የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ዜና መዋ​ዕል ካልእ 20:15-22

መጽ​ሐፈ ዜና መዋ​ዕል ካልእ 20:15-22 አማ2000

እን​ዲ​ህም አለ፥ “ይሁዳ ሁሉ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የም​ት​ኖሩ፥ አን​ተም ንጉሡ ኢዮ​ሣ​ፍጥ! ስሙ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ች​ኋል፦ ሰልፉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው እንጂ የእ​ና​ንተ አይ​ደ​ለ​ምና ከዚህ ታላቅ ወገን የተ​ነሣ አት​ፍሩ፤ አት​ደ​ን​ግ​ጡም። ነገ በእ​ነ​ርሱ ላይ ውረዱ፤ እነሆ፥ በአ​ሲስ ዐቀ​በት ይወ​ጣሉ፤ በሸ​ለ​ቆ​ውም መጨ​ረሻ በኢ​ያ​ር​ሔል ምድረ በዳ ፊት ለፊት ታገ​ኙ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ። እና​ንተ የም​ቷጉ አይ​ደ​ላ​ች​ሁም፤ ይሁ​ዳና ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ ተሰ​ለፉ፤ ዝም ብላ​ችሁ ቁሙ፤ የሚ​ሆ​ነ​ው​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማዳን እዩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ና​ንተ ጋር ነውና አት​ፍሩ፤ አት​ደ​ን​ግ​ጡም፤ ነገም ውጡ​ባ​ቸው።” ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም በም​ድር ላይ ሰገደ፤ ይሁ​ዳም ሁሉ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የሚ​ኖሩ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ወደቁ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰገዱ። ሌዋ​ው​ያ​ንም፥ ከቀ​ዓት ልጆ​ችና ከቆሬ ልጆች የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከፍ ባለ ታላቅ ድምፅ ያመ​ሰ​ግኑ ዘንድ ቆሙ። ማል​ደ​ውም ተነሡ፤ ወደ ቴቁ​ሔም ምድረ በዳ ወጡ፤ ሲወ​ጡም ኢዮ​ሣ​ፍጥ ቆመና፥ “ይሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የም​ት​ኖሩ ሆይ፥ ስሙኝ፤ በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እመኑ፥ ትጸ​ኑ​ማ​ላ​ችሁ፤ በነ​ቢ​ዩም እመኑ፤ ነገ​ሩም ይቀ​ና​ላ​ች​ኋል” አለ። ከሕ​ዝ​ቡም ጋር ተማ​ክሮ በሠ​ራ​ዊቱ ፊት የሚ​ሄ​ዱ​ትን፥ “ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ” የሚ​ሉ​ት​ንም፥ በቅ​ድ​ስና የሚ​ያ​መ​ሰ​ግ​ኑ​ትን፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ዘ​ም​ሩ​ትን መዘ​ም​ራን አቆመ። ዝማ​ሬ​ው​ንና ምስ​ጋ​ና​ው​ንም በጀ​መሩ ጊዜ ይሁ​ዳን ሊወጉ በመ​ጡት በአ​ሞ​ንና በሞ​ዓብ ልጆች በሴ​ይ​ርም ተራራ ሰዎች ላይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይ​ልን ሰጣ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ተመቱ።