የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 2 10

10
ስለ መን​ፈ​ሳዊ የጦር ዕቃ
1ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እኔ ጳው​ሎስ በእ​ና​ንተ ዘንድ ፊት ለፊት ሳለሁ ትሑት የሆ​ንሁ፥ ከእ​ና​ንተ ብርቅ ግን የም​ደ​ፍ​ራ​ችሁ በክ​ር​ስ​ቶስ የዋ​ህ​ነ​ትና ቸር​ነት እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ፥ በፍ​ቅ​ራ​ችሁ እታ​መ​ና​ለ​ሁና።#“በፍ​ቅ​ራ​ችሁ እታ​መ​ና​ለ​ሁና” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። 2ወደ እና​ንተ በመ​ጣሁ ጊዜ እሠ​ራ​ለሁ፤ በሥ​ጋዊ ሥር​ዐ​ትም እን​ደ​ም​ን​ኖር አድ​ር​ገው በሚ​ጠ​ረ​ጥ​ሩን ሰዎች ላይ በድ​ፍ​ረት ለመ​ና​ገር አስ​ባ​ለሁ፤ እና​ንተ ግን በዚህ ዓይ​ነት ድፍ​ረት እን​ድ​ና​ገር እን​ዳ​ታ​ደ​ር​ጉኝ እለ​ም​ና​ች​ኋ​ለሁ። 3በሥ​ጋ​ች​ንስ እን​ሄ​ዳ​ለን፤ ነገር ግን በእ​ር​ሱው ሥር​ዐት የም​ን​ሄ​ድና የም​ን​ዋጋ አይ​ደ​ለም። 4የጦር ዕቃ​ችን ሥጋዊ አይ​ደ​ለ​ምና፥ ጽኑ ምሽ​ግን በሚ​ያ​ፈ​ርስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይል ነው እንጂ። 5ልብ ሁሉ ይማ​ረክ ዘንድ ኅሊ​ናም ለክ​ር​ስ​ቶስ ይገዛ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ የሚ​ታ​በ​የ​ው​ንና ከፍ ከፍ የሚ​ለ​ውን እና​ፈ​ር​ሳ​ለን።#ግእዙ “... ያፈ​ር​ሳል ...” ይላል። 6እና​ንተ ትእ​ዛ​ዝን በፈ​ጸ​ማ​ችሁ ጊዜ የማ​ይ​ገ​ዛ​ውን ሁሉ እኛ ልን​በ​ቀ​ለው ዝግ​ጁ​ዎች ነን።
7በፊ​ታ​ችሁ ያለ​ውን ተመ​ል​ከቱ፤ ማንም በክ​ር​ስ​ቶስ ያመነ ቢሆን፥ ይህን እንደ ገና በራሱ ይቍ​ጠ​ረው፤ እርሱ የክ​ር​ስ​ቶስ እንደ ሆነ እኛም እን​ዲሁ ነንና። 8እና​ን​ተን ለማ​ነጽ እንጂ፥ እና​ን​ተን ለማ​ፍ​ረስ ያይ​ደለ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ና​ንተ ላይ በሰ​ጠን ሥል​ጣን እጅግ የተ​መ​ካ​ሁት መመ​ካት ቢኖር አላ​ፍ​ርም። 9ነገር ግን በመ​ል​እ​ክ​ቶች የማ​ስ​ፈ​ራ​ራ​ችሁ እን​ዳ​ይ​መ​ስ​ላ​ችሁ፥ ይህን ትም​ክ​ሕ​ቴን እተ​ወ​ዋ​ለሁ። 10ከሰ​ዎች መካ​ከል “መል​እ​ክ​ቶቹ ከባ​ዶ​ችና አስ​ጨ​ና​ቂ​ዎች ናቸው፤ ሰው​ነቱ ግን ደካማ ነው፤ ነገ​ሩም ተርታ ነው” የሚሉ አሉና። 11ነገር ግን ይህን ነገር የሚ​ና​ገር ይህን ይወቅ፤ በሌ​ለ​ን​በት ጊዜ በመ​ል​እ​ክ​ታ​ችን እንደ ተገ​ለ​ጠው እንደ ቃላ​ችን፥ ባለ​ን​በ​ትም ጊዜ በሥ​ራ​ችን እን​ዲሁ ነን። 12እነ​ርሱ ራሳ​ቸ​ውን በአ​ሰ​ቡ​ትና በገ​መ​ገ​ሙት መጠን ራሳ​ቸ​ውን ከሚ​ያ​መ​ሰ​ግ​ኑት ሰዎች ጋር ራሳ​ች​ንን ልን​ቈ​ጥር፥ ወይም ራሳ​ች​ንን ልና​ስ​ተ​ያይ አን​ደ​ፍ​ርም፤ እነ​ርሱ ራሳ​ቸ​ውም የሚ​ና​ገ​ሩ​ትን ትር​ጕ​ሙን አያ​ው​ቁ​ትም። 13እኛስ ወደ እና​ንተ እስ​ክ​ን​ደ​ርስ ድረስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በወ​ሰ​ነ​ልን ሕግና ሥር​ዐት እንጂ፥ ከዐ​ቅ​ማ​ችን አል​ፈን እጅግ አን​መ​ካም። 14ወደ እና​ንተ እን​ደ​ማ​ን​ደ​ርስ አድ​ር​ገን፥ ራሳ​ች​ንን የም​ና​መ​ሰ​ግን አይ​ደ​ለ​ምና፤ ነገር ግን የክ​ር​ስ​ቶ​ስን ሕግ በማ​ስ​ተ​ማር ወደ እና​ንተ ደር​ሰ​ናል። 15እኛስ በማ​ይ​ገባ ሌላ በደ​ከ​መ​በት አን​መ​ካም፤ ነገር ግን ሃይ​ማ​ኖ​ታ​ችሁ እን​ድ​ት​ሰፋ፥ የተ​ሠ​ራ​ች​ላ​ችሁ ሕግም በእ​ና​ንተ እን​ድ​ት​ጸና ተስፋ እና​ደ​ር​ጋ​ለን። 16አብ​ዝ​ተ​ንም እና​ስ​ተ​ም​ራ​ች​ኋ​ለን፤ ያን​ጊ​ዜም መጠ​ና​ችን ከሥ​ራ​ችን ጋር ከፍ ከፍ ይላል፤ እኛስ ቀና ባል​ሆ​ነ​ውና በማ​ይ​ገ​ባው አን​መ​ካም። 17#ኤር. 9፥24። “የሚ​መካ ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመካ።” 18እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያከ​በ​ረው ብቻ ይከ​ብ​ራል እንጂ ራሱን የሚ​ያ​ከ​ብር የተ​መ​ረጠ አይ​ደ​ለም።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ