ ጀመረ፤ አርባ አንድ ዓመ​ትም ነገሠ። 24በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ ነገር አደ​ረገ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ካሳ​ታ​ቸው ከና​ባጥ ልጅ ከኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ኀጢ​አት ሁሉ አል​ራ​ቀም። 25በጋ​ት​ሔ​ፌር በነ​በ​ረው በአ​ማቴ ልጅ በባ​ሪ​ያው በነ​ቢዩ በዮ​ናስ አፍ እንደ ተና​ገ​ረው እንደ እስ​ራ​ኤል አም​ላክ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ድን​በር ከሔ​ማት መግ​ቢያ ጀምሮ እስከ ዓረባ ባሕር ድረስ መለሰ። 26በቍ​ጥር እን​ዳ​ነሱ፥ የታ​ሰ​ረ​ውና የተ​ለ​ቀ​ቀ​ውም እንደ ጠፋ፥ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም የሚ​ረዳ እን​ዳ​ል​ነ​በረ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅግ የመ​ረ​ረ​ውን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ጭን​ቀት አየ። 27እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ዘር ከሰ​ማይ በታች ይደ​መ​ስስ ዘንድ አል​ተ​ና​ገ​ረም፤ ነገር ግን በዮ​አስ ልጅ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም እጅ አዳ​ና​ቸው።
28የቀ​ረ​ውም የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ነገር፥ ያደ​ረ​ገ​ውም ሁሉ፥ ኀይ​ሉም፥ የይ​ሁዳ የነ​በ​ረ​ውን ደማ​ስ​ቆ​ንና ሔማ​ትን ለእ​ስ​ራ​ኤል እንደ መለሰ፥ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን? 29ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም እንደ አባ​ቶቹ እንደ እስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት አን​ቀ​ላፋ፤ ልጁም ዘካ​ር​ያስ በፋ​ን​ታው ነገሠ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ