የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ካልእ 24

24
ዳዊት ሕዝ​ቡን እን​ዳ​ስ​ቈ​ጠረ
(1ዜ.መ. 21፥1-27)
1ደግ​ሞም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ነደደ፤ ዳዊ​ት​ንም፥ “ሂድ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንና ይሁ​ዳን ቍጠር” ብሎ በላ​ያ​ቸው አስ​ነ​ሣው። 2ንጉ​ሡም ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ረ​ውን የሠ​ራ​ዊት አለቃ ኢዮ​አ​ብን፥ “የሕ​ዝ​ቡን ድምር አውቅ ዘንድ ከዳን ጀምሮ እስከ ቤር​ሳ​ቤህ ድረስ ሂድ፤ ሕዝ​ቡ​ንም ቍጠ​ራ​ቸው” አለው። 3ኢዮ​አ​ብም ንጉ​ሡን፥ “የጌ​ታዬ የን​ጉሡ ዐይን እያየ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዛሬ ካለው ሕዝብ መጠን በላይ መቶ እጥፍ ይጨ​ም​ር​በት፤ ጌታዬ ንጉሡ ግን ይህን ነገር ለምን ይፈ​ል​ጋል?” አለው። 4ነገር ግን የን​ጉሡ ቃል በኢ​ዮ​አ​ብና በሠ​ራ​ዊቱ አለ​ቆች ላይ አሸ​ነፈ። ኢዮ​አ​ብና የሠ​ራ​ዊቱ አለ​ቆ​ችም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሕዝብ ይቈ​ጥሩ ዘንድ ከን​ጉሥ ዘንድ ወጡ። 5ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም ተሻ​ገሩ፤ በጋድ ሸለቆ መካ​ከል ባለ​ች​ውም በኢ​ያ​ዜር ከተማ ቀኝ በኩል በአ​ሮ​ዔር ላይ ሰፈሩ። 6ወደ ገለ​ዓ​ድም አዳ​ሳይ ወደ​ም​ት​ባል ወደ ተባ​ሶን ሀገ​ርም መጡ፤ ወደ ዳኒ​ዳ​ንና ወደ ኡዳ​ንም ደረሱ፤ ወደ ሲዶ​ናም ዞሩ፤ 7ወደ ጤሮ​ስም ምሽግ ወደ ኤዌ​ዎ​ና​ው​ያን፥ ወደ ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንም ከተ​ሞች ሁሉ መጡ፤ በይ​ሁ​ዳም ደቡብ በኩል በቤ​ር​ሳ​ቤህ ወጡ። 8በሀ​ገ​ሪ​ቱም ሁሉ ላይ ተመ​ላ​ል​ሰው ከዘ​ጠኝ ወርና ከሃያ ቀን በኋላ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሱ። 9ኢዮ​አ​ብም የሕ​ዝ​ቡን ቍጥር ድምር ለን​ጉሡ ሰጠ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰይፍ የሚ​መ​ዝዙ ስም​ንት መቶ ሺህ ጽኑ​ዓን ሰዎች ነበሩ፤ የይ​ሁ​ዳም ተዋ​ጊ​ዎች ሰዎች አም​ስት መቶ ሺህ ነበሩ።
10ሕዝ​ቡ​ንም ከቈ​ጠረ በኋላ ዳዊ​ትን ልቡ መታው፤ ዳዊ​ትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፥ “ባደ​ረ​ግ​ሁት ነገር እጅግ በድ​ያ​ለሁ፤ አሁን ግን አቤቱ! ታላቅ ስን​ፍና አድ​ር​ጌ​አ​ለ​ሁና የባ​ሪ​ያ​ህን ኀጢ​አት ታርቅ ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ” አለው። 11ዳዊ​ትም ማልዶ በተ​ነሣ ጊዜ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ ዳዊት ባለ ራእይ ወደ ነቢዩ ወደ ጋድ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 12“ሂድና ለዳ​ዊት እን​ዲህ ብለህ ንገ​ረው፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ሦስት ነገ​ሮ​ችን በፊ​ትህ አኖ​ራ​ለሁ፤ አደ​ር​ግ​ብህ ዘንድ ከእ​ነ​ርሱ አን​ዱን ምረጥ።” 13ጋድም ወደ ዳዊት መጥቶ፥ “የሦ​ስት ዓመት ራብ በሀ​ገ​ርህ ላይ ይም​ጣ​ብ​ህን? ወይስ ጠላ​ቶ​ችህ እያ​ሳ​ደ​ዱህ ሦስት ወር ከእ​ነ​ርሱ ትሸ​ሽን? ወይስ የሦ​ስት ቀን ቸነ​ፈር በሀ​ገ​ርህ ላይ ይሁን? የሚ​ሻ​ል​ህን ምረጥ። አሁ​ንም ለላ​ከኝ ምን መልስ እን​ደ​ም​ሰጥ አስ​ብና መር​ምር” ብሎ ነገ​ረው። 14ዳዊ​ትም ጋድን፥ “በሁ​ሉም እጅግ ተጨ​ን​ቄ​አ​ለሁ፤ በሰው እጅ ከም​ወ​ድቅ ይልቅ ምሕ​ረቱ ብዙ ነውና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ መው​ደቅ#ዕብ. “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ እን​ው​ደቅ ...” ይላል። ይሻ​ለ​ኛል” አለው።
15ዳዊ​ትም ቸነ​ፈ​ሩን መረጠ፤ የስ​ን​ዴም መከር ወራት በሆነ ጊዜ ጌታ ከጥ​ዋት እስከ ቀትር ቸነ​ፈ​ርን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ላከ። ቸነ​ፈ​ሩም በሕ​ዝቡ መካ​ከል ጀመረ፤ ከሕ​ዝ​ቡም ከዳን እስከ ቤር​ሳ​ቤህ ሰባ ሺህ ሰው ሞተ። 16የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ያጠ​ፋት ዘንድ እጁን ዘረጋ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከክ​ፉው ነገር ይቅር አላት፤ ሕዝ​ቡ​ንም የሚ​ያ​ጠ​ፋ​ውን መል​አክ፥ “እን​ግ​ዲህ በቃህ፤ እጅ​ህን መልስ” አለው። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ በኢ​ያ​ቡ​ሳ​ዊው በኦ​ርና አው​ድማ አጠ​ገብ ቆሞ ነበረ። 17ዳዊ​ትም ሕዝ​ቡን የሚ​መ​ታ​ውን መል​አክ ባየ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፥ “እነሆ፥ እኔ በድ​ያ​ለሁ፤ ክፉም ሥራ እኔ አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ፤ እነ​ዚህ በጎች ግን ምን አደ​ረጉ? እጅህ በእ​ኔና በአ​ባቴ ቤት ላይ ትሆን ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ” ብሎ ተና​ገ​ረው።
18በዚ​ያም ቀን ጋድ ወደ ዳዊት መጥቶ፥ “ውጣ፤ በኢ​ያ​ቡ​ሳ​ዊው በኦ​ርና አው​ድማ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ሥራ” አለው። 19ዳዊ​ትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘው እንደ ጋድ ነገር ወጣ። 20ኦር​ናም ሲመ​ለ​ከት ንጉ​ሡና ብላ​ቴ​ና​ዎቹ ወደ እርሱ ሲመጡ አየ፤ ኦር​ናም ወጥቶ በን​ጉሡ ፊት በም​ድር ላይ በግ​ን​ባሩ ሰገደ። 21ኦር​ናም፥ “ጌታ​ዬን ንጉ​ሡን ወደ አገ​ል​ጋዩ ያመ​ጣው ምክ​ን​ያት ምን​ድን ነው?” አለ። ዳዊ​ትም፥ “መቅ​ሠ​ፍቱ ከሕ​ዝቡ ላይ ይከ​ለ​ከል ዘንድ አው​ድ​ማ​ውን ከአ​ንተ ገዝቼ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ልሠራ ነው” አለው። 22ኦር​ናም ዳዊ​ትን፥ “ጌታዬ ንጉሡ በፊቱ ደስ ያሰ​ኘ​ውን ወስዶ ያቅ​ርብ፤ እነ​ሆም፥ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በሬ​ዎች፥ ለሚ​ቃ​ጠ​ልም እን​ጨት የአ​ው​ድማ ዕቃና የበሬ ዕቃ አለ። 23ንጉሥ ሆይ፥ ኦርና ይህን ሁሉ ለን​ጉሡ ይሰ​ጣል” አለው፤ ኦር​ናም ንጉ​ሡን፥ “አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይባ​ር​ክህ” አለው። 24ንጉ​ሡም ኦር​ናን፥ “እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን በዋጋ ከአ​ንተ እገ​ዛ​ለሁ፤ ለአ​ም​ላ​ኬም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ያለ ዋጋ አላ​ቀ​ር​ብም” አለው። ዳዊ​ትም አው​ድ​ማ​ው​ንና በሬ​ዎ​ቹን በአ​ምሳ ሰቅል ብር ገዛ። 25በዚ​ያም ዳዊት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ሠራ፤ የሚ​ቃ​ጠ​ልና የሰ​ላም መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንም አቀ​ረበ። ሰሎ​ሞ​ንም በኋላ ዘመን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ጨመረ፤ ያን​ጊዜ አነ​ስ​ተኛ ነበ​ርና።#“ሰሎ​ሞን በኋላ ዘመን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ጨመረ ያን​ጊዜ አነ​ስ​ተኛ ነበ​ርና” የሚ​ለው በዕብ. የለም። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ ሀገ​ሪቱ የተ​ለ​መ​ነ​ውን ሰማ፤ መቅ​ሠ​ፍ​ቱም ከእ​ስ​ራ​ኤል ተከ​ለ​ከለ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ