መጽ​ሐፈ ዜና መዋ​ዕል ካልእ 22

22
የአ​ካ​ዝ​ያስ ዘመነ መን​ግ​ሥት
(2ነገ. 8፥25-299፥21-28)
1በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የነ​በ​ሩት ታና​ሹን ልጁን አካ​ዝ​ያ​ስን በእ​ርሱ ፋንታ አነ​ገ​ሡት። የመ​ጣ​ባ​ቸው የዓ​ረ​ብና የአ​ሊ​ማ​ዞን የሽ​ፍ​ቶች ጭፍራ የእ​ር​ሱን ታላ​ቆች ወን​ድ​ሞች ገድ​ለ​ዋ​ቸው ነበ​ርና የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​ራም ልጅ አካ​ዝ​ያስ ነገሠ። 2አካ​ዝ​ያ​ስም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ ዕድ​ሜው ሃያ ሁለት ዓመት#ዕብ. “አርባ ሁለት ዓመት” ይላል። ነበረ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም አንድ ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም ጎቶ​ልያ የተ​ባ​ለች የዘ​ን​በሪ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “አም​ብሪ” ይላል። ልጅ ነበ​ረች። 3እና​ቱም ክፉ እን​ዲ​ያ​ደ​ርግ ትመ​ክ​ረው ነበ​ርና እርሱ ደግሞ በአ​ክ​ዓብ ቤት መን​ገድ ሄደ። 4ከአ​ባ​ቱም ሞት በኋላ የአ​ክ​ዓብ ቤት እን​ዳ​ደ​ረገ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አደ​ረገ፤ ያጠ​ፉት ዘንድ መካ​ሪ​ዎች ነበ​ሩ​ትና። 5በም​ክ​ራ​ቸ​ውም ሄደ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ከአ​ክ​ዓብ ልጅ ከኢ​ዮ​ራም ጋር የሶ​ር​ያን ንጉሥ አዛ​ሄ​ልን በሬ​ማት ዘገ​ለ​ዓድ ሊዋጋ ሄደ፤ ሶር​ያ​ው​ያ​ንም ኢዮ​ራ​ምን አቈ​ሰ​ሉት። 6ከሶ​ር​ያም ንጉሥ ከአ​ዛ​ሄል ጋር በተ​ዋጋ ጊዜ ሶር​ያ​ው​ያን በሬ​ማት#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “በራማ” ይላል ያቈ​ሰ​ሉ​ትን ቍስል ይታ​ከም ዘንድ ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ተመ​ለሰ፤ ታም​ሞም ነበ​ርና የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​ራም ልጅ አካ​ዝ​ያስ የአ​ክ​ዓ​ብን ልጅ ኢዮ​ራ​ምን ያይ ዘንድ ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ወረደ።
7ወደ ኢዮ​ራም በመ​ም​ጣ​ቱም የአ​ካ​ዝ​ያስ ጥፋት ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆነ፤ በመ​ጣም ጊዜ ከኢ​ዮ​ራም ጋር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ክ​ዓ​ብን ቤት ያጠፋ ዘንድ ወደ ቀባው ወደ ናሚሲ ልጅ ወደ ኢዩ ወጣ። 8ኢዩም የአ​ክ​ዓ​ብን ቤት ይበ​ቀል ዘንድ#ዕብ. “በአ​ክ​ዓብ ቤት ላይ ፍር​ድን ሲፈ​ጽም” ይላል። የይ​ሁ​ዳን መሳ​ፍ​ን​ትና አካ​ዝ​ያ​ስን ያገ​ለ​ግሉ የነ​በ​ሩ​ትን የአ​ካ​ዝ​ያ​ስን ወን​ድ​ሞች#ዕብ. “ወን​ድ​ሞች ልጆች” ይላል። አግ​ኝቶ ገደ​ላ​ቸው። 9አካ​ዝ​ያ​ስ​ንም ፈለ​ገው፤ በሰ​ማ​ር​ያም እየ​ታ​ከመ ሳለ አገ​ኙት፤ ወደ ኢዩም አመ​ጡት፤ እር​ሱም ገደ​ለው፦ እነ​ር​ሱም፥ “በፍ​ጹም ልብ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የፈ​ለ​ገው የኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ ልጅ ነው” ብለው ቀበ​ሩት። ከአ​ካ​ዝ​ያ​ስም ቤት ማንም መን​ግ​ሥ​ትን ይይዝ ዘንድ የሚ​ችል አል​ነ​በ​ረም።
የአ​ካ​ዝ​ያስ እናት ጎቶ​ልያ
(2ነገ. 11፥1-3)
10የአ​ካ​ዝ​ያ​ስም እናት ጎቶ​ልያ ልጅዋ እንደ ሞተ ባየች ጊዜ ተነ​ሥታ የይ​ሁ​ዳን ቤተ መን​ግ​ሥት ዘር ሁሉ አጠ​ፋች። 11የን​ጉሡ ልጅ ዮሳ​ቤት ግን ከተ​ገ​ደ​ሉት ከን​ጉሡ ልጆች መካ​ከል የአ​ካ​ዝ​ያ​ስን ልጅ ኢዮ​አ​ስን ሰርቃ ወሰ​ደች፤ እር​ሱ​ንና ሞግ​ዚ​ቱን በእ​ል​ፍኝ ውስጥ አኖ​ረ​ቻ​ቸው፤ የን​ጉሡ የኢ​ዮ​ራም ልጅ የአ​ካ​ዝ​ያስ እኅት የካ​ህኑ የዮ​ዳሄ ሚስት ዮሳ​ቤት ከጎ​ቶ​ልያ ፊት ሸሸ​ገ​ችው፤ እር​ስ​ዋም አል​ገ​ደ​ለ​ች​ውም። 12ከእ​ር​ስ​ዋም ጋር#ዕብ. “በእ​ነ​ር​ሱም ዘንድ” ይላል። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ተሸ​ሽጎ ስድ​ስት ዓመት ያህል ተቀ​መጠ፤ ጎቶ​ል​ያም በም​ድር ላይ ነገ​ሠች።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ