መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ቀዳ​ማዊ 18

18
ኤል​ያ​ስና ነቢ​ያተ ሐሰት
1ከብዙ ቀንም በኋላ በሦ​ስ​ተ​ኛው ዓመት፥ “ሂድ ለአ​ክ​ዓብ ተገ​ለጥ፤ በም​ድር ላይም ዝናም እሰ​ጣ​ለሁ” የሚል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ ኤል​ያስ መጣ። 2ኤል​ያ​ስም ለአ​ክ​ዓብ ይገ​ለጥ ዘንድ ሄደ፤ በሰ​ማ​ር​ያም ራብ ጸንቶ ነበር። 3አክ​ዓ​ብም የቤ​ቱን አዛዢ አብ​ድ​ዩን ጠራ፤ አብ​ድ​ዩም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እጅግ ይፈራ ነበር። 4ኤል​ዛ​ቤ​ልም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ነቢ​ያት ባስ​ገ​ደ​ለች ጊዜ አብ​ድዩ መቶ​ውን ነቢ​ያት ወስዶ አምሳ አም​ሳ​ውን በዋሻ ውስጥ ሸሽጎ እን​ጀ​ራና ውኃ ይመ​ግ​ባ​ቸው ነበር። 5አክ​ዓ​ብም አብ​ድ​ዩን፥ “በሀ​ገሩ መካ​ከል ወደ ውኃ ምንጭ ሁሉና ወደ ፈፋ ሁሉ ና እን​ሂድ፤ እን​ስ​ሶ​ችም ሁሉ እን​ዳ​ይ​ጠፉ ፈረ​ሶ​ች​ንና በቅ​ሎ​ችን የም​ና​ድ​ን​በት ሣር ምና​ል​ባት እና​ገኝ እንደ ሆነ” አለው። 6በመ​ን​ገ​ድም ተለ​ያ​ይ​ተው ሄዱ፤ አክ​ዓ​ብም ለብ​ቻው በአ​ንድ መን​ገድ፥ አብ​ድ​ዩም ለብ​ቻው በሌላ መን​ገድ ሄዱ።
7አብ​ድ​ዩም በመ​ን​ገድ ብቻ​ውን ሳለ እነሆ፥ ኤል​ያስ ሊገ​ና​ኘው ብቻ​ውን መጣ፤ አብ​ድ​ዩም ሮጠና፥ በግ​ን​ባሩ ወድቆ ሰገ​ደ​ለት፥ “ጌታዬ ሆይ፥ ኤል​ያስ አንተ ነህን?” አለው። 8ኤል​ያ​ስም፥ “አዎ እኔ ነኝ ሄደህ ለጌ​ታህ፦ እነሆ፥ ኤል​ያስ በዚህ አለ በል” አለው። 9አብ​ድ​ዩም አለ፥ “እኔን አገ​ል​ጋ​ይ​ህን እን​ዲ​ገ​ድ​ለኝ በአ​ክ​ዓብ እጅ አሳ​ል​ፈህ ትሰ​ጠኝ ዘንድ ምን በደ​ልሁ? 10አም​ላ​ክህ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ጌታዬ፥ ይፈ​ል​ግህ ዘንድ ያል​ላ​ከ​በት ሕዝብ ወይም መን​ግ​ሥት የለም፤ ሁሉም፦ በዚህ የለም ባሉ ጊዜ አን​ተን እን​ዳ​ላ​ገኙ መን​ግ​ሥ​ቱ​ንና ሕዝ​ቡን አም​ሎ​አ​ቸው ነበር።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “መን​ግ​ሥ​ቱ​ንና ሀገ​ሮ​ች​ዋን አቃ​ጠለ” ይላል። 11አሁ​ንም፥ እነሆ፦ ሂድ፥ ኤል​ያስ አለ ብለህ ለጌ​ታህ ንገር ትለ​ኛ​ለህ። 12እኔም ከአ​ንተ ጥቂት ራቅ ስል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ አን​ሥቶ ወደ​ማ​ላ​ው​ቀው ስፍራ ይወ​ስ​ድ​ሃል፤ እኔም ገብቼ ለአ​ክ​ዓብ ስና​ገር፥ ባያ​ገ​ኝህ ይገ​ድ​ለ​ኛል፤ እኔም ባሪ​ያህ ከት​ን​ሽ​ነቴ ጀምሬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እፈራ ነበር። 13ኤል​ዛ​ቤል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ነቢ​ያት ባስ​ገ​ደ​ለች ጊዜ፥ መቶ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነቢ​ያት ወስጄ፥ አምሳ አም​ሳ​ውን በዋሻ ውስጥ ሸሽጌ፥ እን​ጀ​ራና ውኃ የመ​ገ​ብ​ኋ​ቸ​ውን፥ ይህን ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ነገር በውኑ አንተ ጌታዬ አል​ሰ​ማ​ህ​ምን? 14አሁ​ንም፦ ሄደህ ኤል​ያስ አለ ብለህ ለጌ​ታህ ንገር ትላ​ለህ፤ እር​ሱም ይገ​ድ​ለ​ኛል።” 15ኤል​ያ​ስም፥ “በፊቱ የቆ​ም​ሁት የሠ​ራ​ዊት ጌታ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! እኔ ዛሬ ለእ​ርሱ እገ​ለ​ጣ​ለሁ” አለው።
16አብ​ድ​ዩም ሄዶ አክ​ዓ​ብን ተገ​ና​ኘው፤ ነገ​ረ​ውም፤ አክ​ዓ​ብም ሮጦ ሄዶ ኤል​ያ​ስን ተገ​ና​ኘው። 17አክ​ዓ​ብም ኤል​ያ​ስን ባየው ጊዜ፥ አክ​ዓብ ኤል​ያ​ስን፥ “እስ​ራ​ኤ​ልን የም​ት​ገ​ለ​ባ​ብጥ አንተ ነህን?” አለው። 18ኤል​ያ​ስም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትታ​ችሁ በዓ​ሊ​ምን የተ​ከ​ተ​ላ​ችሁ፥ አን​ተና የአ​ባ​ትህ ቤት ናችሁ እንጂ እኔስ እስ​ራ​ኤ​ልን አል​ገ​ለ​ባ​ብ​ጥም። 19አሁ​ንም ወደ እስ​ራ​ኤል ሁሉ ልከህ፥ አራት መቶ ሃምሳ ነቢ​ያተ ሐሰ​ትን፥ አራት መቶ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀድ ነቢ​ያ​ትን ወደ እኔ ወደ ቀር​ሜ​ሎስ ተራራ ሰብ​ስብ” አለው።
20አክ​ዓ​ብም ወደ እስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ ልኮ ነቢ​ያ​ቱን ሁሉ ወደ ቀር​ሜ​ሎስ ተራራ ሰበ​ሰ​ባ​ቸው። 21ኤል​ያ​ስም ወደ ሕዝቡ ሁሉ ቀርቦ፥ “እስከ መቼ በሁ​ለት አሳብ ታነ​ክ​ሳ​ላ​ችሁ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ቢሆን እር​ሱን ተከ​ተሉ፤ በዓ​ልም አም​ላክ ቢሆን እር​ሱን ተከ​ተሉ” አለ። ሕዝ​ቡም አን​ዲት ቃል አል​መ​ለ​ሱ​ለ​ትም። 22ኤል​ያ​ስም ሕዝ​ቡን አለ፥ “ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነቢ​ያት አንድ እኔ ብቻ ቀር​ቻ​ለሁ፤ የበ​ዓል ነቢ​ያት ግን አራት መቶ ሃምሳ ሰዎች ናቸው። የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀድ#“የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀድ ካህ​ና​ትም አራት መቶ ናቸው” የሚ​ለው በዕብ. የለም። ነቢ​ያ​ትም አራት መቶ ናቸው። 23ሁለት ወይ​ፈ​ኖች ይሰ​ጡን፤ እነ​ር​ሱም አንድ ወይ​ፈን ይም​ረጡ፤ እየ​ብ​ል​ቱም ይቍ​ረ​ጡት፤ በእ​ን​ጨ​ትም ላይ ያኑ​ሩት፤ በበ​ታ​ቹም እሳት አይ​ጨ​ምሩ፤ እኔም ሁለ​ተ​ኛ​ውን ወይ​ፈን አዘ​ጋ​ጃ​ለሁ፤ በእ​ን​ጨ​ቱም ላይ አኖ​ረ​ዋ​ለሁ፤ በበ​ታ​ቹም እሳት አል​ጨ​ም​ርም። 24እና​ን​ተም የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን ስም ጥሩ፤ እኔም የፈ​ጣ​ሪ​ዬን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም እጠ​ራ​ለሁ፤ ሰም​ቶም በእ​ሳት የሚ​መ​ልስ አም​ላክ፥ እርሱ አም​ላክ ይሁን።” ሕዝ​ቡም ሁሉ፥ “ይህ ነገር መል​ካም ነው” ብለው መለሱ።
25ኤል​ያ​ስም የበ​ዓ​ልን ነቢ​ያት፥ “እና​ንተ ብዙ​ዎች ናች​ሁና አስ​ቀ​ድ​ማ​ችሁ አንድ ወይ​ፈን ምረ​ጡና አዘ​ጋጁ፤ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁ​ንም ስም ጥሩ፤ በበ​ታ​ቹም እሳት አት​ጨ​ምሩ” አላ​ቸው። 26የተ​ሰ​ጣ​ቸ​ውን ወይ​ፈ​ንም ወስ​ደው አዘ​ጋጁ፤ ከጥ​ዋ​ትም እስከ ቀትር ድረስ፥ “በዓል ሆይ፥ ስማን፥” እያሉ የበ​ዓ​ልን ስም ጠሩ። ድም​ፅም አል​ነ​በ​ረም፤ የሚ​መ​ል​ስም አል​ነ​በ​ረም፤ የሠ​ሩ​ት​ንም መሠ​ዊያ እያ​ነ​ከሱ ይዞሩ ነበር። 27በቀ​ት​ርም ጊዜ ቴስ​ብ​ያ​ዊው ኤል​ያስ፥ “አም​ላክ ነውና በታ​ላቅ ቃል ጩኹ፤ ምና​ል​ባት ይጫ​ወት ይሆ​ናል፥ ወይም አሳብ ይዞት ይሆ​ናል፥ ወይም ተኝቶ እንደ ሆነ መቀ​ስ​ቀስ ያስ​ፈ​ል​ገ​ዋል” እያለ ይዘ​ባ​በ​ት​ባ​ቸው ጀመር። 28በታ​ላ​ቅም ቃል ይጮኹ ጀመር፤ እንደ ልማ​ዳ​ቸ​ውም ደማ​ቸው እስ​ኪ​ፈ​ስስ ድረስ ገላ​ቸ​ውን በጦ​ርና በሰ​ይፍ ይብ​ዋ​ጭሩ ነበር። 29እስከ ሠር​ክም ድረስ ትን​ቢት ይና​ገሩ ነበር፤ ድም​ፅም አል​ነ​በ​ረም፤ የሚ​መ​ል​ስና የሚ​ያ​ደ​ም​ጥም አል​ነ​በ​ረም። ከዚ​ህም በኋላ መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ያ​ር​ግ​በት ጊዜ ኤል​ያስ ነቢ​ያተ ሐሰ​ትን፥ “እን​ግ​ዲ​ህስ ወዲያ በቃ​ችሁ፤ ወግዱ፤ ሂዱም፥ እኔም መሥ​ዋ​ዕ​ቴን እሠ​ዋ​ለሁ” አላ​ቸው።
ኤል​ያስ መሥ​ዋ​ዕት እንደ አቀ​ረ​በና ዝናብ እን​ዲ​ዘ​ንብ እንደ ጸለየ
30ኤል​ያ​ስም ሕዝ​ቡን ሁሉ፥ “ወደ እኔ ቅረቡ” አላ​ቸው። ሕዝ​ቡም ሁሉ ወደ እርሱ ቀረቡ። 31ኤል​ያ​ስም፦ ስምህ እስ​ራ​ኤል ይሆ​ናል የሚል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እንደ ደረ​ሰ​ለት እንደ እስ​ራ​ኤል ልጆች ነገድ ቍጥር ዐሥራ ሁለት ድን​ጋ​ዮ​ችን ወሰደ። 32ድን​ጋ​ዮ​ች​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም መሠ​ዊያ አድ​ርጎ ሠራ​ቸው፤ የፈ​ረ​ሰ​ው​ንም መሠ​ዊያ አደሰ፤ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ዙሪያ ሁለት መስ​ፈ​ሪያ እህል የሚ​ይዝ ጕድ​ጓድ ቈፈረ። 33በሠ​ራ​ውም መሠ​ዊያ ላይ እን​ጨ​ቱን ደረ​ደረ፤ ወይ​ፈ​ኑ​ንም በብ​ልት በብ​ልቱ ቈረጠ፤ በእ​ን​ጨ​ቱም ላይ አኖረ፤ 34“አራት ጋን ውኃ አም​ጡ​ልኝ፤ በሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ትና በእ​ን​ጨቱ ላይም አፍ​ስሱ” አለ፤ እነ​ር​ሱም እን​ዲሁ አደ​ረጉ። ደግ​ሞም፥ “ድገሙ” አለ፤ እነ​ር​ሱም ደገሙ። እር​ሱም፥ “ሦስ​ተኛ አድ​ርጉ” አለ፤ ሦስ​ተ​ኛም አደ​ረጉ። 35ውኃ​ውም በመ​ሠ​ዊ​ያው ዙሪያ ፈሰሰ። ደግ​ሞም ጕድ​ጓ​ዱን በውኃ ሞላው። 36ነቢዩ ኤል​ያ​ስም ወደ ሰማይ አቅ​ንቶ ጮኸ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “አቤቱ፥ የአ​ብ​ር​ሃ​ምና የይ​ስ​ሐቅ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ሆይ፥ ስማኝ፤ ጌታዬ ሆይ፥ ዛሬ በእ​ሳት ስማኝ፤ አንተ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አም​ላክ እንደ ሆንህ፥ እኔም ባሪ​ያህ እንደ ሆንሁ፤ ይህ​ንም ሥራ ስለ አንተ እን​ዳ​ደ​ረ​ግሁ እነ​ዚህ ሕዝ​ቦች ይወቁ። 37አንተ፥ አቤቱ፥ አም​ላክ እንደ ሆንህ፥ ልባ​ቸ​ው​ንም ደግሞ እንደ መለ​ስህ፤ ይህ ሕዝብ ያውቅ ዘንድ ስማኝ፤ አቤቱ፥ ስማኝ” አለ። 38እሳ​ትም ከሰ​ማይ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወረ​ደች፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ እን​ጨ​ቱ​ንም፥ ድን​ጋ​ዮ​ቹ​ንም በላች፤ በጕ​ድ​ጓ​ዱም ውስጥ ያለ​ውን ውኃ፥ አፈ​ሩ​ንም ላሰች። 39ሕዝ​ቡም ሁሉ ያን ባዩ ጊዜ በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ተደ​ፍ​ተው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ው​ነት እርሱ አም​ላክ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ አም​ላክ ነው” አሉ። 40ኤል​ያ​ስም ሕዝ​ቡን፥ “የበ​ዓ​ልን ነቢ​ያት ያዙ፤ ከእ​ነ​ርሱ አንድ ሰው እን​ኳን የሚ​ያ​መ​ልጥ አይ​ኑር፤” አላ​ቸው። ያዙ​አ​ቸ​ውም፤ ኤል​ያ​ስም ወደ ቂሶን ወንዝ ወስዶ፥ በዚያ እየ​ወጋ ጣላ​ቸው።
41ኤል​ያ​ስም አክ​ዓ​ብን፥ “የዝ​ናቡ ውሽ​ን​ፍር እጅግ ነውና ተነ​ሥ​ተህ ውጣ፤ ብላም፤ ጠጣም” አለው። 42አክ​ዓ​ብም ሊበ​ላና ሊጠጣ ወጣ። ኤል​ያ​ስም ወደ ቀር​ሜ​ሎስ አናት ወጣ፤ ፊቱ​ንም በጕ​ል​በቱ መካ​ከል አቀ​ር​ቅሮ በግ​ን​ባሩ ወደ ምድር ተደፋ። 43ብላ​ቴ​ና​ው​ንም፥ “ወጥ​ተህ ወደ ባሕሩ ተመ​ል​ከት” አለው። ብላ​ቴ​ና​ውም ተመ​ል​ክቶ፥ “ምንም የለም” አለ። ኤል​ያ​ስም፥ “ሰባት ጊዜ ተመ​ላ​ለስ” አለው። ብላ​ቴ​ና​ውም ሰባት ጊዜ ተመ​ላ​ለሰ። 44በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ጊዜ፥ “እነሆ፥ የሰው ጫማ የም​ታ​ህል ትንሽ ደመና ከባ​ሕር ውኃ ቋጥራ ስት​ወጣ አየሁ” አለ። እር​ሱም፥ “ወጥ​ተህ አክ​ዓ​ብን፦ ዝናብ እን​ዳ​ይ​ዝህ ሰረ​ገ​ላ​ህን ጭነህ ውረድ በለው” አለ። 45ወዲያ ወዲ​ህም እስ​ኪ​መ​ላ​ለስ ድረስ ሰማዩ በደ​መ​ናና በነ​ፋስ ጨለመ፤ ትል​ቅም ዝናብ ዘነበ፤ አክ​ዓ​ብም በሰ​ረ​ገላ ተቀ​ምጦ እያ​ለ​ቀሰ ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ሄደ። 46የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅ በኤ​ል​ያስ ላይ ነበ​ረች፤ ወገ​ቡ​ንም ታጥቆ ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል እስ​ኪ​ገባ ድረስ በአ​ክ​ዓብ ፊት ይሮጥ ነበር።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ