የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 1 7:36-40

ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 1 7:36-40 አማ2000

በሸ​መ​ገለ ጊዜ ስለ ድን​ግ​ል​ናው እን​ደ​ሚ​ያ​ፍር የሚ​ያ​ስብ ሰው ቢኖር እን​ዲህ ሊሆን ይገ​ባል፤ የወ​ደ​ደ​ውን ያድ​ርግ፤ ቢያ​ገ​ባም ኀጢ​አት የለ​በ​ትም። በልቡ የቈ​ረ​ጠና ያላ​ወ​ላ​ወለ ግን የወ​ደ​ደ​ውን ሊያ​ደ​ርግ ይች​ላል፤ ግድም አይ​በ​ሉት፤ ድን​ግ​ል​ና​ው​ንም ይጠ​ብቅ ዘንድ በልቡ ቢጸና መል​ካም አደ​ረገ። ድን​ግ​ሊ​ቱን ያገባ መል​ካም አደ​ረገ፤ ያላ​ገባ ግን የም​ት​ሻ​ለ​ውን አደ​ረገ። ሴት ባልዋ በሕ​ይ​ወት ሳለ የታ​ሠ​ረች ናት፤ ባልዋ የሞተ እንደ ሆነ ግን ነጻ ናት፤ የወ​ደ​ደ​ች​ውን ታግባ፤ ነገር ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሁን። በም​ክሬ ጸንታ እን​ዲሁ ብት​ኖር ግን ብፅ​ዕት ናት፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በእኔ ላይ ያለ ይመ​ስ​ለ​ኛል።