የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 1 9:13-27

ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 1 9:13-27 አማ2000

የጣ​ዖ​ታቱ ካህ​ናት የጣ​ዖ​ታ​ቱን መባ እን​ደ​ሚ​በሉ አታ​ው​ቁ​ምን? መሠ​ዊ​ያ​ውን የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉም መሥ​ዋ​ዕ​ቱን እን​ደ​ሚ​ካ​ፈሉ አታ​ው​ቁ​ምን? ለቤተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሹሞች መተ​ዳ​ደ​ሪ​ያ​ቸው የቤተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መባ ነው። ጌታ​ች​ንም እን​ዲሁ ወን​ጌ​ልን ለሚ​ያ​ስ​ተ​ምሩ ሰዎች ለሕ​ይ​ወ​ታ​ቸው መተ​ዳ​ደ​ሪያ በዚ​ያው ወን​ጌ​ልን በማ​ስ​ተ​ማር ይሆን ዘንድ አዘዘ። እኔ ግን ይህ​ንም ቢሆን አል​ፈ​ቀ​ድ​ሁ​ትም፤ ይህን የጻ​ፍ​ሁም ይህን እን​ዳ​ገኝ ብዬ አይ​ደ​ለም፤ እኔ ግን ምስ​ጋ​ናዬ ከሚ​ቀ​ር​ብኝ ሞት ይሻ​ለ​ኛል። ወን​ጌ​ልን ባስ​ተ​ም​ርም መመ​ስ​ገን አይ​ገ​ባ​ኝም፤ ታዝዤ አድ​ር​ጌ​ዋ​ለ​ሁና፤ ወን​ጌ​ልን ባላ​ስ​ተ​ምር ደግሞ ወዮ​ልኝ። ይህ​ንስ በፈ​ቃዴ አድ​ር​ጌው ብሆን ዋጋ​ዬን ባገ​ኘሁ ነበር፤ በግድ ከሆነ ግን በተ​ሰ​ጠኝ መጋ​ቢ​ነት አገ​ለ​ገ​ልሁ። እን​ግ​ዲህ ዋጋዬ ምን​ድን ነው? ወን​ጌ​ልን ባስ​ተ​ም​ርም በሹ​መቴ የማ​ገ​ኘው ሳይ​ኖር ወን​ጌ​ልን ያለ ዋጋ እን​ዳ​ስ​ተ​ምር ባደ​ርግ ነው። እኔ ከሁሉ ይልቅ ነጻ ስሆን ብዙ​ዎ​ችን ወደ ሃይ​ማ​ኖት እሰ​በ​ስ​ባ​ቸው ዘንድ እንደ ባሪያ ራሴን ለሁሉ አስ​ገ​ዛሁ። አይ​ሁ​ድን እጠ​ቅ​ማ​ቸው ዘንድ ለአ​ይ​ሁድ እንደ አይ​ሁ​ዳዊ ሆን​ሁ​ላ​ቸው፤ ከኦ​ሪት በታች ያሉ​ትን እጠ​ቅም ዘንድ እኔ ራሴ ከኦ​ሪት በታች ሳል​ሆን ከኦ​ሪት በታች ላሉት ከኦ​ሪት በታች እን​ዳለ ሰው ሆን​ሁ​ላ​ቸው። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ የዘ​ነ​ጋሁ ሳል​ሆን፥ በክ​ር​ስ​ቶስ ሕግም ሳለሁ ሕግ የሌ​ላ​ቸ​ውን እጠ​ቅ​ማ​ቸው ዘንድ ሕግ ለሌ​ላ​ቸው ሕግ እን​ደ​ሌ​ለው ሆን​ሁ​ላ​ቸው። ደካ​ሞ​ች​ንም እጠ​ቅ​ማ​ቸው ዘንድ ለደ​ካ​ሞች እንደ ደካማ ሆን​ሁ​ላ​ቸው፤ በሁሉ መን​ገድ አን​ዳ​ን​ዶ​ቹን አድን ዘንድ ከሁሉ ጋር በሁሉ ነገር እንደ እነ​ርሱ ሆንሁ። በወ​ን​ጌ​ልም ትም​ህ​ርት አን​ድ​ነት ይኖ​ረኝ ዘንድ ስለ ወን​ጌል ትም​ህ​ርት ሁሉን አደ​ር​ጋ​ለሁ። በእ​ሽ​ቅ​ድ​ም​ድም ስፍራ የሚ​ሽ​ቀ​ዳ​ደሙ ሁሉ እን​ደ​ሚ​ፋ​ጠኑ አታ​ው​ቁ​ምን? ለቀ​ደ​መው የሚ​ደ​ረ​ግ​ለት ዋጋ አለ፤ እን​ዲሁ እና​ን​ተም እን​ድ​ታ​ገኙ ፈጽ​ማ​ችሁ ሩጡ። የሚ​ታ​ገል ሁሉ በሁሉ ነገር ይታ​ገ​ሣል፤ እነ​ር​ሱስ የሚ​ጠ​ፋ​ው​ንና የሚ​ያ​ል​ፈ​ውን የም​ስ​ጋ​ና​ቸ​ውን ዋጋ አክ​ሊል ያገኙ ዘንድ ይበ​ረ​ታሉ፤ እኛ ግን የማ​ያ​ል​ፈ​ውን አክ​ሊል ለማ​ግ​ኘት እን​ታ​ገ​ሣ​ለን። እኔ ያለ አሳብ እን​ደ​ሚ​ሮጥ ሁሉ እን​ዲሁ አል​ሮ​ጥም፤ ነፋ​ስ​ንም እን​ደ​ሚ​ጐ​ስም ሁሉ እን​ዲሁ አል​ጋ​ደ​ልም። ነገር ግን ለሌላ ሳስ​ተ​ምር፥ እኔ ለራሴ የተ​ና​ቅሁ እን​ዳ​ል​ሆን ሰው​ነ​ቴን አስ​ጨ​ን​ቃ​ታ​ለሁ፥ ሥጋ​ዬ​ንም አስ​ገ​ዛ​ዋ​ለሁ።