የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ዕዝራ ካልእ 2

2
1በፋ​ርስ ንጉሥ በቂ​ሮስ መን​ግ​ሥት በመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ዪቱ ዓመት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በነ​ቢዩ በኤ​ር​ም​ያስ አፍ የተ​ና​ገ​ረው ቃል ደረሰ። 2እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የፋ​ር​ስን ንጉሥ የቂ​ሮ​ስን መን​ፈስ አነ​ሣሣ፤ በመ​ን​ግ​ሥ​ቱም ሁሉ ዐዋጅ ነገረ፤ እን​ዲ​ህም ብሎ ጻፈ። 3የፋ​ርስ ንጉሥ ቂሮስ እን​ዲህ ይላል፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ልዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አነ​ገ​ሠኝ። 4በይ​ሁዳ ባለ​ችው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቤተ መቅ​ደ​ስን እሠ​ራ​ለት ዘንድ አዘ​ዘኝ፤ 5ስለ​ዚህ ከእ​ና​ንተ ውስጥ ከሕ​ዝቡ ወገን የሆነ ቢኖር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ርሱ ጋር ይሁን፤ በይ​ሁዳ ወደ አለች ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ይውጣ፤ ለእ​ስ​ራ​ኤል ጌታ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቤተ መቅ​ደ​ስን ይሥራ።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያድ​ራ​ልና” የሚል ይጨ​ም​ራል። 6በያ​ገ​ራ​ችሁ ያላ​ችሁ ሁሉ በየ​አ​ው​ራ​ጃ​ችሁ ወር​ቁ​ንና ብሩን ርዱ። 7እና​ን​ተም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤተ መቅ​ደስ ፈረ​ሱ​ንና ከብ​ቱን ስእ​ለት ካለው ሁሉ ጋር ጨምሩ።
8“የይ​ሁ​ዳና የብ​ን​ያም ሀገ​ሮች መሳ​ፍ​ን​ትም በየ​ነ​ገ​ዳ​ቸው፥ ሕዝ​ቡም፥ ካህ​ና​ቱም፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ልቡ​ና​ውን ያነ​ሣ​ሣ​ለት ሁሉ ይውጣ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያለ​ው​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤተ መቅ​ደስ ይሥራ። 9ባው​ራ​ጃ​ቸው ያሉም በወ​ር​ቅና በብር፥ በፈ​ረ​ስና በከ​ብት ሁሉ፥ ስእ​ለት ያለ​ባ​ቸ​ውም፥ ልቡ​ና​ውም የወ​ደደ ሁሉ ይር​ዷ​ቸው።”
10ንጉሥ ቂሮ​ስም ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወስዶ በጣ​ዖ​ቶቹ ቤት ያኖ​ረ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ንዋየ ቅድ​ሳት አወጣ። 11የፋ​ርስ ንጉሥ ቂሮ​ስም ንዋየ ቅዱ​ሳ​ቱን ባወጣ ጊዜ ለጠ​ባ​ቂው ለሚ​ት​ረ​ዳጡ ሰጠው፥ 12ለይ​ሁዳ የተ​ሾ​መው ሰል​ም​ና​ስም#“ሰሳ​ብ​ሳር፥ ሸሻ​ባ​ፃር፥ ሰና​ባ​ሳር” የሚል ዘርዕ አለ። ከእ​ርሱ ተቀ​በለ፤ 13ቍጥ​ሩም እን​ዲህ ነው፦ የወ​ርቁ ወጭት አንድ ሺህ፥#ግእዙ “ሠላሳ” ይላል። የብ​ሩም ወጭት አንድ ሺህ ነው። የብር ሳህ​ኖች ሃያ ዘጠኝ፥ የወ​ርቅ ጽዋ​ዎ​ችም ሠላሳ፥ የብ​ርም ጽዋ​ዎች ሁለት ሺህ አራት መቶ ዐሥር፥ ሌሎች ዕቃ​ዎች ግን አንድ ሺህ ነበሩ። 14የተ​መ​ለ​ሰ​ውም የወ​ር​ቁና የብሩ ዕቃ ሁሉ ተዳ​ምሮ አም​ስት ሺህ አራት መቶ ስድሳ ዘጠኝ ነበር። 15ስል​ም​ና​ሶ​ርም ከም​ር​ኮ​ኞቹ ጋር ከባ​ቢ​ሎን ወስዶ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም አገ​ባው።
በግ​ንቡ ሥራ ላይ የደ​ረሰ ተቃ​ውሞ
16ከእ​ነ​ር​ሱም ውስጥ የፋ​ርስ ንጉሥ አር​ጤ​ክ​ስስ በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አው​ራ​ጃ​ዎች ያስ​ቈ​ጠ​ራ​ቸው አሉ፤ ቤል​ሞ​ስና ሚጥ​ራ​ዳጢ፥ ጠቢ​ል​ዮ​ስና ራቲ​ሞስ፥ ቤሔ​ል​ጤ​ሞ​ስና ጸሓ​ፊው ሲሳ​ዮስ፥#ሀ. ቤሴ​ል​ሞስ ለ. ሮኡ​ሞስ ሐ. ሳማ​ሴ​ዎስ። ከነ​ዚ​ህም በታች ያሉ በሰ​ማ​ርያ የሚ​ኖሩ ሁሉ፥ በሌ​ላም ሀገር ያሉ ሁሉ እን​ዲህ ብለው መል​እ​ክት ጻፉ። 17“ለጌ​ታ​ችን ለን​ጉሡ ለአ​ር​ጤ​ክ​ስስ፦ ከብ​ላ​ቴ​ኖ​ችህ፥ ከታ​ሪክ ጸሓ​ፊህ ከራ​ቲ​ሞ​ስና ከጸ​ሓ​ፊው ከሰ​ሜ​ል​ዮስ#ሮኡ​ሞስ... ሳማ​ሴ​ዎስ ከእ​ነ​ርሱ በታች ከተ​ሾ​ሙት ሁሉና በቄሌ-ሶር​ያና በፊ​ኒቄ ከሚ​ኖሩ ሁሉ፦ 18አሁ​ንም ጌታ​ችን ንጉሥ ሆይ፥ ይህን ዕወቅ፤ ከእ​ና​ንተ ወደ እኛ የመጡ አይ​ሁድ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሄደው፥ ክፉና ከዳ​ተኛ ከተ​ማን ይገ​ነ​ባሉ፤ የገ​በያ ቦታ​ዎ​ች​ዋ​ንና ቅፅ​ሮ​ች​ዋን፥ ቤተ መቅ​ደ​ስ​ዋ​ንም ያድ​ሳሉ። 19ያችም ከተማ ከተ​ሠ​ራች፥ ቅፅ​ሯም ካለቀ፥ ከዚያ በኋላ ግብር አይ​ገ​ብ​ሩም፤ ዳግ​መ​ኛም መን​ግ​ሥ​ታ​ች​ንን ይቀ​ማሉ። 20ቤተ መቅ​ደ​ስ​ንም አሳ​ም​ረው ይሠ​ራሉ። አሁ​ንም ስለ​ዚህ ቸል አት​በል። 21በአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ ይፈ​ልጉ ዘንድ ወደ ንጉሡ ወደ ቂሮስ ላክ። 22ያች ከተማ ነገ​ሥ​ታ​ቱን የም​ት​ከ​ዳና ከተ​ሞ​ችን እን​ደ​ም​ታ​ውክ፥ ስለ​ዚህ የተ​ጻፈ ታገ​ኛ​ለህ። 23አይ​ሁ​ድም ከጥ​ንት ጀምሮ ከዳ​ተ​ኞች እንደ ሆኑ ተጽፎ ታገ​ኛ​ለህ፤ ስለ​ዚ​ህም ያች ከተማ ጠፍታ ነበር። 24አሁ​ንም ጌታ​ችን ንጉሥ ሆይ፥ እን​ነ​ግ​ር​ሃ​ለን፤ ያች ከተማ ከተ​ሠ​ራች፥ ቅጽ​ሮ​ች​ዋም ከተ​ፈ​ጸሙ በኋላ ወደ ቄሌ-ሶር​ያና ወደ ፊንቄ አያ​ሳ​ል​ፏ​ች​ሁም።”
25ከዚህ በኋላ ንጉሡ ለጻ​ፈ​ለት ለታ​ሪክ ጸሓ​ፊው ለራ​ቲ​ሞ​ስና ለቤ​ሔ​ል​ማ​ቴም፥ ለጸ​ሓ​ፊው ለሳ​ሚ​ል​ዮ​ስም በሰ​ማ​ር​ያና በፊ​ኒ​ቂስ ለሚ​ኖሩ፥ ከእ​ነ​ርሱ በታች ላሉ፥ ለቀ​ሩ​ትም እንደ ጻፉ​ለት እን​ዲህ የም​ትል ደብ​ዳ​ቤን ጻፈ​ላ​ቸው። 26“እኔም የላ​ካ​ች​ሁ​ል​ኝን ደብ​ዳቤ አን​ብቤ ይፈ​ልጉ ዘንድ አዘ​ዝሁ፤ ያቺም ከተማ ከጥ​ንት ጀምሮ ነገ​ሥ​ታ​ቱን የም​ት​ከዳ እንደ ሆነች አገ​ኘሁ። 27ሰዎ​ችም ከዳ​ተ​ኞች እንደ ነበሩ፥ ሥራ​ቸ​ውም ጦር​ነት እንደ ነበረ፥ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ነገ​ሥ​ታት ጠን​ካ​ሮ​ችና ክፉ​ዎች እንደ ነበሩ፥ ቄሌ-ሶር​ያ​ንና ፊኒ​ቄን እንደ ገዙና እን​ደ​ገ​በ​ሩ​ላ​ቸው አገ​ኘሁ። 28አሁ​ንም እነ​ዚ​ያን ሰዎች ያቺን ከተማ መሥ​ራ​ትን እን​ዲ​ከ​ለ​ክ​ሏ​ቸው፥ 29ነገ​ሥ​ታ​ትም ይደ​ክሙ ዘንድ ክፋ​ትን እን​ዳ​ታ​በዛ በው​ስጧ ምንም የሚ​ሠራ እን​ዳ​ይ​ኖር እነሆ አዘ​ዝሁ።”
30ከዚህ በኋላ ራቲ​ሞ​ስና ጸሓ​ፊው ስል​ም​ዮስ፥ ከእ​ነ​ዚ​ህም በታች ያሉት ንጉሡ አር​ጤ​ክ​ስስ የጻ​ፋ​ትን ያችን መል​እ​ክት ባነ​በ​ቧት ጊዜ ከብዙ ሰዎች ጋር በብዙ ችኮላ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ፈረ​ሶ​ቻ​ቸ​ውን አስ​ነሡ፤ የሚ​ሠ​ሩ​ት​ንም ይከ​ለ​ክሉ ጀመሩ። 31የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቤተ መቅ​ደስ ሥራም እስከ ፋርስ ንጉሥ ዳር​ዮስ ሁለ​ተ​ኛ​ዪቱ ዘመነ መን​ግ​ሥት ድረስ ቆመ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ