የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ካልእ 10

10
የአ​ክ​አብ ወገ​ኖች እንደ ተገ​ደሉ
1ለአ​ክ​አ​ብም በሰ​ማ​ርያ ሰባ ልጆች ነበ​ሩት፤ ኢዩም ደብ​ዳቤ ጽፎ፥ የአ​ክ​አ​ብን ልጆች ለሚ​ያ​ሳ​ድጉ፥ ለሰ​ማ​ርያ አለ​ቆ​ችና ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ወደ ሰማ​ርያ ላከ። 2እን​ዲ​ህም አለ፥ “ይህ ደብ​ዳቤ አሁን በደ​ረ​ሳ​ችሁ ጊዜ የጌ​ታ​ችሁ ልጆች ሰረ​ገ​ሎ​ቹና ፈረ​ሶ​ቹም፥ የተ​መ​ሸጉ ከተ​ሞ​ቹም፥ የጦር መሣ​ሪ​ያ​ዎ​ቹም በእ​ና​ንተ ዘንድ አሉ፤ 3ከጌ​ታ​ችሁ ልጆች ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኛ​ች​ሁ​ንና የሚ​ሻ​ላ​ች​ሁን ምረጡ፤ በአ​ባ​ቱም ዙፋን አስ​ቀ​ም​ጡት፤ ስለ ጌታ​ች​ሁም ቤት ተዋጉ።” 4እነ​ር​ሱም እጅግ ፈር​ተው፥ “እነሆ፥ ሁለቱ ነገ​ሥ​ታት በፊቱ ይቆሙ ዘንድ አል​ቻ​ሉም፤ እኛስ እን​ዴት በፊቱ መቆም እን​ች​ላ​ለን?” አሉ። 5የአ​ክ​አ​ብም የቤቱ አለ​ቆች፥ የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም አለ​ቆች፥ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቹና ልጆ​ቹ​ንም የሚ​ያ​ሳ​ድጉ፥ “እኛ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ነን፤ ያዘ​ዝ​ኸ​ን​ንም ሁሉ እና​ደ​ር​ጋ​ለን፤ የም​ና​ነ​ግ​ሠው ሰው የለም፤ የም​ት​ወ​ድ​ደ​ውን አድ​ርግ” ብለው ወደ ኢዩ ላኩ። 6ከዚ​ህም በኋላ ኢዩ፥ “ወገ​ኖ​ቼስ ከሆ​ና​ችሁ፥ ነገ​ሬ​ንም ከሰ​ማ​ችሁ የጌ​ታ​ች​ሁን ልጆች ራስ ቍረጡ፤ ነገም በዚህ ሰዓት ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ወደ እኔ ይዛ​ችሁ ኑ” ብሎ ሁለ​ተኛ ደብ​ዳቤ ጻፈ​ላ​ቸው። የን​ጉ​ሡም ልጆች ሰባው ሰዎች በሚ​ያ​ሳ​ድ​ጓ​ቸው በከ​ተ​ማ​ዪቱ ታላ​ላ​ቆች ዘንድ ነበሩ። 7ደብ​ዳ​ቤ​ውም በደ​ረ​ሳ​ቸው ጊዜ የሀ​ገሩ ሰዎች የን​ጉ​ሡን ልጆች ሰባ​ውን ሰዎች ይዘው ገደ​ሉ​አ​ቸው፤ ራሳ​ቸ​ው​ንም በቅ​ር​ጫት አድ​ር​ገው ወደ እርሱ ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ላኩ። 8መል​እ​ክ​ተ​ኛም መጥቶ፥ “የን​ጉ​ሡን ልጆች ራስ ይዘው መጥ​ተ​ዋል” ብሎ ነገ​ረው። ንጉ​ሡም፥ “እስከ ነገ ድረስ በበሩ አደ​ባ​ባይ ሁለት ክምር አድ​ር​ጋ​ችሁ አኑ​ሩ​አ​ቸው” አለ። 9በነ​ጋ​ውም ንጉሡ ወጥቶ ቆመ፤ ሕዝ​ቡ​ንም ሁሉ፥ “እና​ንተ ንጹ​ሓን ናችሁ፤ እነሆ፥ የጌ​ታ​ዬን ቤት የወ​ነ​ጀ​ልሁ የገ​ደ​ል​ኋ​ቸ​ውም እኔ ነኝ፤ እነ​ዚ​ህ​ንስ ሁሉ የገ​ደለ ማን ነው? 10እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ክ​አብ ቤት ላይ ከተ​ና​ገ​ረው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በም​ድር ላይ አን​ዳች እን​ዳ​ይ​ወ​ድቅ አሁን ዕወቁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በባ​ሪ​ያው በኤ​ል​ያስ ቃል የተ​ና​ገ​ረ​ውን አድ​ር​ጎ​አል” አላ​ቸው። 11ኢዩም ከአ​ክ​አብ ቤት በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል የቀ​ረ​ውን ሁሉ፥ ታላ​ላ​ቆ​ቹ​ንም ሁሉ፥ ወዳ​ጆ​ቹ​ንና ካህ​ና​ቱን ሁሉ ገደ​ላ​ቸው፤ ከእ​ነ​ርሱ አን​ድስ እንኳ አላ​ስ​ቀ​ረም።
የአ​ካ​ዝ​ያስ ዘመ​ዶች እንደ ተገ​ደሉ
12ተነ​ሥ​ቶም ወደ ሰማ​ርያ ሄደ፤ በመ​ን​ገ​ድም ወዳ​ለው ወደ በግ ጠባ​ቂ​ዎች ቤት በደ​ረሰ ጊዜ፥ 13ኢዩ ከይ​ሁዳ ንጉሥ ከአ​ካ​ዝ​ያስ ወን​ድ​ሞች ጋር ተገ​ና​ኝቶ፥ “እና​ንተ እነ​ማን ናችሁ?” አለ፤ እነ​ር​ሱም፥ “እኛ የይ​ሁዳ ንጉሥ የአ​ካ​ዝ​ያስ ወን​ድ​ሞች ነን፤ የን​ጉ​ሡ​ንና የእ​ቴ​ጌ​ዪ​ቱን ልጆች ደኅ​ን​ነት እን​ነ​ግ​ረው ዘንድ ወረ​ድን” አሉት። 14እር​ሱም፥ “በሕ​ይ​ወ​ታ​ቸው ያዙ​አ​ቸው” ብሎ አዘዘ። በበግ ጠባ​ቂ​ዎች ቤትም አጠ​ገብ አርባ ሁለ​ቱን ሰዎች ገደ​ሉ​አ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም አንድ ሰው እንኳ አላ​ስ​ቀ​ረም።
15ከዚ​ያም በሄደ ጊዜ የሬ​ካ​ብን ልጅ ኢዮ​ና​ዳ​ብን በመ​ን​ገድ አገ​ኘው፤ ተቀ​ብ​ሎም መረ​ቀው፤ ኢዩም፥ “ልቤ ከል​ብህ ጋር ቅን እንደ ሆነ ያህል ልብህ ከልቤ ጋር በቅ​ን​ነት ነውን?” አለው። ኢዮ​ና​ዳ​ብም፥ “አዎን” አለው። ኢዩም፥ “እው​ነ​ት​ህስ ከሆነ እጅ​ህን ስጠኝ” አለ። እጁ​ንም ሰጠው፤ ወደ እር​ሱም ወደ ሰረ​ገ​ላው አወ​ጣው። 16“ከእኔ ጋር ና፥ ለሠ​ራ​ዊት ጌታ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ደ​ም​ቀና ታያ​ለህ” አለው። ከእ​ር​ሱም ጋር በሰ​ረ​ገ​ላው አስ​ቀ​መ​ጠው። 17ወደ ሰማ​ር​ያም ገብቶ ለኤ​ል​ያስ እንደ ተና​ገ​ረው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እስ​ኪ​ያ​ጠ​ፋው ድረስ በሰ​ማ​ርያ የቀ​ረ​ውን የአ​ክ​አ​ብን ሰው ገደለ።
በዓ​ልን የሚ​ያ​መ​ልኩ ሁሉ እንደ ተገ​ደሉ
18ኢዩም ሕዝ​ቡን ሁሉ ሰብ​ስቦ፥ “አክ​አብ በዓ​ልን በጥ​ቂቱ አመ​ለ​ከው፤ ኢዩ ግን በብዙ ያመ​ል​ከ​ዋል። 19አሁ​ንም የበ​ዓ​ልን ነቢ​ያት ሁሉ፥ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹ​ንም ሁሉ፥ ካህ​ና​ቱ​ንም ሁሉ ወደ እኔ ጥሩ፤ ማንም እን​ዳ​ይ​ቀር፤ ለበ​ዓል ታላቅ መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ር​ባ​ለሁ፤ የቀ​ረ​ውም ሁሉ በሕ​ይ​ወት አይ​ኖ​ርም” አላ​ቸው። ኢዩ ግን የበ​ዓ​ልን አገ​ል​ጋ​ዮች ያጠፋ ዘንድ በተ​ን​ኮል ይህን አደ​ረገ። 20ኢዩም፥ “ለበ​ዓል መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁን አንጹ” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም አዋጅ ነገሩ። 21ኢዩም ወደ እስ​ራ​ኤል ሀገ​ሮች ሁሉ ላከ፤ የበ​ዓ​ልም አገ​ል​ጋ​ዮች ሁሉ፥ ካህ​ና​ቱም ሁሉ፥ ነቢ​ያ​ቶ​ቹም ሁሉ መጡ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ሳይ​መጣ የቀረ አንድ ሰው እንኳ አል​ነ​በ​ረም። ሁሉም ወደ በዓል ቤት ገቡ፤ የበ​ዓ​ል​ንም ቤት ከዳር እስከ ዳር ድረስ ሞሉት። 22የዕቃ ቤቱ​ንም ሹም፥ “ለበ​ዓል አገ​ል​ጋ​ዮች ሁሉ ልብ​ስን አውጣ” አለው። የሚ​ያ​ለ​ብ​ሳ​ቸ​ው​ንም ልብ​ሱን አወ​ጣ​ላ​ቸው። 23ኢዩና የሬ​ካብ ልጅ ኢዮ​ና​ዳ​ብም ወደ በዓል ቤት ገቡ። የበ​ዓ​ል​ንም አገ​ል​ጋ​ዮች፥ “መር​ምሩ፥ ከበ​ዓል አገ​ል​ጋ​ዮች ብቻ በቀር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከሚ​ያ​መ​ልኩ ወገን በእ​ና​ንተ ዘንድ አንድ እንኳ እን​ዳ​ይ​ኖር ተመ​ል​ከቱ” አላ​ቸው። 24የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትና ሌላ መሥ​ዋ​ዕ​ትም ያቀ​ርቡ ዘንድ ገቡ፤ ኢዩም፥ “በእ​ጃ​ችሁ አሳ​ልፌ ከም​ሰ​ጣ​ችሁ ሰዎች አንድ ሰው ያመ​ለጠ እንደ ሆነ ነፍሱ በዚያ እን​ዲ​ያ​መ​ልጥ ባደ​ረ​ገው ሰው ነፍስ ፋንታ ትሆ​ና​ለች” ብሎ በውጭ ሰማ​ንያ ሰዎ​ችን አዘ​ጋ​ጅቶ ነበር።
25የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት አቅ​ር​በው በፈ​ጸሙ ጊዜ ኢዩ ዘበ​ኞ​ቹ​ንና አለ​ቆ​ቹን፥ “ግቡና ግደ​ሉ​አ​ቸው፤ አን​ድም አያ​ም​ልጥ” አላ​ቸው። በሰ​ይ​ፍም ስለት ገደ​ሉ​አ​ቸው፤ ዘበ​ኞ​ችና አለ​ቆ​ችም ወደ ውጭ ጣሉ​አ​ቸው፤ ወደ በዓ​ልም ቤት ከተማ ሄዱ። 26ከበ​ዓ​ልም ቤት ሐው​ል​ቶ​ቹን አወጡ፤ አቃ​ጠ​ሉ​አ​ቸ​ውም። 27የበ​ዓ​ልን ሐው​ልት ቀጠ​ቀጡ፤ የበ​ዓ​ል​ንም ቤት አፈ​ረሱ፤ እስከ ዛሬም ድረስ የው​ዳቂ መጣያ አደ​ረ​ጉት።
28እን​ዲ​ሁም ኢዩ በዓ​ልን ከእ​ስ​ራ​ኤል አጠፋ። 29ነገር ግን እስ​ራ​ኤ​ልን ካሳ​ተው ከና​ባጥ ልጅ ከኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ኀጢ​አት ኢዩ አል​ራ​ቀም፥ በቤ​ቴ​ልና በዳን የነ​በ​ሩ​ትን የወ​ርቅ እን​ቦ​ሶ​ች​ንም፥ አላ​ስ​ወ​ገ​ደም። 30እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢዩን፥ “በፊቴ ቅን ነገር አድ​ር​ገ​ሃ​ልና፥ በል​ቤም ያለ​ውን ሁሉ በአ​ክ​አብ ቤት ላይ አድ​ር​ገ​ሃ​ልና ልጆ​ችህ እስከ አራት ትው​ልድ ድረስ በእ​ስ​ራ​ኤል ዙፋን ላይ ይቀ​መ​ጣሉ” አለው። 31ኢዩ ግን በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ በፍ​ጹም ልቡ ይሄድ ዘንድ አል​ተ​ጠ​ነ​ቀ​ቀም፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ካሳ​ተው ከኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ኀጢ​አት አል​ራ​ቀም።
32በዚ​ያም ወራት እዚ​አ​ብ​ሔር እስ​ራ​ኤ​ልን ያጠፋ ጀመረ፤ አዛ​ሄ​ልም በእ​ስ​ራ​ኤል ዳርቻ ሁሉ መታ​ቸው። 33በዮ​ር​ዳ​ኖስ ምሥ​ራቅ ያለ​ውን የገ​ለ​ዓ​ድን ሀገር ሁሉ፥ በአ​ር​ኖን ወንዝ አጠ​ገብ ካለ​ችው ከአ​ሮ​ዔር ጀምሮ የጋ​ድ​ንና የሮ​ቤ​ልን የም​ና​ሴ​ንም ሀገር፥ ገለ​ዓ​ድ​ንና ባሳ​ንን መታ። 34የቀ​ረ​ውም የኢዩ ነገር፥ የሠ​ራ​ውም ሥራ ሁሉ፥ ኀይ​ሉም ሁሉ፥ የገ​ደ​ለ​ውም ሁሉ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን? 35ኢዩም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በሰ​ማ​ር​ያም ቀበ​ሩት። በፋ​ን​ታ​ውም ልጁ ኢዩ​አ​ካዝ ነገሠ። 36ኢዩም በሰ​ማ​ርያ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ የነ​ገ​ሠ​በት ዘመን ሃያ ስም​ንት ዓመት ነበረ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ