ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 16
16
ለኢየሩሳሌም ምእመናንስለሚደረግ አስተዋፅኦ
1 #
ሮሜ 15፥25-26። ለቅዱሳን ስለሚደረገው አስተዋፅኦ በገላትያ ላሉት ምእመናን እንደ ደነገግሁት እናንተም እንዲሁ አድርጉ። 2እኔ ስመጣ ይህ የገንዘብ ማዋጣት ያንጊዜ እንዳይሆን፥ ከእናንተ ሰው ሁሉ በየሳምንቱ እሑድ የተቻለውን ያወጣጣ፤ ያገኘውንም በቤቱ ይጠብቅ። 3በመጣሁ ጊዜም ስጦታችሁን ወደ ኢየሩሳሌም ያደርሱ ዘንድ የመረጣችኋቸውን ሰዎች መልእክቴን ጨምሬ እልካቸዋለሁ። 4ለመሄድ ቢቻለኝ ግን እኔ ራሴ እሄዳለሁና፥ እነርሱም አብረውኝ ይሄዳሉ። 5#የሐዋ. 19፥21። መቄዶንያም ደርሼ ወደ እናንተ እመጣለሁ፤ በመቄዶንያ በኩል አልፋለሁና። 6እናንተም ወደምሄድበት ትሸኙኝ ዘንድ ምንአልባት የሆነውን ቀን ያህል በእናንተ ዘንድ እቈይ፥ ወይም እከርም ይሆናል። 7አሁን እግረ መንገዴን ላያችሁ አልሻም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር የፈቀደ እንደ ሆነ የሆነውን ቀን ያህል በእናንተ ዘንድ እንደምቈይ ተስፋ አደርጋለሁ። 8#ዘሌ. 23፥15-21፤ ዘዳ. 16፥9-11። እስከ በዓለ ኀምሳ በኤፌሶን እቈያለሁ። 9#የሐዋ. 19፥8-10። ሥራ የሞላበት ታላቅ በር ተከፍቶልኛልና፤ ነገር ግን ብዙዎች ተቃዋሚዎች አሉ።
10 #
1ቆሮ. 4፥17። ጢሞቴዎስም በመጣ ጊዜ በእናንተ ዘንድ ያለ ፍርሀት እንዲኖር ተጠንቀቁ፤ እንደ እኔ የእግዚአብሔርን ሥራ ይሠራልና። 11የሚንቀውም አይኑር፤ ከወንድሞቻችን ጋር እጠብቀዋለሁና፥ ወደ እኔ እንዲመጣ በሰላም ሸኙት።
12ስለ ወንድማችን ስለ አጵሎስም ከወንድሞች ጋር ወደ እናንተ እንዲመጣ መላልሼ ማልጄው ነበር፤ አሁን ሊመጣ አልወደደም፤ በተቻለው ጊዜ ግን ይመጣል። 13ትጉ፤ በሃይማኖትም ቁሙ፤ ታገሡ#ግሪኩ “ጐልምሱ” ይላል። ጽኑ፤ 14ሁሉን በፍቅር አድርጉ። 15#1ቆሮ. 1፥16። ወንድሞቻችን ሆይ፥ የእስጢፋኖስና የፈርዶናጥስ፥ የአካይቆስም#“የፈርዶናጥስና የአካይቆስም ቤተሰቦች” የሚለው በግሪኩ የለም። ቤተሰቦች፥ የአካይያ መጀመሪያዎች እንደ ሆኑ፥ ቅዱሳንንም ለማገልገል ራሳቸውን እንደ ሰጡ ታውቁ ዘንድ እማልዳችኋለሁ። 16እናንተም እንደ እነዚህ ላሉትና ከእኛ ጋር በሥራ ተባብሮ ለሚደክም ሁሉ ትታዘዙላቸው ዘንድ እማልዳችኋለሁ። 17እስጢፋኖስ፥ ፈርዶናጥስና አካይቆስ በመምጣታቸውም ደስ ይለኛል፤ እናንተ ያጐደላችሁትን እነርሱ ፈጽመዋልና። 18እነርሱ መንፈሴንና መንፈሳችሁን ደስ አሰኝተዋል፤ እንዲህ ያሉትንም ዕወቋቸው።
19 #
የሐዋ. 18፥2። በእስያ ያሉ ምእመናን ሰላምታ ያቀርቡላችኋል፤ አቂላና ጵርስቅላ በቤታቸው ከእነርሱ ጋር ያሉ ምእመናንም ሁሉ በጌታችን እጅግ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። 20ወንድሞቻችሁ ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል፤ በተቀደሰች ሰላምታ እርስ በርሳችሁ ሰላም ተባባሉ።
21እኔ ጳውሎስ ይህን ሰላምታ በእጄ ጻፍሁ። 22ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን የማይወደው የተለየ ይሁን፤ ጌታችን ይመጣል። 23የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋራ ይሁን። 24የእኔም ፍቅር በኢየሱስ ክርስቶስ ከእናንተ ጋር ይሁን። አሜን።
በኤፌሶን ተጽፎ በጢሞቴዎስና በእስጢፋኖስ፥ በፈርዶናጥስና በአካይቆስ እጅ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች የተላከው መጀመሪያዉ መልእክት ተፈጸመ።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን። አሜን።
Currently Selected:
ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 16: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ