ለቅዱሳን ስለሚደረገው አስተዋፅኦ በገላትያ ላሉት ምእመናን እንደ ደነገግሁት እናንተም እንዲሁ አድርጉ። እኔ ስመጣ ይህ የገንዘብ ማዋጣት ያንጊዜ እንዳይሆን፥ ከእናንተ ሰው ሁሉ በየሳምንቱ እሑድ የተቻለውን ያወጣጣ፤ ያገኘውንም በቤቱ ይጠብቅ። በመጣሁ ጊዜም ስጦታችሁን ወደ ኢየሩሳሌም ያደርሱ ዘንድ የመረጣችኋቸውን ሰዎች መልእክቴን ጨምሬ እልካቸዋለሁ። ለመሄድ ቢቻለኝ ግን እኔ ራሴ እሄዳለሁና፥ እነርሱም አብረውኝ ይሄዳሉ። መቄዶንያም ደርሼ ወደ እናንተ እመጣለሁ፤ በመቄዶንያ በኩል አልፋለሁና። እናንተም ወደምሄድበት ትሸኙኝ ዘንድ ምንአልባት የሆነውን ቀን ያህል በእናንተ ዘንድ እቈይ፥ ወይም እከርም ይሆናል። አሁን እግረ መንገዴን ላያችሁ አልሻም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር የፈቀደ እንደ ሆነ የሆነውን ቀን ያህል በእናንተ ዘንድ እንደምቈይ ተስፋ አደርጋለሁ። እስከ በዓለ ኀምሳ በኤፌሶን እቈያለሁ። ሥራ የሞላበት ታላቅ በር ተከፍቶልኛልና፤ ነገር ግን ብዙዎች ተቃዋሚዎች አሉ።
ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 16 ያንብቡ
ያዳምጡ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 16
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 16:1-9
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos