መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልእ 19
19
ነቢዩ ኢዩ የይሁዳን ንጉሥ ኢዮሣፍጥን እንደ ገሠጸው
1የይሁዳም ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ወደ ቤቱ ወደ ኢየሩሳሌም በሰላም ተመለሰ። 2ነቢዩ የአናኒ ልጅ ኢዩ ሊገናኘው ወጣ፤ ንጉሡንም ኢዮሣፍጥን፥ “ኀጢአተኛውን ታግዛለህን? ወይስ እግዚአብሔር የሚጠላውን ትወድዳለህን? ስለዚህም ነገር ከእግዚአብሔር ዘንድ ቍጣ መጥቶብሃል። 3ነገር ግን የማምለኪያ ዐፀዶችን ከምድረ ይሁዳ አስወግደሃልና፥ እግዚአብሔርንም ትፈልግ ዘንድ ልብህን አዘጋጅተሃልና መልካም ነገር ተገኝቶብሃል” አለው።
4ኢዮሣፍጥም በኢየሩሳሌም ተቀመጠ፤ ደግሞም ከቤርሳቤህ ጀምሮ እስከ ተራራማው እስከ ኤፍሬም ሀገር ድረስ ወደ ሕዝቡ ወጥቶ ወደ አባቶቻቸው አምላክ ወደ እግዚአብሔር መለሳቸው። 5በተመሸጉት በይሁዳ ከተሞች ሁሉ በእያንዳንዱ ከተማ ውስጥ ፈራጆችን ሾመ። 6ፈራጆቹንም፥ “ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው አትፈርዱምና፥ የፍርድም ነገር ከእናንተ ጋር#ዕብ. “እርሱ በፍርድ ነገር ከእናንተ ጋር ነውና” ይላል። ነውና የምታደርጉትን ተመልከቱ። 7አሁንም እግዚአብሔርን መፍራት በእናንተ ላይ ይሁን፤ በአምላካችንም በእግዚአብሔር ዘንድ በደልና ለሰው ፊት ማድላት፥ መማለጃም መውሰድ የለምና ሁሉን ተጠንቅቃችሁ አድርጉ” አላቸው።
8ኢዮሣፍጥም ከሌዋውያንና ከካህናት፥ ከእስራኤልም የአባቶች ቤቶች አለቆች በእግዚአብሔር ፍርድ በኢየሩሳሌም በሚኖሩ ላይ#ዕብ. “ፍርድን እንዲፈርዱ፥ ክርክርን እንዲቈርጡ በኢየሩሳሌም ሾመ ፤ እነርሱም በኢየሩሳሌም ተቀመጡ” ይላል። ፍርድን እንዲፈርዱ በኢየሩሳሌም ሾመ። 9እንዲህም ብሎ አዘዛቸው፥ “እንዲሁ እግዚአብሔርን በመፍራት፥ በቅንነትም፥ በፍጹምም ልብ አድርጉ።” 10በከተሞቻቸውም ከተቀመጡት ከወንድሞቻችሁ በደምና በደም መካከል፥ በሕግና በትእዛዝ፥ በሥርዐትና በፍርድም መካከል ያለ ማናቸውም ሰው ለፍርድ ወደ እናንተ ቢመጣ እግዚአብሔርን እንዳይበድሉ፥ ቍጣም በእናንተና በወንድሞቻችሁ ላይ እንዳይመጣ አስጠንቅቁአቸው፤ እንዲህም ብታደርጉ በደለኞች አትሆኑም። 11እነሆም፥ ለእግዚአብሔር በሚሆነው ነገር ሁሉ የካህናቱ አለቃ አማርያ፥ በንጉሡም ነገር ሁሉ የይሁዳ ቤት አለቃ የይስማኤል ልጅ ዝባድያስ በላያችሁ ተሾመዋል፤ ጸሐፍቱና ሌዋውያኑ ደግሞ በፊታችሁ አሉ፤ በርትታችሁም አድርጉ፤ እግዚአብሔር መልካም ከሚያደርግ ጋር ይሁን።
Currently Selected:
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልእ 19: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ