መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ቀዳ​ማዊ 17:32-37

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ቀዳ​ማዊ 17:32-37 አማ2000

ዳዊ​ትም ሳኦ​ልን፥ “ስለ እርሱ የማ​ንም ልብ አይ​ው​ደቅ፤ እኔ ባሪ​ያህ ሄጄ ያን ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማዊ እወ​ጋ​ዋ​ለሁ” አለው። ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን፥ “አንተ ገና ብላ​ቴና ነህና፥ እር​ሱም ከብ​ላ​ቴ​ን​ነቱ ጀምሮ ጦረኛ ነውና ይህን ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማዊ ለመ​ው​ጋት ትሄድ ዘንድ አት​ች​ልም” አለው። ዳዊ​ትም ሳኦ​ልን አለው፥ “እኔ ባሪ​ያህ የአ​ባ​ቴን በጎች ስጠ​ብቅ አን​በሳ ወይም ድብ ይመጣ ነበር፤ ከመ​ን​ጋ​ውም ጠቦት ይወ​ስድ ነበር። በኋ​ላ​ውም እከ​ተ​ለ​ውና እመ​ታው ነበር። ከአ​ፉም አስ​ጥ​ለው ነበር፤ በተ​ነ​ሣ​ብ​ኝም ጊዜ ጕሮ​ሮ​ውን አንቄ እመ​ታ​ውና እገ​ድ​ለው ነበር። እኔ ባሪ​ያህ አን​በ​ሳና ድብ ገደ​ልሁ፤ ይህም ያል​ተ​ገ​ረ​ዘው ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማዊ ከእ​ነ​ርሱ እንደ አንዱ ይሆ​ናል። እን​ግ​ዲህ እገ​ድ​ለው ዘንድ፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ተግ​ዳ​ሮ​ትን አስ​ወ​ግድ ዘንድ ዛሬ አል​ሄ​ድ​ምን? የሕ​ያው አም​ላክ ጭፍ​ሮ​ችን ይገ​ዳ​ደር ዘንድ ይህ ቈላፍ ምን​ድን ነው?” ዳዊ​ትም፥ “ከአ​ን​በ​ሳና ከድብ እጅ ያስ​ጣ​ለኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዚህ ያል​ተ​ገ​ረዘ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማዊ እጅ ያስ​ጥ​ለ​ኛል” አለ። ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን፥ “ሂድ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከአ​ንተ ጋር ይሁን” አለው።