የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ቀዳ​ማዊ 1

1
ንጉሥ ዳዊት እንደ ሸመ​ገለ
1ንጉሡ ዳዊ​ትም አረጀ፤ ዘመ​ኑም አለፈ፤ ልብ​ስም ይደ​ር​ቡ​ለት ነበር፤ ነገር ግን አይ​ሞ​ቀ​ውም ነበር። 2የዳ​ዊት አሽ​ከ​ሮ​ችም፥ “ለጌ​ታ​ችን ለን​ጉሡ ድን​ግል ልጅ ትፈ​ለ​ግ​ለት፤ በን​ጉ​ሡም ፊት ቆማ ታገ​ል​ግ​ለው፥ በጌ​ታ​ች​ንም በን​ጉሡ ብብት ተኝታ ትቀ​ፈው፤ ታሙ​ቀ​ውም” አሉ። 3በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሀገር ሁሉ የተ​ዋ​በች ቆንጆ ፈለጉ፤ ሱነ​ማ​ዪ​ቱን አቢ​ሳ​ንም አገኙ፤ ወደ ንጉ​ሡም ወሰ​ዱ​አት። 4ቆን​ጆ​ዪ​ቱም እጅግ ውብ ነበ​ረች፤ ንጉ​ሡ​ንም ታቅ​ፈ​ውና ታገ​ለ​ግ​ለው ነበር፤ ንጉሡ ግን አያ​ው​ቃ​ትም ነበር።
አዶ​ን​ያስ ለመ​ን​ገሥ እንደ ሞከረ
5የአ​ጊ​ትም ልጅ አዶ​ን​ያስ፥ “ንጉሥ እሆ​ና​ለሁ” ብሎ ተነሣ፤ ሰረ​ገ​ሎ​ች​ንና ፈረ​ሰ​ኞ​ችን በፊ​ቱም የሚ​ሮጡ አምሳ ሰዎ​ችን አዘ​ጋጀ። 6አባ​ቱም፥ “ከቶ ለምን እን​ዲህ ታደ​ር​ጋ​ለህ?” ብሎ አል​ከ​ለ​ከ​ለ​ውም ነበር፤ እር​ሱም ደግሞ መልኩ እጅግ ያማረ ሰው ነበረ፤ እር​ሱ​ንም ከአ​ቤ​ሴ​ሎም በኋላ ወል​ዶት ነበር። 7ሴራ​ውም ከሶ​ር​ህያ ልጅ ከኢ​ዮ​አ​ብና ከካ​ህኑ ከአ​ብ​ያ​ታር ጋር ነበረ፤ እነ​ር​ሱም አዶ​ን​ያ​ስን ተከ​ት​ለው ይረ​ዱት ነበር። 8ነገር ግን ካህኑ ሳዶ​ቅና የዮ​ዳሄ ልጅ በና​ያስ ነቢ​ዩም ናታን፥ ሳሚም፥ ሬሲም፥ የዳ​ዊ​ትም ኀያ​ላን አዶ​ን​ያ​ስን አል​ተ​ከ​ተ​ሉም ነበር። 9አዶ​ን​ያ​ስም በጎ​ች​ንና በሬ​ዎ​ችን፥ ጠቦ​ቶ​ች​ንም በሮ​ጌል ምንጭ አጠ​ገብ ባለ​ችው በዞ​ሔ​ሌት ድን​ጋይ ዘንድ ሠዋ፤ የን​ጉ​ሡ​ንም ልጆች ወን​ድ​ሞ​ቹን ሁሉ፥ የን​ጉ​ሡ​ንም አገ​ል​ጋ​ዮች፥ የይ​ሁ​ዳ​ንም ኀያ​ላን ሁሉ ጠራ። 10ነገር ግን ነቢ​ዩን ናታ​ንን፥ በና​ያ​ስ​ንም፥ ኀያ​ላ​ኑ​ንም፥ ወን​ድ​ሙ​ንም ሰሎ​ሞ​ንን አል​ጠ​ራም።
ሰሎ​ሞን እንደ ነገሠ
11ናታ​ንም የሰ​ሎ​ሞ​ንን እናት ቤር​ሳ​ቤ​ህን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራት፥ “ጌታ​ችን ዳዊት ሳያ​ውቅ የአ​ጊት ልጅ አዶ​ን​ያስ እንደ ነገሠ አል​ሰ​ማ​ሽ​ምን? 12አሁ​ንም ነዪ፤ የል​ጅ​ሽን የሰ​ሎ​ሞ​ንን ነፍ​ስና የአ​ን​ቺን ነፍስ እን​ድ​ታ​ድኚ እመ​ክ​ር​ሻ​ለሁ። 13ሄደሽ ወደ ንጉሡ ወደ ዳዊት ግቢና፦ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ለእኔ ለአ​ገ​ል​ጋ​ይህ፦ ልጅሽ ሰሎ​ሞን ከእኔ በኋላ ይነ​ግ​ሣል፤ በዙ​ፋ​ኔም ይቀ​መ​ጣል ብለህ አል​ማ​ል​ህ​ል​ኝ​ምን? ስለ​ም​ንስ አዶ​ን​ያስ ይነ​ግ​ሣል? በዪው። 14እነሆ፥ አንቺ በዚያ ለን​ጉሥ ስት​ነ​ግሪ እኔ ከአ​ንቺ በኋላ እገ​ባ​ለሁ፤ ቃል​ሽ​ንም አጸ​ና​ለሁ።”
15ቤር​ሳ​ቤ​ህም ወደ ንጉሡ ወደ እል​ፍኝ ገባች፤ ንጉ​ሡም እጅግ ሸም​ግሎ ነበር፤ ሱነ​ማ​ዪ​ቱም አቢሳ ንጉ​ሡን ታገ​ለ​ግ​ለው ነበር። 16ቤር​ሳ​ቤ​ህም አጎ​ን​ብሳ ለን​ጉሡ ሰገ​ደች፤ ንጉ​ሡም፥ “ምን ሆንሽ?” አላት። 17እር​ስ​ዋም አለ​ችው፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ አንተ ለአ​ገ​ል​ጋ​ይህ፦ ልጅሽ ሰሎ​ሞን ከእኔ በኋላ ይነ​ግ​ሣል፤ በዙ​ፋ​ኔም ይቀ​መ​ጣል ብለህ በአ​ም​ላ​ክህ ምለ​ህ​ልኝ አል​ነ​በ​ረ​ምን? 18አሁ​ንም፥ እነሆ፥ አዶ​ን​ያስ መን​ገሡ ነው፤ አን​ተም ጌታዬ ንጉሥ ይህን አታ​ው​ቅም፤ 19እር​ሱም ብዙ በሬ​ዎ​ች​ንና ጠቦ​ቶ​ችን፥ በጎ​ች​ንም ሠው​ቶ​አል፤ የን​ጉ​ሡ​ንም ልጆች ሁሉ፥ ካህ​ኑ​ንም አብ​ያ​ታ​ርን፥ የሠ​ራ​ዊ​ቱ​ንም አለቃ ኢዮ​አ​ብን ጠር​ቶ​አል፤ ባሪ​ያ​ህን ሰሎ​ሞ​ንን ግን አል​ጠ​ራ​ውም። 20አሁ​ንም ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ከአ​ንተ በኋላ በጌ​ታዬ በን​ጉሥ ዙፋን ላይ የሚ​ቀ​መ​ጠ​ውን ትነ​ግ​ራ​ቸው ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ዐይን ይመ​ለ​ከ​ት​ሃል። 21ይህ ባይ​ሆን፥ ጌታዬ ንጉሥ ከአ​ባ​ቶ​ችህ ጋር ባን​ቀ​ላ​ፋህ ጊዜ እኔና ልጄ ሰሎ​ሞን እንደ ኀጢ​አ​ተ​ኞች እን​ቈ​ጠ​ራ​ለን።”
22እነ​ሆም፥ እር​ስዋ ከን​ጉሡ ጋር ስት​ነ​ጋ​ገር ነቢዩ ናታን መጣ፤ 23ለን​ጉ​ሡም፥ “እነሆ፥ ነቢዩ ናታን መጥ​ቶ​አል” ብለው ነገ​ሩት፤ እር​ሱም ወደ ንጉሡ ፊት በገባ ጊዜ በግ​ን​ባሩ በም​ድር ላይ ተደ​ፍቶ ለን​ጉሡ እጅ ነሣ። 24ነቢዩ ናታ​ንም አለ፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፦ አንተ ከእኔ በኋላ አዶ​ን​ያስ ይነ​ግ​ሣል፥ በዙ​ፋኔ ላይም ይቀ​መ​ጣል ብለ​ሃ​ልን? 25እርሱ ዛሬ ወርዶ ብዙ በሬ​ዎ​ች​ንና ጠቦ​ቶ​ችን፥ በጎ​ች​ንም ሠው​ቶ​አል፤ የን​ጉ​ሡ​ንም ልጆች ሁሉ፥ የሠ​ራ​ዊ​ቱን አለቃ ኢዮ​አ​ብን፥ ካህ​ኑ​ንም አብ​ያ​ታ​ርን ጠር​ቶ​አል፤ እነ​ሆም፥ በፊቱ እየ​በ​ሉና እየ​ጠጡ፦ አዶ​ን​ያስ ሺህ ዓመት ይን​ገሥ ይላሉ። 26ነገር ግን እኔን አገ​ል​ጋ​ይ​ህን፥ ካህ​ኑ​ንም ሳዶ​ቅን፥ የዮ​ዳ​ሄ​ንም ልጅ በና​ያ​ስን፥ አገ​ል​ጋ​ይ​ህ​ንም ሰሎ​ሞ​ንን አል​ጠ​ራም። 27በውኑ ይህ ነገር ከጌ​ታዬ ከን​ጉሡ የተ​ደ​ረገ ነገር ነውን? ለአ​ገ​ል​ጋ​ይ​ህም ከአ​ንተ በኋላ በጌ​ታዬ በን​ጉሡ ዙፋን ላይ የሚ​ቀ​መ​ጠ​ውን ለምን አል​ነ​ገ​ር​ኸ​ውም?”
28ንጉ​ሡም ዳዊት፥ “ቤር​ሳ​ቤ​ህን ጥሩ​ልኝ” ብሎ መለሰ። ወደ ንጉ​ሡም ገባች፤ በን​ጉ​ሡም ፊት ቆመች። 29ንጉ​ሡም እን​ዲህ ብሎ ማለ፥ “ነፍ​ሴን ከመ​ከራ ሁሉ ያዳ​ነኝ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! 30በእ​ው​ነት፦ ልጅሽ ሰሎ​ሞን ከእኔ በኋላ ይነ​ግ​ሣል፤ በእ​ኔም ፋንታ በዙ​ፋኔ ላይ ይቀ​መ​ጣል ብዬ በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ማል​ሁ​ልሽ፥ እን​ዲሁ ዛሬ በእ​ው​ነት አደ​ር​ጋ​ለሁ።” 31ቤር​ሳ​ቤ​ህም በግ​ን​ባ​ርዋ በም​ድር ላይ ተደ​ፍታ ለን​ጉሡ ሰገ​ደ​ችና፥ “ጌታዬ ንጉሥ ዳዊት ለዘ​ለ​ዓ​ለም በሕ​ይ​ወት ይኑር” አለች።
32ንጉ​ሡም ዳዊት፥ “ካህ​ኑን ሳዶ​ቅ​ንና ነቢዩ ናታ​ንን የዮ​ዳ​ሄ​ንም ልጅ በና​ያ​ስን ጥሩ​ልኝ” አለ። 33ወደ ንጉ​ሡም ገቡ። ንጉ​ሡም አላ​ቸው፥ “የጌ​ታ​ች​ሁን አገ​ል​ጋ​ዮች ይዛ​ችሁ ሂዱ፥ ልጄ​ንም ሰሎ​ሞ​ንን በበ​ቅ​ሎዬ ላይ አስ​ቀ​ም​ጡት፥ ወደ ግዮ​ንም አው​ር​ዱት፤ 34በዚ​ያም ካህኑ ሳዶ​ቅና ነቢዩ ናታን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ቀብ​ተው ያን​ግ​ሡት፤ መለ​ከ​ትም ነፍ​ታ​ችሁ፦ ሰሎ​ሞን ሺህ ዓመት ይን​ገሥ በሉ። 35በኋ​ላ​ውም ተከ​ት​ላ​ችሁ ውጡ፤#“በኋ​ላ​ውም ተከ​ት​ላ​ችሁ ውጡ” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። እር​ሱም መጥቶ በዙ​ፋኔ ላይ ይቀ​መጥ፤ በእ​ኔም ፋንታ ይን​ገሥ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በይ​ሁ​ዳም ላይ ይነ​ግሥ ዘንድ አዝ​ዣ​ለሁ።” 36የዮ​ዳ​ሄም ልጅ በና​ያስ መልሶ ለን​ጉሡ አለ፥ “እን​ዲሁ ይሁን፤ የጌ​ታ​ዬም የን​ጉሥ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ያጽና። 37እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከጌ​ታዬ ከን​ጉሥ ጋር እንደ ነበረ እን​ዲሁ ከሰ​ሎ​ሞን ጋር ይሁን፤ ዙፋ​ኑ​ንም ከጌ​ታዬ ከን​ጉሡ ከዳ​ዊት ዙፋን የበ​ለጠ ያድ​ርግ።”
38ካህ​ኑም ሳዶ​ቅና ነቢዩ ናታን የዮ​ዳ​ሄም ልጅ በና​ያስ ከሊ​ታ​ው​ያ​ንና ፈሊ​ታ​ው​ያ​ንም ወረዱ፤ ሰሎ​ሞ​ን​ንም በን​ጉሡ በዳ​ዊት በቅሎ ላይ አስ​ቀ​ም​ጠው ወደ ግዮን ወሰ​ዱት። 39ካህ​ኑም ሳዶቅ ከድ​ን​ኳኑ የዘ​ይ​ቱን ቀንድ ወስዶ ሰሎ​ሞ​ንን ቀባ፤ መለ​ከ​ትም ነፋ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ፥ “ሰሎ​ሞን ሺህ ዓመት ይን​ገሥ” አሉ። 40ሕዝ​ቡም ሁሉ እር​ሱን ተከ​ት​ለው ወጡ፤ ከበ​ሮ​ንና መሰ​ን​ቆ​ንም መቱ፥#“ከበ​ሮ​ንና መሰ​ን​ቆን መቱ” የሚ​ለው በዕብ. እና በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። በታ​ላ​ቅም ደስታ ደስ አላ​ቸው፤ ከጩ​ኸ​ታ​ቸ​ውም የተ​ነሣ ምድር ተና​ወ​ጠች።
41አዶ​ን​ያ​ስና እር​ሱም የጠ​ራ​ቸው ሁሉ መብ​ሉና መጠጡ ተፈ​ጽሞ ሳለ ሰሙ፤ ኢዮ​አ​ብም የመ​ለ​ከት ድምፅ በሰማ ጊዜ፥ “ይህ በከ​ተማ የም​ሰ​ማው ድምፅ ምን​ድን ነው?” አለ። 42እር​ሱም ይህን ሲና​ገር የካ​ህኑ የአ​ብ​ያ​ታር ልጅ ዮና​ታን መጣ፤ አዶ​ን​ያ​ስም፥ “አንተ ኀያል ሰው ነህና፥ መል​ካ​ምም ታወ​ራ​ል​ና​ለ​ህና ግባ” አለው። 43ዮና​ታ​ንም ለአ​ዶ​ን​ያስ እን​ዲህ ብሎ መለሰ፥ “በእ​ው​ነት ጌታ​ችን ንጉሥ ዳዊት ሰሎ​ሞ​ንን አነ​ገ​ሠው። 44ንጉ​ሡም ከእ​ርሱ ጋር ካህ​ኑን ሳዶ​ቅ​ንና ነቢ​ዩን ናታ​ንን፥ የዮ​ዳ​ሄ​ንም ልጅ በና​ያ​ስን፥ ከሊ​ታ​ው​ያ​ን​ንና ፈሊ​ታ​ው​ያ​ን​ንም ላከ፤ በን​ጉ​ሡም በቅሎ ላይ አስ​ቀ​መ​ጡት። 45ካህ​ኑም ሳዶ​ቅና ነቢዩ ናታን ቀብ​ተው በግ​ዮን አነ​ገ​ሡት፤ ከዚ​ያም ደስ ብሎ​አ​ቸው ወጡ፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱም አስ​ተ​ጋ​ባች፤ የሰ​ማ​ች​ሁ​ትም ድምፅ ይህ ነው። 46ሰሎ​ሞ​ንም በመ​ን​ግ​ሥቱ ዙፋን ላይ ተቀ​ም​ጦ​አል። 47የን​ጉ​ሡም አገ​ል​ጋ​ዮች ገብ​ተው፦ ‘እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ሎ​ሞ​ንን ስም ከስ​ምህ ይልቅ መል​ካም ያድ​ርግ፤ ዙፋ​ኑ​ንም ከዙ​ፋ​ንህ የበ​ለጠ ያድ​ርግ’ ብለው ጌታ​ቸ​ውን ንጉሡ ዳዊ​ትን መረቁ፤” ንጉ​ሡም በአ​ል​ጋው ላይ ሆኖ ሰገደ። 48ንጉ​ሡም፥ “ዐይኔ እያየ ዛሬ በዙ​ፋኔ ላይ የሚ​ቀ​መ​ጠ​ውን ዘር የሰ​ጠኝ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን” አለ።
49አዶ​ን​ያ​ስም የጠ​ራ​ቸው ሁሉ ፈሩ፤ ተነ​ሥ​ተ​ውም እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው በየ​መ​ን​ገ​ዳ​ቸው ሄዱ። 50አዶ​ን​ያ​ስም ከሰ​ሎ​ሞን ፊት የተ​ነሣ ፈራ፤ ተነ​ሥ​ቶም ሄደ፤ የመ​ሠ​ዊ​ያ​ው​ንም ቀንድ ያዘ። 51ለሰ​ሎ​ሞ​ንም፥ “እነሆ፥ አዶ​ን​ያስ ንጉ​ሡን ሰሎ​ሞ​ንን ፈርቶ፦ ንጉሡ ሰሎ​ሞን አገ​ል​ጋ​ዩን በሰ​ይፍ እን​ዳ​ይ​ገ​ድ​ለኝ ዛሬ ይማ​ል​ልኝ ብሎ የመ​ሠ​ዊ​ያ​ውን ቀንድ ይዞ​አል” አሉት። 52ሰሎ​ሞ​ንም፥ “እርሱ አካ​ሄ​ዱን ያሳ​መረ እንደ ሆነ ከእ​ርሱ አን​ዲት ጠጕር እንኳ በም​ድር ላይ አት​ወ​ድ​ቅም፤ ነገር ግን ክፋት የተ​ገ​ኘ​በት እንደ ሆነ ይሞ​ታል” አለ። 53ንጉሡ ሰሎ​ሞ​ንም ላከ፤ ከመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም አወ​ረ​ዱት፤ መጥ​ቶም ለን​ጉሡ ለሰ​ሎ​ሞን ሰገደ፤ ሰሎ​ሞ​ንም፥ “ወደ ቤትህ ሂድ” አለው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ