የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ዕዝራ ካልእ 1

1
1ኢዮ​ስ​ያስ ለፈ​ጣ​ሪው የፋ​ሲ​ካ​ውን በግ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም አመጣ፤ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወርም በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ቀን የፋ​ሲ​ካ​ውን በግ ሠዋ። 2ካህ​ና​ቱ​ንም የአ​ገ​ል​ግ​ሎት ልብ​ሳ​ቸ​ውን አል​ብሶ አቆ​ማ​ቸው፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤተ መቅ​ደስ በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው ሠራ​ቸው። 3#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የእ​ስ​ራ​ኤል የቤተ መቅ​ደስ አገ​ል​ጋ​ዮች ሌዋ​ው​ያ​ንን ራሳ​ቸ​ውን እን​ዲ​ያ​ነ​ጹና የዳ​ዊት ልጅ ሰሎ​ሞን በሠ​ራው ቤተ መቅ​ደስ የጌ​ታን ቅዱስ ታቦት እን​ዲ​ያ​ስ​ቀ​ምጡ ነገ​ራ​ቸው” ይላል።ሌዋ​ው​ያ​ን​ንም አላ​ቸው፥ “ለእ​ስ​ራ​ኤል ካህ​ናት ተገዙ፤ የን​ጉሡ የዳ​ዊት ልጅ ሰሎ​ሞን በሠ​ራው ቤተ መቅ​ደ​ስም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ቅድ​ስና ሥር​ዐት አክ​ብ​ሯ​ቸው። 4ታቦ​ቱ​ንም በጫ​ን​ቃ​ችሁ መሸ​ከም አይ​ገ​ባ​ች​ሁም። አሁ​ንም ፈጣ​ሪ​ያ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አም​ል​ኩት፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ሕዝብ አገ​ል​ግሉ። 5እንደ እስ​ራ​ኤል ንጉሥ እንደ ዳዊት መጽ​ሐ​ፍና እንደ ልጁ ሰሎ​ሞ​ንም ገና​ና​ነት በየ​ሀ​ገ​ራ​ች​ሁና በየ​ነ​ገ​ዳ​ችሁ ተዘ​ጋጁ፤ ሌዋ​ው​ያ​ንም በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት በቤተ መቅ​ደስ በየ​ቦ​ታ​ች​ሁና በየ​ሀ​ገ​ራ​ችሁ ግዛት በየ​ሹ​መ​ታ​ችሁ ቁሙ። 6የፋ​ሲ​ካ​ው​ንም በግ ሠዉ፤ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁም መሥ​ዋ​ዕ​ቱን አዘ​ጋጁ፤ ለሙሴ በተ​ሰ​ጠው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕግ ፋሲ​ካን አድ​ርጉ።”
7ኢዮ​ስ​ያ​ስም በዚያ ለነ​በሩ ሰዎች ሠላሳ ሺህ ፍየ​ሎ​ች​ንና በጎ​ችን፥ ሦስት ሺህ በሬ​ዎ​ች​ንም ሰጣ​ቸው፤ እን​ደ​ዚ​ሁም ለሕ​ዝቡ፥ ለካ​ህ​ና​ቱና ለሌ​ዋ​ው​ያ​ኑም ከን​ጉሥ ቤት አዝዞ ሰጠ። 8የቤተ መቅ​ደ​ሱም ሹሞች ኬል​ቅ​ያስ፥ ዘካ​ር​ያ​ስና ሲሉ​ያስ ለካ​ህ​ናቱ ለፋ​ሲካ በዓል ሁለት ሺህ ስድ​ስት መቶ በጎ​ች​ንና ሦስት መቶ በሬ​ዎ​ችን ሰጧ​ቸው። 9መሳ​ፍ​ን​ቱም ኢኮ​ን​ያ​ስና ሳሚ​ያስ፥ ወን​ድሙ ናት​ና​ኤ​ልና ሲብ​ያስ፥ ኪያ​ሎ​ስና ኢዮ​ራም ለሌ​ዋ​ው​ያን ለፋ​ሲ​ካ​ቸው ሺህ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “አም​ስት ሺህ” ይላል። በጎ​ች​ንና ሰባት መቶ በሬ​ዎ​ችን ሰጧ​ቸው።
10ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያ​ኑም እንደ ሕጉ እን​ዲሁ መል​ካም አደ​ረጉ፤ ቂጣ​ው​ንም በየ​ነ​ገ​ዳ​ቸው ተመ​ገቡ። 11በሙሴ መጽ​ሐ​ፍም እንደ ተጻፈ በሕ​ዝቡ ፊት በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ሹመት መሥ​ዋ​ዕ​ቱን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቀ​ረቡ። 12በነ​ጋ​ውም እን​ደ​ዚሁ እንደ ሥር​ዐ​ታ​ቸው የፋ​ሲ​ካ​ውን በግ በእ​ሳት ሠዉ፤ መሥ​ዋ​ዕ​ቶ​ች​ንም በጋ​ንና በብ​ረት ምጣድ አበ​ሰሉ። 13ለሕ​ዝ​ቡም ሁሉ በጎ መዓዛ ያለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ሠሩ​ላ​ቸው፤ ከዚ​ህም በኋላ ለራ​ሳ​ቸ​ውና ለወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ለአ​ሮን ልጆች ካህ​ናት አዘ​ጋ​ጁ​ላ​ቸው።
14ካህ​ናቱ ግን ቀኑ እስ​ኪ​መሽ ድረስ የሰ​ባ​ውን መሥ​ዕ​ዋት ሠዉ፤ ሌዋ​ው​ያ​ኑም ለራ​ሳ​ቸ​ውና ለወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ለአ​ሮን ልጆች ሠዉ። 15መዘ​ም​ራኑ የአ​ሳፍ ልጆ​ችም ዳዊት በሠ​ራው ሥር​ዐት በሹ​መ​ታ​ቸው ነበሩ፤ ከን​ጉሡ የተ​ሾሙ አሳ​ፍና ዘካ​ር​ያስ፥ ዐዲ​ኑ​ስም ነበሩ። 16የበሩ ሁሉ ጠባ​ቂ​ዎ​ችም ነበሩ፤ ከሰ​ሞ​ኑም የሚ​ያ​ጓ​ድል አል​ነ​በ​ረም፤ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ሌዋ​ው​ያን ያዘ​ጋ​ጁ​ላ​ቸው ነበ​ርና። 17ያን​ጊ​ዜም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መሥ​ዋ​ዕት አቅ​ር​በው ጨረሱ። 18ንጉሡ ኢዮ​ስ​ያስ እን​ዳ​ዘ​ዘም ፋሲ​ካ​ቸ​ውን አደ​ረጉ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መሠ​ዊያ መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውን አቀ​ረቡ።
19በእ​ነ​ዚ​ያም ወራ​ቶች የነ​በሩ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፋሲ​ካ​ንና የቂ​ጣ​ውን በዓል ለሰ​ባት ቀን አደ​ረጉ። 20ከነ​ቢዩ ከሳ​ሙ​ኤ​ልም ዘመን ወዲህ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ እንደ እርሱ ያለ በዓል አል​ተ​ደ​ረ​ገም። 21የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ነገ​ሥ​ታት ሁሉ ኢዮ​ስ​ያስ እን​ዳ​ደ​ረ​ገው ፋሲ​ካን አላ​ደ​ረ​ጉም፤ ሌዋ​ው​ያ​ንና ካህ​ናት፥ አይ​ሁ​ድና ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጥ​ተው በዚያ የነ​በሩ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ አላ​ደ​ረ​ጉም። 22ኢዮ​ስ​ያስ በነ​ገሠ በዐ​ሥራ ስም​ን​ተ​ኛው ዓመት ይህን ፋሲካ አደ​ረገ።
የኢ​ዮ​ስ​ያስ ዘመነ መን​ግ​ሥት ፍጻሜ
23የኢ​ዮ​ስ​ያ​ስም ሥራው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት በተ​መ​ላ​በት ልቡና በፈ​ጣ​ሪው ፊት የቀና ነበር። 24በቀ​ድ​ሞው ዘመን ከአ​ሕ​ዛ​ብና ከመ​ን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈጽ​መው ስለ በደ​ሉ​ትና ስለ አሳ​ዘ​ኑት ሰዎች እንደ ተጻፈ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ቃሉን አጸና። 25ከዚ​ህም ከኢ​ዮ​ስ​ያስ ሥራ ሁሉ በኋላ፦ የግ​ብፅ ንጉሥ ፈር​ዖን በኤ​ፍ​ራ​ጥስ ወንዝ በከ​ር​ከ​ሚስ ሠራ​ዊ​ቱን ይዞ ዘመተ፤ ኢዮ​ስ​ያ​ስም ወጥቶ ተቀ​በ​ለው። 26የግ​ብፅ ንጉ​ሥም፥ “የይ​ሁዳ ንጉሥ ሆይ፥ እኔ ካንተ ጋራ ምን አለኝ?” ብሎ ላከ​በት። 27“ከጌታ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በአ​ንተ ላይ የተ​ላ​ክሁ አይ​ደ​ለም፥ እኔ የም​ወጋ ኤፍ​ራ​ጥ​ስን ነውና፥ አሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኔ ጋር ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእኔ ዘንድ አለ፤ እር​ሱም ይረ​ዳ​ኛል፤ ገለል በል፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጋር አት​ከ​ራ​ከር” አለው። 28ኢዮ​ስ​ያ​ስም በሠ​ረ​ገ​ላ​ዎቹ ሆኖ ገለል አል​ልም አለ፤ ይዋ​ጋም ዘንድ ጀመረ፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አፍ በነ​ቢዩ በኤ​ር​ም​ያስ የተ​ነ​ገ​ረ​ውን ቃል መስ​ማት እንቢ አለ። 29ነገር ግን መጊ​ዶስ በሚ​ባል ምድረ በዳ ይዋ​ጋ​ቸው ዘንድ ጸና፤ አለ​ቆ​ችም ወደ ንጉሡ ወደ ኢዮ​ስ​ያስ ወረዱ። 30ንጉ​ሡም ብላ​ቴ​ኖ​ቹን አላ​ቸው፥ “እጅግ ደክ​ሜ​አ​ለ​ሁና ከሰ​ልፉ ውስጥ አው​ጡኝ፥” ብላ​ቴ​ኖ​ቹም ወዲ​ያ​ውኑ ከሰ​ልፉ ውስጥ አወ​ጡት። 31በሌላ ሰረ​ገ​ላ​ውም ተቀ​ምጦ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ገባ፤ በዚ​ያም ሞተ፤ በአ​ባቱ መቃ​ብ​ርም ተቀ​በረ። 32በይ​ሁ​ዳም ሁሉ ለኢ​ዮ​ስ​ያስ አለ​ቀ​ሱ​ለት፤ ኤር​ም​ያ​ስም ለኢ​ዮ​ስ​ያስ አለ​ቀ​ሰ​ለት፤ እስ​ከ​ዚች ቀን ድረ​ስም ወን​ዶች ሁሉ ከሴ​ቶች ጋር አለ​ቀ​ሱ​ለት፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም እን​ዲሁ ያደ​ርጉ ዘንድ ለእ​ስ​ራ​ኤል ወገ​ኖች ሥር​ዐት ሆኖ ተሰጠ። 33ይህም በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት ታሪክ መጽ​ሐፍ ተጻፈ፤ ኢዮ​ስ​ያ​ስም የሠ​ራው ሥራ ሁሉ፥ ክብ​ሩም፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሕግ ማወቁ፥ በፊ​ትም፥ በኋ​ላም የሠ​ራው ሥራ ሁሉ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት ታሪክ መጽ​ሐፍ ተጽ​ፏል።
የመ​ጨ​ረ​ሻ​ዎቹ የይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት
34ሕዝ​ቡም የኢ​ዮ​ስ​ያ​ስን ልጅ ኢዮ​አ​ክ​ስን ወስ​ደው በተ​ወ​ለደ በሃያ ሦስት ዓመት ዕድ​ሜው በአ​ባቱ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ፋንታ አነ​ገ​ሡት። 35#2ነገ​ሥት ምዕ. 23 ቍ. 31 “ለእ​ስ​ራ​ኤል” እይ​ልም።ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሦስት ወር ነገሠ፤ የግ​ብፅ ንጉ​ሥም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ከመ​ን​ግ​ሥት አወ​ረ​ደው። 36ሕዝ​ቡ​ንም ሁለት መቶ መክ​ሊት ብርና አንድ መክ​ሊት ወርቅ አስ​ገ​በ​ራ​ቸው።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “አንድ መቶ መክ​ሊት ብር” ይላል። 37የግ​ብፅ ንጉ​ሥም ወን​ድ​ሙን ኢዮ​አ​ቄ​ምን የይ​ሁዳ ንጉሥ አድ​ርጎ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አነ​ገ​ሠው። 38ኢዮ​አ​ቄ​ምም መሳ​ፍ​ን​ቱን አሰ​ራ​ቸው፤ ወን​ድሙ ዛር​ዮ​ን​ንም ይዞ ወደ ግብፅ አገ​ባው።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ከግ​ብፅ መለ​ሰው” ይላል። 39ኢዮ​አ​ቄ​ምም በይ​ሁዳ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በነ​ገሠ ጊዜ ዕድ​ሜው ሃያ አም​ስት ዓመት ሆኖት ነበር፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ አደ​ረገ። 40ከዚ​ህም በኋላ የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ወደ እርሱ ዘመተ፤ በብ​ረት ሰን​ሰ​ለ​ትም አስሮ ወደ ባቢ​ሎን ሰደ​ደው። 41ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ንዋየ ቅድ​ሳት ወስዶ ወደ ባቢ​ሎን አገ​ባው፤ በጣ​ዖ​ቱም ቤት አኖ​ረው። 42ይህም በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት ታሪክ መጽ​ሐፍ ተጽ​ፎ​አል።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ስለ ኢዮ​አ​ቄም የተ​ነ​ገ​ረው ርኵ​ሰ​ቱና ክፋቱ ሁሉ...” ይላል 43ከዚ​ህም በኋላ ልጁ ኢኮ​ን​ያስ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ኢዮ​አ​ኪም” ይላል። ነገሠ፤ ዕድ​ሜ​ውም ዐሥራ ስም​ንት ዓመት ነበረ። 44ሦስት ወር ከዐ​ሥር ቀን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ነገሠ፤ እር​ሱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አደ​ረገ።
45ከዓ​መ​ትም በኋላ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ንዋየ ቅድ​ሳት ጋር ልኮ ወደ ባቢ​ሎን አገ​ባው። 46ሴዴ​ቅ​ያ​ስ​ንም በተ​ወ​ለደ በሃያ አንድ ዓመቱ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና በይ​ሁዳ አነ​ገ​ሠው፤ ዐሥራ አንድ ዓመ​ትም ነገሠ። 47በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ አደ​ረገ፤ በነ​ቢዩ በኤ​ር​ም​ያስ አፍ ከተ​ነ​ገ​ረው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል የተ​ነሣ አል​ፈ​ራም። 48ንጉሡ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም አማ​ለው፤ እርሱ ግን ከዳው፤ አን​ገ​ቱ​ንም አደ​ነ​ደነ፤ ልቡ​ና​ው​ንም አስ​ታ​በየ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ፈጣሪ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሕግ ተላ​ለፈ። 49የሕ​ዝ​ቡና የካ​ህ​ናቱ መሪ​ዎ​ችም ብዙ ተላ​ለፉ፤ ከአ​ሕ​ዛ​ብም ርኵ​ሰት ይልቅ እጅግ በደሉ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የተ​ቀ​ደ​ሰ​ች​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መቅ​ደስ አሳ​ደፉ።
የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ጥፋት
50የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይገ​ሥ​ጻ​ቸ​ውና ይመ​ል​ሳ​ቸው ዘንድ መል​እ​ክ​ተ​ኛ​ውን ላከ፤ ለእ​ነ​ር​ሱና ለመ​ቅ​ደ​ሳ​ቸው ይራ​ራ​ልና። 51እነ​ርሱ ግን በመ​ል​እ​ክ​ተ​ኞቹ ዘበ​ቱ​ባ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በተ​ና​ገ​ራ​ቸው ጊዜ በሕ​ዝቡ እስ​ኪ​ቈጣ ድረስ በነ​ቢ​ያት ይስ​ቁ​ባ​ቸው ነበር። 52ጣዖ​ቱን እጥፍ አድ​ር​ገው ያመ​ልኩ ነበ​ርና የከ​ላ​ው​ዴ​ዎን ክፍል የአ​ሦር ነገ​ሥ​ታ​ትም ይዘ​ም​ቱ​ባ​ቸው ዘንድ አዘዘ። 53መጥ​ተ​ውም በቤተ መቅ​ደሱ አደ​ባ​ባይ ጐል​ማ​ሶ​ቻ​ቸ​ውን በሰ​ይፍ ገደሉ፤ ለጐ​ል​ማ​ሳ​ውም፥ ለቆ​ን​ጆ​ዋም፥ ለት​ል​ቁም፥ ለት​ን​ሹም ቢሆን አል​ራ​ሩም፤ ሁሉ​ንም በእ​ጃ​ቸው አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው። 54የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ንዋየ ቅድ​ሳት ትል​ቁ​ንም ትን​ሹ​ንም ሁሉ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት፥ የን​ጉ​ሡ​ንም ቤት ዕቃ ሁሉ ዘር​ፈው ወደ ባቢ​ሎን ወሰዱ። 55የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት አቃ​ጠሉ፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ቅጽ​ሯን አፈ​ረሱ፤ ግን​ቧ​ንም በእ​ሳት አቃ​ጠሉ። 56ያማ​ረ​ው​ንም ዕቃ​ዋን ሁሉ አጠፉ፤ ከጦር የቀ​ሩ​ት​ንም ማር​ከው ወደ ባቢ​ሎን ወሰ​ዱ​አ​ቸው። 57በነ​ቢዩ በኤ​ር​ም​ያስ አፍ የተ​ነ​ገ​ረው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ይደ​ርስ ዘንድ፥ ፋር​ሳ​ው​ያን መግ​ዛት እስከ ጀመ​ሩ​በት ድረስ ለእ​ር​ሱና ለል​ጆቹ አገ​ል​ጋ​ዮች ሆኑ። 58ምድ​ርም በማ​ረ​ፍዋ ደስ ይላ​ታል፤ በተ​ፈ​ታ​ች​በ​ትም ዘመን ሁሉ ሰብ​ዓው ዘመን እስ​ኪ​ፈ​ጸም ድረስ ታር​ፋ​ለች።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ