መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ቀዳ​ማዊ 7:38-51

መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ቀዳ​ማዊ 7:38-51 አማ2000

ዐሥ​ሩ​ንም የናስ መታ​ጠ​ቢያ ሰን ሠራ፤ አንዱ መታ​ጠ​ቢያ ሰን አርባ የባ​ዶስ መስ​ፈ​ሪያ ያነሣ ነበር፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም መታ​ጠ​ቢያ ሰን አራት ክንድ ነበረ፤ በዐ​ሥ​ሩም መቀ​መ​ጫ​ዎች ላይ በእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ አንድ አንድ መታ​ጠ​ቢያ ሰን ይቀ​መጥ ነበር። አም​ስ​ቱ​ንም መቀ​መ​ጫ​ዎች በቤቱ ቀኝ፥ አም​ስ​ቱ​ንም በቤቱ ግራ አኖ​ራ​ቸው፤ ኩሬ​ው​ንም በቤቱ ቀኝ በአ​ዜብ ፊት ለፊት በስ​ተ​ም​ሥ​ራቅ አኖ​ረው። ኪራ​ምም ምን​ቸ​ቶ​ች​ንና መጫ​ሪ​ያ​ዎ​ችን፥ ድስ​ቶ​ች​ንም ሠራ፤ ኪራ​ምም ለን​ጉሡ ለሰ​ሎ​ሞን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የሠ​ራ​ውን ሥራ ሁሉ ጨረሰ። ሁለ​ቱ​ንም አዕ​ማድ፥ በሁ​ለ​ቱም አዕ​ማድ ራስ ላይ የነ​በ​ሩ​ትን ኩብ የሚ​መ​ስ​ሉ​ትን ጕል​ላ​ቶች፥ በሁ​ለ​ቱም አዕ​ማድ ላይ የነ​በ​ሩ​ትን ሁለ​ቱን ጕል​ላ​ቶች የሚ​ሸ​ፍ​ኑ​ትን ሁለ​ቱን መር​በ​ቦች፥ በሁ​ለ​ቱም አዕ​ማድ ላይ የነ​በ​ሩ​ትን ሁለ​ቱን ጕል​ላ​ቶች ይሸ​ፍኑ ዘንድ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ መር​በብ በሁ​ለት በሁ​ለት ተራ አድ​ርጎ ለሁ​ለቱ መር​በ​ቦች አራት መቶ ሮማ​ኖ​ችን አደ​ረገ። ዐሥ​ሩ​ንም መቀ​መ​ጫ​ዎች፥ በመ​ቀ​መ​ጫ​ዎ​ቹም ላይ የሚ​ቀ​መ​ጡ​ትን ዐሥ​ሩን መታ​ጠ​ቢያ ሰን፥ አን​ዱ​ንም ኩሬ፥ ከኩ​ሬ​ውም በታች የሚ​ሆ​ኑ​ትን ዐሥራ ሁለ​ቱን በሬ​ዎች፥ ምን​ቸ​ቶ​ቹ​ንም፥ መጫ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም፥ ድስ​ቶ​ቹ​ንም፥ ዕቃ​ዎ​ቹ​ንም ሁሉ ኪራም ለን​ጉሡ ለሰ​ሎ​ሞን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ሠራ። በን​ጉሡ ቤትና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤትም አርባ ስም​ንት አዕ​ማድ ነበሩ። ኪራ​ምም ለን​ጉሡ የሠ​ራ​ቸው ዕቃ​ዎች ሁሉ ከጥሩ ናስ ነበር። በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ሜዳ በሱ​ኮ​ትና በተ​ር​ታን መካ​ከል ባለው በወ​ፍ​ራሙ መሬት ውስጥ አስ​ፈ​ሰ​ሰው። ይህ ሁሉ ሥራ ለተ​ሠ​ራ​በት ናስ ሚዛን አል​ነ​በ​ረ​ውም፤ የና​ሱም ሚዛን ብዙ ነበ​ርና አይ​ቈ​ጠ​ርም ነበር። ሰሎ​ሞ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ዕቃን ሁሉ አሠራ፤ የወ​ር​ቁን መሠ​ዊያ፥ የገ​ጹም ኅብ​ስት የነ​በ​ረ​በ​ትን የወ​ርቅ ገበታ፥ በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳኑ ፊት አም​ስቱ በቀኝ፥ አም​ስ​ቱም በግራ የሚ​ቀ​መ​ጡ​ትን ከጥሩ ወርቅ የተ​ሠ​ሩ​ት​ንም መቅ​ረ​ዞች፥ የወ​ር​ቁ​ንም አበ​ባ​ዎ​ችና ቀን​ዲ​ሎች፥ መኮ​ስ​ተ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ንም፥ ከጥሩ ወር​ቅም የተ​ሠ​ሩ​ትን ጽዋ​ዎ​ችና ጕጠ​ቶች፥ ድስ​ቶ​ቹ​ንና ጭል​ፋ​ዎ​ቹ​ንም፥ ማን​ደ​ጃ​ዎ​ቹ​ንም፥ ጽን​ሐ​ሖ​ችን፥ ለው​ስ​ጠ​ኛ​ውም ቤት ለቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳን ደጆች፥ ለቤተ መቅ​ደ​ሱም ደጆች የሚ​ሆ​ኑ​ትን የወ​ርቅ ማጠ​ፊ​ያ​ዎች አሠራ። እን​ዲ​ሁም ንጉሡ ሰሎ​ሞን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የአ​ሠ​ራው ሥራ ሁሉ ተፈ​ጸመ። አባ​ቱም ዳዊት የቀ​ደ​ሰ​ውን፥ ራሱም የቀ​ደ​ሰ​ውን፥ የብ​ርና የወ​ርቅ ዕቃ ሰሎ​ሞን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ውስጥ በነ​በሩ ግምጃ ቤቶች አገባ።