የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ቀዳ​ማዊ 19

19
1አክ​ዓ​ብም ኤል​ያስ ያደ​ረ​ገ​ውን፥ የሐ​ሰት ነቢ​ያ​ት​ንም ሁሉ በሰ​ይፍ እንደ ገደ​ላ​ቸው ለሚ​ስቱ ለኤ​ል​ዛ​ቤል ነገ​ራት። 2ኤል​ዛ​ቤ​ልም፥ “አንተ ኤል​ያስ ከሆ​ንህ እኔም ኤል​ዛ​ቤል ከሆ​ንሁ ነገ በዚህ ጊዜ ሰው​ነ​ት​ህን ከእ​ነ​ዚህ እንደ አንዱ ሰው​ነት ባላ​ደ​ር​ጋት፥ አማ​ል​ክት#ግሪክ ሰባ. ሊ. “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር” ይላል። እን​ዲህ ያድ​ር​ጉ​ብኝ፤ እን​ዲ​ህም ይግ​ደ​ሉኝ” ብላ ወደ ኤል​ያስ ላከች። 3ኤል​ያ​ስም ፈርቶ ተነሣ፤ ነፍ​ሱ​ንም ሊያ​ድን ሄደ፤ በይ​ሁ​ዳም ወዳ​ለው ወደ ቤር​ሳ​ቤህ መጥቶ ብላ​ቴ​ና​ውን በዚያ ተወ። 4እር​ሱም አንድ ቀን የሚ​ያ​ህል መን​ገድ በም​ድረ በዳ ሄደ፤ መጥ​ቶም ከደ​ድሆ ዛፍ በታች ተቀ​መ​ጠና፦ ይበ​ቃ​ኛል፤ አሁ​ንም አቤቱ! እኔ ከአ​ባ​ቶቼ አል​በ​ል​ጥ​ምና ነፍ​ሴን ውሰድ” ብሎ እን​ዲ​ሞት ለመነ። 5በደ​ድ​ሆ​ውም ዛፍ በታች ተኛ፤ እን​ቅ​ል​ፍም አን​ቀ​ላፋ፤ እነ​ሆም፥ መል​አክ ዳሰ​ሰ​ውና፥ “ተነ​ሥ​ተህ ብላ” አለው። 6ከዚህ በኋላ ኤል​ያስ ተነ​ሥቶ፥ እነሆ፥ በራሱ አጠ​ገብ የተ​ጋ​ገረ እን​ጎ​ቻና በማ​ሰሮ ውኃ አገኘ። በላም፤ ጠጣም፤ ተመ​ል​ሶም ተኛ። 7የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ ደግሞ ሁለ​ተኛ ጊዜ መጥቶ ዳሰ​ሰ​ውና፥ “የም​ት​ሄ​ድ​በት መን​ገድ ሩቅ ነውና ተነ​ሥ​ተህ ብላ” አለው። 8ተነ​ሥ​ቶም በላ፤ ጠጣም፤ በዚ​ያም በበ​ላው የም​ግብ ኀይል#ዕብ. “እስከ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተራራ” የሚል ይጨ​ም​ራል። እስከ ኮሬብ ድረስ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ሄደ።
9እዚ​ያም ወዳለ ዋሻ ገባ፤ በዚ​ያም አደረ፤ እነ​ሆም፥ “ኤል​ያስ ሆይ! ምን አመ​ጣህ?” የሚል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እርሱ መጣ። 10ኤል​ያ​ስም፥ “ሁሉን ለሚ​ገዛ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅግ ቀን​ቻ​ለሁ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ቃል ኪዳ​ን​ህን ትተ​ዋ​ልና፥ መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ች​ህ​ንም አፍ​ር​ሰ​ዋ​ልና፥ ነቢ​ያ​ት​ህ​ንም በሰ​ይፍ ገድ​ለ​ዋ​ልና፤ እኔም ብቻ​ዬን ቀር​ቻ​ለሁ ነፍ​ሴ​ንም ሊወ​ስ​ዱ​አት ይሻሉ” አለ። 11እር​ሱም አለ፥ “ነገ ውጣ፤ በተ​ራ​ራ​ውም ላይ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቁም። እነ​ሆም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚያ አለፈ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ትል​ቅና ብርቱ ነፋስ ተራ​ሮ​ቹን ሰነ​ጠቀ፤ ዓለ​ቶ​ቹ​ንም ሰባ​በረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን በነ​ፋሱ ውስጥ አል​ነ​በ​ረም። ከነ​ፋ​ሱም በኋላ የም​ድር መና​ወጥ ሆነ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን በም​ድር መና​ወጥ ውስጥ አል​ነ​በ​ረም። 12ከም​ድር መና​ወጥ በኋላ እሳት ሆነ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ሳቱ ውስጥ አል​ነ​በ​ረም። ከእ​ሳ​ቱም በኋላ እንደ ፉጨት ያለ ቀጭን ድምፅ ሆነ፤ በዚ​ያም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነበረ። 13ኤል​ያ​ስም ያን በሰማ ጊዜ ፊቱን በመ​ጐ​ና​ጸ​ፊ​ያው ሸፈነ፤ ወጥ​ቶም በዋ​ሻው ደጃፍ ቆመ። እነ​ሆም፥ “ኤል​ያስ ሆይ፥ ወደ​ዚህ ለምን መጣህ?” የሚል ቃል ወደ እርሱ መጣ። 14እር​ሱም፥ “ሁሉን ለሚ​ገዛ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅግ ቀን​ቻ​ለሁ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ቃል ኪዳ​ን​ህን ትተ​ዋ​ልና፥ መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ች​ህ​ንም አፍ​ር​ሰ​ዋ​ልና፥ ነቢ​ያ​ት​ህ​ንም በሰ​ይፍ ገድ​ለ​ዋ​ልና፤ እኔም ብቻ​ዬን ቀር​ቻ​ለሁ፤ ነፍ​ሴ​ንም ሊወ​ስ​ዱ​አት ይሻሉ” አለ።
15እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለው፥ “ሂድ፤ በመ​ጣ​ህ​በ​ትም መን​ገድ በም​ድረ በዳ ወደ ደማ​ስቆ ተመ​ለስ፤ ከዚ​ያም በደ​ረ​ስህ ጊዜ በሶ​ርያ ላይ ንጉሥ ይሆን ዘንድ አዛ​ሄ​ልን ቅባው፤ 16በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ ንጉሥ ይሆን ዘንድ የና​ሚ​ሶን ልጅ ኢዩን ቅባው፤ በፋ​ን​ታ​ህም ነቢይ ይሆን ዘንድ የአ​ቤ​ል​መ​ሁ​ላን ሰው የሣ​ፋ​ጥን ልጅ ኤል​ሳ​ዕን ቅባው፤ 17ከአ​ዛ​ሄ​ልም ሰይፍ የሚ​ያ​መ​ል​ጠ​ውን ሁሉ ኢዩ ይገ​ድ​ለ​ዋል፤ ከኢ​ዩም ሰይፍ የሚ​ያ​መ​ል​ጠ​ውን ሁሉ ኤል​ሳዕ ይገ​ድ​ለ​ዋል። 18እኔም ከእ​ስ​ራ​ኤል ጕል​በ​ታ​ቸ​ውን ለበ​ዓል ያላ​ን​በ​ረ​ከ​ኩ​ትን ሁሉ፥ በአ​ፋ​ቸ​ውም ያል​ሳ​ሙ​ትን ሁሉ፥ ሰባት ሺህ ሰዎች ለእኔ አስ​ቀ​ራ​ለሁ።”
19ከዚ​ያም ሄደ፤ የሣ​ፋ​ጥ​ንም ልጅ ኤል​ሳ​ዕን በዐ​ሥራ ሁለት ጥማድ በሬ​ዎች ሲያ​ርስ፥ እር​ሱም ከዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ጋር ሆኖ አገ​ኘው። ኤል​ያ​ስም ወደ እርሱ አልፎ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ውን ጣለ​በት። 20ኤል​ሳ​ዕም በሬ​ዎ​ቹን ተወ፤ ኤል​ያ​ስ​ንም ተከ​ትሎ ሄደ፥ “አባ​ቴ​ንና እና​ቴን እስ​ማ​ቸው ዘንድ፥ እባ​ክህ ተወኝ፤ ከዚ​ያም በኋላ እከ​ተ​ል​ሃ​ለሁ” አለው። እር​ሱም“ሂድና ተመ​ለስ፤ ምን አድ​ር​ጌ​ል​ሃ​ለሁ?” አለው። 21ከእ​ር​ሱም ዘንድ ተመ​ልሶ ሁለ​ቱን በሬ​ዎች ወስዶ አረ​ዳ​ቸው፤ ሥጋ​ቸ​ው​ንም በበ​ሬ​ዎቹ ዕቃ ቀቀ​ለው፤ ለሕ​ዝ​ቡም ሰጣ​ቸው፤ በሉም፤ እር​ሱም ተነ​ሥቶ ኤል​ያ​ስን ተከ​ትሎ ሄደ፤ ያገ​ለ​ግ​ለ​ውም ነበር።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ