የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ዜና መዋ​ዕል ካልእ 24

24
የኢ​ዮ​አስ ዘመነ መን​ግ​ሥት
(2ነገ. 12፥1-16)
1ኢዮ​አ​ስም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የሰ​ባት ዓመት ልጅ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም አርባ ዓመት ነገሠ፤ እናቱ ሳብያ የተ​ባ​ለች የቤ​ር​ሳ​ቤህ ሴት ነበ​ረች። 2ኢዮ​አ​ስም በካ​ህኑ በኢ​ዮ​አዳ ዘመን ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቅን ነገ​ርን አደ​ረገ። 3ኢዮ​አ​ዳም ሁለት ሚስ​ቶ​ችን አጋ​ባው፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ች​ንም ወለደ።
4ከዚ​ህም በኋላ ኢዮ​አስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ይጠ​ግን ዘንድ አሰበ። 5ካህ​ና​ት​ንና ሌዋ​ው​ያ​ን​ንም ሰብ​ስቦ፥ “ወደ ይሁዳ ከተ​ሞች ውጡ፤ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁ​ንም ቤት በየ​ዓ​መቱ ለማ​ደስ የሚ​በቃ ከእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ገን​ዘ​ብን ሰብ​ስቡ፤ ነገ​ሩ​ንም ፈጥ​ና​ችሁ አድ​ርጉ” አላ​ቸው። ሌዋ​ው​ያን ግን አላ​ፋ​ጠ​ኑም። 6ንጉሡ ኢዮ​አ​ስም አለ​ቃ​ውን ኢዮ​አ​ዳን ጠርቶ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባሪያ ሙሴ እስ​ራ​ኤ​ልን በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን በሰ​በ​ሰበ ጊዜ እን​ዲ​ያ​ዋጣ ያዘ​ዘ​ውን ግብር ከይ​ሁ​ዳና ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያመጡ ዘንድ ስለ ምን ሌዋ​ው​ያ​ንን አል​ተ​ከ​ታ​ተ​ል​ህም?” አለው። 7ጎቶ​ልያ ከሐ​ዲት ነበ​ረ​ችና ልጆ​ች​ዋም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት አፍ​ር​ሰ​ዋ​ልና፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ተቀ​ድሶ የነ​በ​ረ​ውን ሁሉ ለበ​ኣ​ሊም ሰጥ​ተ​ዋ​ልና።
8ንጉ​ሡም ሣጥን ሠር​ተው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በር አጠ​ገብ በስ​ተ​ውጭ ያኖ​ሩት ዘንድ አዘዘ። 9የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ባሪያ ሙሴ በም​ድረ በዳ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ያዘ​ዘ​ውን ግብር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያመጡ ዘንድ፥ በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያስ​ተ​ምሩ ዘንድ አዘዘ። 10አለ​ቆ​ቹና ሕዝ​ቡም ሁሉ ሰጡ፤ እስ​ኪ​ሞ​ላም ድረስ በሣ​ጥኑ ውስጥ አስ​ገ​ቡት። 11ሣጥ​ኑም በሌ​ዋ​ው​ያን እጅ ወደ ንጉሡ ሹሞች በደ​ረሰ ጊዜ፥ ብዙ ገን​ዘ​ብም እን​ዳ​ለ​በት ባዩ ጊዜ፥ የን​ጉሡ ጸሓ​ፊና የሊቀ ካህ​ናቱ ሹም እየ​መጡ ብሩን ከሣ​ጥን ያወጡ ነበር፤ ሣጥ​ኑ​ንም ደግሞ ወደ ስፍ​ራው ይመ​ል​ሱት ነበር። እን​ዲ​ሁም በየ​ቀኑ ያደ​ርጉ ነበር፤ ብዙም ገን​ዘብ ሰበ​ሰቡ። 12ንጉ​ሡና ኢዮ​አ​ዳም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ሥራ ላይ ለተ​ሾ​ሙት ሰጡ​አ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት የሚ​ጠ​ግ​ኑ​ትን ጠራ​ቢ​ዎ​ች​ንና አና​ጢ​ዎ​ችን፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት የሚ​ያ​ድ​ሱ​ትን የብ​ረ​ትና የናስ ሠራ​ተ​ኞ​ችን ይቀ​ጥ​ሩ​በት ነበር። 13ሠራ​ተ​ኞ​ችም ሠሩ፤ ሥራ​ውም ሁሉ በእ​ጃ​ቸው ተፈ​ጸመ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት እንደ ቀድ​ሞው ሥራ መለሱ፤ አጽ​ን​ተ​ውም አቆ​ሙት። 14በጨ​ረ​ሱም ጊዜ የተ​ረ​ፈ​ውን ገን​ዘብ ወደ ንጉ​ሡና ወደ ካህኑ ኢዮ​አዳ ፊት አመጡ፤ እነ​ር​ሱም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ዕቃ፥ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎ​ትና ለቍ​ር​ባን ዕቃ፥ ለጭ​ል​ፋ​ዎ​ችም፥ ለወ​ር​ቅና ለብ​ርም ዕቃ አደ​ረ​ጉት። በኢ​ዮ​አ​ዳም ዘመን ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ሁል​ጊዜ ያቀ​ርቡ ነበር።
15ኢዮ​አ​ዳም ሸመ​ገለ፤ ዕድ​ሜም ጠግቦ ሞተ፤ በሞ​ተም ጊዜ ዕድ​ሜው መቶ ሠላሳ ዓመት ነበረ። 16ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ጋር፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና ከቤ​ቱም ጋር መል​ካም ሠር​ቶ​አ​ልና በዳ​ዊት ከተማ ከነ​ገ​ሥ​ታቱ ጋር ቀበ​ሩት። 17ካህኑ ኢዮ​አ​ዳም ከሞተ በኋላ የይ​ሁዳ አለ​ቆች ገብ​ተው ለን​ጉሡ ሰገዱ፤ ንጉ​ሡም ሰማ​ቸው። 18የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም አም​ላክ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ትተው ባዕድ አም​ላ​ክ​ንና#ዕብ. “የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዶ​ችን” ይላል። ጣዖ​ታ​ትን አመ​ለኩ፤ በዚ​ያም ወራት#ዕብ. “በዚህ በደ​ላ​ቸ​ውም ምክ​ን​ያት” ይላል። በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ ቍጣ ወረደ። 19ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይመ​ል​ሱ​አ​ቸው ዘንድ ነቢ​ያ​ትን ይሰ​ድ​ድ​ላ​ቸው ነበር፤ መሰ​ከ​ሩ​ባ​ቸ​ውም፤ እነ​ርሱ ግን አላ​ደ​መ​ጡም።
20የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በካ​ህኑ በኢ​ዮ​አዳ ልጅ በአ​ዛ​ር​ያስ#ዕብ. “ዘካ​ር​ያስ” ይላል። ላይ መጣ፤ እር​ሱም በሕ​ዝቡ ፊት ቆመና፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ለምን ትተ​ላ​ለ​ፋ​ላ​ችሁ? መል​ካ​ምም አይ​ሆ​ን​ላ​ች​ሁም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ ተዋ​ችሁ እርሱ ትቶ​አ​ች​ኋል” አላ​ቸው። 21ወደ እር​ሱም ሮጡ#ዕብ. እና ግሪክ “ተማ​ማ​ሉ​በት” ይላል። በን​ጉ​ሡም ትእ​ዛዝ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አደ​ባ​ባይ ውስጥ በድ​ን​ጋይ ደበ​ደ​ቡት። 22እን​ዲ​ሁም ንጉሡ ኢዮ​አስ አባቱ ኢዮ​አዳ ያደ​ረ​ገ​ለ​ትን ቸር​ነት አላ​ሰ​በም፤ ልጁ​ንም አዛ​ር​ያ​ስን አስ​ገ​ደ​ለው፤ እር​ሱም ሲሞት፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይየው፤ ይፍ​ረ​ደ​ውም” አለ።
23ዓመ​ቱም ካለፈ በኋላ የሶ​ር​ያ​ው​ያን ሠራ​ዊት መጡ​በት፤ ወደ ይሁ​ዳና ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም መጥ​ተው ከሕ​ዝቡ መካ​ከል የሕ​ዝ​ቡን አለ​ቆች ሁሉ አጠፉ፤ ምር​ኮ​አ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ለደ​ማ​ስቆ ንጉሥ ላኩ። 24የሶ​ር​ያ​ው​ያ​ንም ሠራ​ዊት ቍጥር ጥቂት ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ብዙ​ው​ንና ጠን​ካ​ራ​ውን ሠራ​ዊት አሳ​ልፎ በእ​ጃ​ቸው ሰጣ​ቸው፤ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ዘን​ግ​ተ​ዋ​ልና። በኢ​ዮ​አ​ስም ላይ ፈረ​ደ​በት።
25ከእ​ር​ሱም ዘንድ አል​ፈው ከሄዱ በኋላ እጅግ ታሞ ሳለ ተዉት፤ የገዛ ባሪ​ያ​ዎ​ቹም ስለ ካህኑ ስለ ኢዮ​አዳ ልጅ ደም ተበ​ቅ​ለው በአ​ል​ጋው ላይ ገደ​ሉት፤ ሞተም፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ቀበ​ሩት፤ ነገር ግን በነ​ገ​ሥ​ታት መቃ​ብር አል​ቀ​በ​ሩ​ትም። 26የገ​ደ​ሉ​ትም#ዕብ. “የተ​ማ​ማ​ሉ​በት” ይላል። የአ​ሞ​ና​ዊቱ የሰ​ማት ልጅ ዘቡድ፥ የሞ​ዓ​ባ​ዊ​ቱም የሰ​ማ​ሪት ልጅ ኢዮ​ዛ​ብድ ነበሩ። 27የል​ጆ​ቹና በእ​ርሱ ላይ የተ​ደ​ረ​ገው ነገር፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት ማደሱ፥ እነሆ በነ​ገ​ሥ​ታቱ የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ ተጽ​ፎ​አል። ልጁም አሜ​ስ​ያስ በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ