የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ቀዳ​ማዊ 15

15
የይ​ሁዳ ንጉሥ አብያ
(2ዜ.መ. 13፥1—14፥1)
1የና​ባጥ ልጅ ኢዮ​ር​ብ​ዓም በነ​ገሠ በዐ​ሥራ ስም​ን​ተ​ኛው ዓመት የሮ​ብ​ዓም ልጅ አብያ በይ​ሁዳ ላይ ንጉሥ ሆነ። 2በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሦስት ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም መዓካ የተ​ባ​ለች የአ​ቤ​ሴ​ሎም ልጅ ነበ​ረች። 3ከእ​ር​ሱም አስ​ቀ​ድሞ ባደ​ረ​ገው በአ​ባቱ ኀጢ​አት ሁሉ ሄደ፤ ልቡም እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ልብ ከአ​ም​ላኩ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ፍጹም አል​ነ​በ​ረም። 4ነገር ግን ልጁን ከእ​ርሱ በኋላ ያስ​ነሣ ዘንድ፥ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ያጸና ዘንድ አም​ላኩ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ዳዊት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም መብ​ራ​ትን#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ቅሬት” ይላል። አደ​ረ​ገ​ለት፤ 5ከኬ​ጥ​ያ​ዊው ከኦ​ርዮ ነገር በቀር#“ከኬ​ጥ​ያ​ዊው ከኦ​ርዮ ነገር በቀር” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ዳዊት በዘ​መኑ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቅን ነገ​ርን አድ​ርጎ ነበ​ርና፥ ካዘ​ዘ​ውም ነገር ሁሉ ፈቀቅ አላ​ለም ነበ​ርና። 6በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓ​ምና በሮ​ብ​ዓም መካ​ከል በዘ​መ​ና​ቸው ሁሉ ጠብ ነበረ።#ምዕ. 15 ቍ. 6 በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. ዘሩ የለም።
7የቀ​ረ​ውም የአ​ብያ ነገር፥ ያደ​ረ​ገ​ውም ሁሉ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት ታሪክ መጽ​ሐፍ እነሆ፥ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን? በአ​ብ​ያና በኢ​ዮ​ር​ብ​አም መካ​ከል ሰልፍ ነበረ። 8ኢዮ​ር​ብ​ዓም በነ​ገሠ በሃያ አራ​ተኛ ዓመቱ አብያ ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ቀበ​ሩት። ልጁም አሳ በፋ​ን​ታው ነገሠ።
9በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም በሃያ አራ​ተ​ኛው ዓመት#ዕብ. “በሃ​ያ​ኛው ዓመት” ይላል። አሳ በይ​ሁዳ ላይ ነገሠ። 10በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም አርባ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም ሐና የተ​ባ​ለች የአ​ቤ​ሴ​ሎም ልጅ ነበ​ረች። 11አሳም እንደ አባቱ እንደ ዳዊት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቅን ነገ​ርን አደ​ረገ። 12ከሀ​ገ​ሩም የጣ​ዖ​ታ​ትን ምስል ሁሉ#ዕብ. “ሰዶ​ማ​ው​ያ​ንን” ይላል። አስ​ወ​ገደ፥ አባ​ቶ​ቹም የሠ​ሩ​አ​ቸ​ውን ጣዖ​ታ​ትን ሁሉ አጠፋ። 13የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀድ ጣዖ​ታ​ትን ስለ ሠራች እና​ቱን ሐናን እቴጌ እን​ዳ​ት​ሆን ሻራት፤ አሳም የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዱን አስ​ቈ​ረ​ጠው፥ በቄ​ድ​ሮ​ንም ፈፋ አጠ​ገብ በእ​ሳት አቃ​ጠ​ለው። 14ነገር ግን በኮ​ረ​ብ​ቶች ላይ ያሉ​ትን መስ​ገ​ጃ​ዎች አላ​ራ​ቀም፤ የአሳ ልብ ግን በዘ​መኑ ሁሉ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ፍጹም ነበረ። 15አባቱ የቀ​ደ​ሰ​ው​ንና እር​ሱም የቀ​ደ​ሰ​ውን ወር​ቅና ብር፥ ዕቃ​ው​ንም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አገ​ባው።
16አሳና የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ባኦስ በዘ​መ​ና​ቸው ሁሉ ሲዋጉ ኖሩ። 17የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ባኦስ በይ​ሁዳ ላይ ወጣ፤ ከይ​ሁዳ ንጉሥ ከአሳ ዘንድ ማንም እን​ዳ​ይ​ወጣ ወደ እር​ሱም ማንም እን​ዳ​ይ​ገባ አድ​ርጎ ራማን ሠራት። 18አሳም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤትና በን​ጉሥ ቤተ መዛ​ግ​ብት የተ​ገ​ኘ​ውን ብርና ወርቅ ሁሉ ወስዶ ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮቹ ሰጣ​ቸው፤ ንጉ​ሡም አሳ በደ​ማ​ስቆ ለተ​ቀ​መ​ጠው ለአ​ዚን ልጅ ለጤ​ቤ​ር​ማን ልጅ ለሶ​ርያ ንጉሥ ለወ​ልደ አዴር፥ 19“በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል በአ​ባ​ቴና በአ​ባ​ትህ መካ​ከል ቃል ኪዳን ጸን​ቶ​አል፤ እነሆ፥ ብርና ወርቅ ገጸ በረ​ከት ልኬ​ል​ሃ​ለሁ፤ እርሱ ከእኔ ዘንድ እን​ዲ​ርቅ ሄደህ ከእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ከባ​ኦስ ጋር ያለ​ህን ቃል ኪዳን አፍ​ርስ” ብሎ ላከ። 20ወልደ አዴ​ርም ለን​ጉሡ ለአሳ እሺ አለው፤ የሠ​ራ​ዊ​ቱ​ንም አለ​ቆች በእ​ስ​ራ​ኤል ከተ​ሞች ላይ ሰድዶ ኢና​ን​ንና ዳንን፥ አቤ​ል​ቤ​ት​መ​ዓ​ካ​ንና ኬኔሬ​ትን ሁሉ የን​ፍ​ታ​ሌ​ም​ንም ሀገር ሁሉ መታ። 21ባኦ​ስም ያን በሰማ ጊዜ ራማን መሥ​ራት ትቶ ወደ ቴርሳ ተመ​ለሰ። 22ንጉ​ሡም አሳ በይ​ሁዳ ሁሉ ላይ አዋጅ ነገረ፤ ማንም ነጻ አል​ነ​በ​ረም፥ ንጉሡ ባኦ​ስም የሠ​ራ​በ​ትን የራ​ማን ድን​ጋ​ይና እን​ጨት ወሰደ፤ የይ​ሁ​ዳም ንጉሥ አሳ የብ​ን​ያ​ም​ንና የመ​ሴ​ፋን ኮረ​ብታ ሠራ​በት።
23የቀ​ረ​ውም የአሳ ነገር ሁሉ ብርቱ ሥራ​ዎ​ቹም ሁሉ፥ ያደ​ረ​ገ​ውም ሁሉ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥት ታሪክ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን? ነገር ግን በሸ​መ​ገለ ጊዜ እግ​ሮቹ ታመሙ። 24አሳም እንደ አባ​ቶቹ አን​ቀ​ላፋ፤ በአ​ባ​ቱም በዳ​ዊት ከተማ ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ተቀ​በረ። ልጁም ኢዮ​ሣ​ፍጥ በፋ​ን​ታው ነገሠ።
25በይ​ሁ​ዳም ንጉሥ በአሳ በሁ​ለ​ተ​ኛው ዓመት የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ልጅ ናባጥ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ነገሠ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ ሁለት ዓመት ነገሠ። 26በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ አደ​ረገ፤ በአ​ባ​ቱም መን​ገድ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ባሳ​ተ​በት ኀጢ​አት ሄደ። 27ከበ​ለ​ዓን#ዕብ. “ይሳ​ኮር” ይላል። ቤት የሆነ የአ​ኪያ ልጅ ባኦስ ዐመ​ፀ​በት፤ ናባ​ጥና እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ገባ​ቶ​ንን ከብ​በው ነበ​ርና ባኦስ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ልም ሀገር ባለው በገ​ባ​ቶን ገደ​ለው። 28በይ​ሁዳ ንጉሥ በአሳ በሦ​ስ​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት ባኦስ ናባ​ጥን ገደ​ለው፥ በፋ​ን​ታ​ውም ነገሠ። 29ከነ​ገ​ሠም በኋላ የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓ​ምን ወገን ሁሉ አጠፋ፥ በባ​ሪ​ያው በሴ​ሎ​ና​ዊው በአ​ኪያ እጅ እንደ ተና​ገ​ረው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል፥ እስ​ኪ​ያ​ጠ​ፋው ድረስ ከኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ወገን ሕይ​ወት ያለ​ውን አላ​ስ​ቀ​ረም። 30ይኸ​ውም ኢዮ​ር​ብ​ዓም ስለ ሠራው ኀጢ​አት፥ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ስላ​ሳ​ተ​በት፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስላ​ስ​ቈ​ጣ​በት ማስ​ቈ​ጣት ነው።
31የቀ​ረ​ውም የና​ባጥ ነገ​ርና ያደ​ረ​ገ​ውም ሁሉ፥ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን? 32በአ​ሳና በእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ በባ​ኦስ መካ​ከል በዘ​መ​ና​ቸው ሁሉ ጦር​ነት ነበረ።#በምዕ. 15 ቍ. 32 የተ​ጻ​ፈው በአ​ን​ዳ​ንድ የግ​ሪክ ሰባ. ሊ. እና የግ​እዝ ዘርዕ አይ​ገ​ኝም።
33በይ​ሁ​ዳም ንጉሥ በአሳ በሦ​ስ​ተ​ኛው ዓመት የአ​ኪያ ልጅ ባኦስ በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ላይ በቴ​ርሣ ንጉሥ ሆኖ ሃያ አራት ዓመት ነገሠ። 34በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ አደ​ረገ፥ በና​ባ​ጥም ልጅ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም መን​ገድ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ባሳ​ተ​በት ኀጢ​አት ሄደ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ