የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 1 8

8
ለጣ​ዖት የተ​ሠ​ዋ​ውን መብ​ላት ስለ​ማ​ይ​ገባ
1ለጣ​ዖ​ታት ስለ​ሚ​ሠዉ መሥ​ዋ​ዕ​ቶች ሁላ​ች​ንም ዕው​ቀት እን​ዳ​ለን እና​ው​ቃ​ለን፤ ዕው​ቀት ያስ​ታ​ብ​ያል፤ ፍቅር ግን ያን​ጻል። 2ዐወ​ቅሁ የሚል ቢኖር፥ ሊያ​ውቅ የሚ​ገ​ባ​ውን ገና አላ​ወ​ቀም። 3እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ወድ ሰው ግን እርሱ በእ​ርሱ ዘንድ በእ​ው​ነት የታ​ወቀ ነው።
4ለጣ​ዖ​ታት የተ​ሠ​ዋ​ውን ስለ​መ​ብ​ላት ግን ጣዖት ሁሉ በዓ​ለም ከንቱ እን​ደ​ሆነ፥ ከአ​ንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በቀር ሌላ አም​ላክ እን​ደ​ሌለ እና​ው​ቃ​ለን። 5አማ​ል​ክት የሚ​ሉ​አ​ቸው ነገ​ሮች አሉና፤ በሰ​ማ​ይም ቢሆን፥ በም​ድ​ርም ቢሆን፥ ብዙ አማ​ል​ክ​ትና ብዙ ጌቶች ቢኖሩ፥ 6ለእ​ኛስ ሁሉ ከእ​ርሱ የሆነ፥ እኛም ለእ​ርሱ የሆን አንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብ አለን፤ ሁሉ በእ​ርሱ የሆነ፥ እኛም በእ​ርሱ የሆን አንድ ጌታ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም አለን። 7ነገር ግን ሁሉ የሚ​ያ​ው​ቀው አይ​ደ​ለም፤ እስከ ዛሬ በጣ​ዖ​ታት ልማድ፥ ለጣ​ዖት የተ​ሠ​ዋ​ውን የሚ​በሉ አሉ፤ ኅሊ​ና​ቸ​ውም ደካማ ስለ​ሆነ ይረ​ክ​ሳል። 8መብል ግን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አያ​ደ​ር​ሰ​ንም፤ ብን​በ​ላም አይ​ረ​ባ​ንም፤ ባን​በ​ላም አይ​ጎ​ዳ​ንም። 9ነገር ግን እና​ን​ተን በማ​የት ሌላው እን​ዳ​ይ​ሰ​ና​ከል#ግሪኩ “ይህ መብ​ላ​ታ​ችሁ ለደ​ካ​ሞች እን​ቅ​ፋት እን​ዳ​ይ​ሆን ...” ይላል። ተጠ​ን​ቀቁ። 10አንተ አማኙ#ግሪኩ “ዕው​ቀት ያለህ” ይላል። በጣ​ዖት ቤት በማ​ዕድ ተቀ​ም​ጠህ ያየህ ቢኖር ያ ልቡ ደካማ የሆነ ሰው ወዲ​ያው ለጣ​ዖት የተ​ሠ​ዋ​ውን ደፍሮ ይበ​ላል። 11ክር​ስ​ቶስ ስለ እርሱ የሞ​ተ​ለት ያ ደካማ ወን​ድም አን​ተን በማ​የት#ግሪኩ “በአ​ንተ ዕው​ቀት” ይላል። ይጎ​ዳል። 12በባ​ል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ችሁ ላይ እን​ዲህ የም​ት​በ​ድሉ ከሆነ ደካማ ሕሊ​ና​ቸ​ው​ንም የም​ታ​ቈ​ስሉ ከሆነ ክር​ስ​ቶ​ስን ትበ​ድ​ላ​ላ​ችሁ። 13ነገር ግን በመ​ብል ምክ​ን​ያት ወን​ድሜ የሚ​ሰ​ና​ከል ከሆነ ወን​ድ​ሜን እን​ዳ​ላ​ሰ​ና​ክል ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሥጋን አል​በ​ላም።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ