መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 15
15
የይሁዳ ንጉሥ አብያ
(2ዜ.መ. 13፥1—14፥1)
1የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም በነገሠ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት የሮብዓም ልጅ አብያ በይሁዳ ላይ ንጉሥ ሆነ። 2በኢየሩሳሌምም ሦስት ዓመት ነገሠ፤ እናቱም መዓካ የተባለች የአቤሴሎም ልጅ ነበረች። 3ከእርሱም አስቀድሞ ባደረገው በአባቱ ኀጢአት ሁሉ ሄደ፤ ልቡም እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ልብ ከአምላኩ ከእግዚአብሔር ጋር ፍጹም አልነበረም። 4ነገር ግን ልጁን ከእርሱ በኋላ ያስነሣ ዘንድ፥ ኢየሩሳሌምንም ያጸና ዘንድ አምላኩ እግዚአብሔር ስለ ዳዊት በኢየሩሳሌም መብራትን#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ቅሬት” ይላል። አደረገለት፤ 5ከኬጥያዊው ከኦርዮ ነገር በቀር#“ከኬጥያዊው ከኦርዮ ነገር በቀር” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ዳዊት በዘመኑ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገርን አድርጎ ነበርና፥ ካዘዘውም ነገር ሁሉ ፈቀቅ አላለም ነበርና። 6በኢዮርብዓምና በሮብዓም መካከል በዘመናቸው ሁሉ ጠብ ነበረ።#ምዕ. 15 ቍ. 6 በግሪክ ሰባ. ሊ. ዘሩ የለም።
7የቀረውም የአብያ ነገር፥ ያደረገውም ሁሉ፥ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ እነሆ፥ የተጻፈ አይደለምን? በአብያና በኢዮርብአም መካከል ሰልፍ ነበረ። 8ኢዮርብዓም በነገሠ በሃያ አራተኛ ዓመቱ አብያ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊትም ከተማ ቀበሩት። ልጁም አሳ በፋንታው ነገሠ።
9በእስራኤልም ንጉሥ በኢዮርብዓም በሃያ አራተኛው ዓመት#ዕብ. “በሃያኛው ዓመት” ይላል። አሳ በይሁዳ ላይ ነገሠ። 10በኢየሩሳሌምም አርባ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እናቱም ሐና የተባለች የአቤሴሎም ልጅ ነበረች። 11አሳም እንደ አባቱ እንደ ዳዊት በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገርን አደረገ። 12ከሀገሩም የጣዖታትን ምስል ሁሉ#ዕብ. “ሰዶማውያንን” ይላል። አስወገደ፥ አባቶቹም የሠሩአቸውን ጣዖታትን ሁሉ አጠፋ። 13የማምለኪያ ዐፀድ ጣዖታትን ስለ ሠራች እናቱን ሐናን እቴጌ እንዳትሆን ሻራት፤ አሳም የማምለኪያ ዐፀዱን አስቈረጠው፥ በቄድሮንም ፈፋ አጠገብ በእሳት አቃጠለው። 14ነገር ግን በኮረብቶች ላይ ያሉትን መስገጃዎች አላራቀም፤ የአሳ ልብ ግን በዘመኑ ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር ፍጹም ነበረ። 15አባቱ የቀደሰውንና እርሱም የቀደሰውን ወርቅና ብር፥ ዕቃውንም ወደ እግዚአብሔር ቤት አገባው።
16አሳና የእስራኤል ንጉሥ ባኦስ በዘመናቸው ሁሉ ሲዋጉ ኖሩ። 17የእስራኤልም ንጉሥ ባኦስ በይሁዳ ላይ ወጣ፤ ከይሁዳ ንጉሥ ከአሳ ዘንድ ማንም እንዳይወጣ ወደ እርሱም ማንም እንዳይገባ አድርጎ ራማን ሠራት። 18አሳም በእግዚአብሔር ቤትና በንጉሥ ቤተ መዛግብት የተገኘውን ብርና ወርቅ ሁሉ ወስዶ ለአገልጋዮቹ ሰጣቸው፤ ንጉሡም አሳ በደማስቆ ለተቀመጠው ለአዚን ልጅ ለጤቤርማን ልጅ ለሶርያ ንጉሥ ለወልደ አዴር፥ 19“በእኔና በአንተ መካከል በአባቴና በአባትህ መካከል ቃል ኪዳን ጸንቶአል፤ እነሆ፥ ብርና ወርቅ ገጸ በረከት ልኬልሃለሁ፤ እርሱ ከእኔ ዘንድ እንዲርቅ ሄደህ ከእስራኤል ንጉሥ ከባኦስ ጋር ያለህን ቃል ኪዳን አፍርስ” ብሎ ላከ። 20ወልደ አዴርም ለንጉሡ ለአሳ እሺ አለው፤ የሠራዊቱንም አለቆች በእስራኤል ከተሞች ላይ ሰድዶ ኢናንንና ዳንን፥ አቤልቤትመዓካንና ኬኔሬትን ሁሉ የንፍታሌምንም ሀገር ሁሉ መታ። 21ባኦስም ያን በሰማ ጊዜ ራማን መሥራት ትቶ ወደ ቴርሳ ተመለሰ። 22ንጉሡም አሳ በይሁዳ ሁሉ ላይ አዋጅ ነገረ፤ ማንም ነጻ አልነበረም፥ ንጉሡ ባኦስም የሠራበትን የራማን ድንጋይና እንጨት ወሰደ፤ የይሁዳም ንጉሥ አሳ የብንያምንና የመሴፋን ኮረብታ ሠራበት።
23የቀረውም የአሳ ነገር ሁሉ ብርቱ ሥራዎቹም ሁሉ፥ ያደረገውም ሁሉ፥ በይሁዳ ነገሥት ታሪክ የተጻፈ አይደለምን? ነገር ግን በሸመገለ ጊዜ እግሮቹ ታመሙ። 24አሳም እንደ አባቶቹ አንቀላፋ፤ በአባቱም በዳዊት ከተማ ከአባቶቹ ጋር ተቀበረ። ልጁም ኢዮሣፍጥ በፋንታው ነገሠ።
25በይሁዳም ንጉሥ በአሳ በሁለተኛው ዓመት የኢዮርብዓም ልጅ ናባጥ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ በእስራኤልም ላይ ሁለት ዓመት ነገሠ። 26በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ አደረገ፤ በአባቱም መንገድ እስራኤልንም ባሳተበት ኀጢአት ሄደ። 27ከበለዓን#ዕብ. “ይሳኮር” ይላል። ቤት የሆነ የአኪያ ልጅ ባኦስ ዐመፀበት፤ ናባጥና እስራኤልም ሁሉ ገባቶንን ከብበው ነበርና ባኦስ በፍልስጥኤልም ሀገር ባለው በገባቶን ገደለው። 28በይሁዳ ንጉሥ በአሳ በሦስተኛው ዓመተ መንግሥት ባኦስ ናባጥን ገደለው፥ በፋንታውም ነገሠ። 29ከነገሠም በኋላ የኢዮርብዓምን ወገን ሁሉ አጠፋ፥ በባሪያው በሴሎናዊው በአኪያ እጅ እንደ ተናገረው እንደ እግዚአብሔር ቃል፥ እስኪያጠፋው ድረስ ከኢዮርብዓም ወገን ሕይወት ያለውን አላስቀረም። 30ይኸውም ኢዮርብዓም ስለ ሠራው ኀጢአት፥ እስራኤልንም ስላሳተበት፥ የእስራኤልንም አምላክ እግዚአብሔርን ስላስቈጣበት ማስቈጣት ነው።
31የቀረውም የናባጥ ነገርና ያደረገውም ሁሉ፥ እነሆ፥ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? 32በአሳና በእስራኤል ንጉሥ በባኦስ መካከል በዘመናቸው ሁሉ ጦርነት ነበረ።#በምዕ. 15 ቍ. 32 የተጻፈው በአንዳንድ የግሪክ ሰባ. ሊ. እና የግእዝ ዘርዕ አይገኝም።
33በይሁዳም ንጉሥ በአሳ በሦስተኛው ዓመት የአኪያ ልጅ ባኦስ በእስራኤል ሁሉ ላይ በቴርሣ ንጉሥ ሆኖ ሃያ አራት ዓመት ነገሠ። 34በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ አደረገ፥ በናባጥም ልጅ በኢዮርብዓም መንገድ እስራኤልንም ባሳተበት ኀጢአት ሄደ።
Currently Selected:
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 15: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ