ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2 1
1
ሰላምታና ምስጋና
1 #
የሐዋ. 18፥1። በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ከሆነ ጳውሎስና ከወንድማችን ጢሞቴዎስ በቆሮንቶስ ሀገር ላለችው የእግዚአሔር ቤተ ክርስቲያንና በአካይያ ሀገር ላሉ ቅዱሳን ሁሉ፥ 2ከአባታችን ከእግዚአብሔርና ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምና ጸጋ ለእናንተ ይሁን።
3የምሕረት አባት፥ የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን። 4እግዚአብሔር በአጽናናን በዚያ መጽናናት በመከራ ያሉትን ሁሉ ማጽናናት እንችል ዘንድ ከመከራችን ሁሉ ያጽናናን እርሱ ይመስገን። 5የክርስቶስ መከራ በእኛ ላይ እንደ በዛ መጠን እንዲሁ መጽናናታችንም በክርስቶስ ይበዛልና። 6መከራ ብንቀበልም እናንተ እንድትድኑና እንድትጽናኑ ነው፤ ብንጽናናም እኛ የተቀበልነውን ያን መከራ በመታገሥ ስለሚደረግ መጽናናታችሁ ነው። 7ስለ እናንተ ያለን ተስፋም የጸና ነው፤ መከራችንን እንደ ተካፈላችሁ መጠን፥ እንዲሁ በመጽናናታችንም እንደምትተባበሩ እናውቃለን።
8 #
1ቆሮ. 15፥3። ወንድሞቻችን ሆይ፥ በእስያ መከራ እንደ ተቀበልን ልታውቁ እወዳለሁ፤ ለሕይወታችን ተስፋ እስክንቈርጥ ድረስ ከዐቅማችን በላይ እጅግ መከራ ጸንቶብን ነበርና። 9ሙታንን በሚያስነሣቸው በእግዚአብሔር እንጂ በራሳችን እንዳንታመን በውስጣችን ለመሞት ቈርጠን ነበር። 10እርሱም እንዲህ ካለ ሞት አዳነን፤ ያድነንማል፤ አሁንም እንደሚያድነን እርሱን እንታመናለን። 11በብዙዎች ጸሎት ጸጋን እናገኝ ዘንድ፥ ብዙዎችም በእኛ ፋንታ ያመሰግኑ ዘንድ እናንተ በጸሎታችሁ ርዱን።
12በእግዚአብሔር ቸርነትና ይቅርታ መመኪያችንና የነፃነታችን ምስክር ይህቺ ናትና፥ በሥጋዊ ጥበብ ሳይሆን፥ በእግዚአብሔር ጸጋ በዚህ ዓለም፥ ይልቁንም በእናንተ ዘንድ ተመላለስን። 13የምታነቡትንና የምታውቁትን ነው እንጂ፥ ሌላ የምንጽፍላችሁ የለምና፥ ይህንም እስከ ፍጻሜ እንደምታስተውሉት ተስፋ አደርጋለሁ። 14እኛ መመኪያችሁ እንደሆን፥ እንዲሁ እናንተም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቀን መመኪያችን እንድትሆኑ በከፊል እንዳወቃችሁ ተስፋ እናደርጋለን።
15በዚህም ታምኜ ጸጋን በዕጥፍ እንድታገኙ በመጀመሪያ ወደ እናንተ እመጣ ዘንድ መከርሁ። 16#የሐዋ. 19፥21። በእናንተም በኩል ወደ መቄዶንያ እንዳልፍ፥ ዳግመኛም ከመቄዶንያ እንድመለስና እናንተም ደግሞ ወደ ይሁዳ ሀገር ትሸኙኝ ዘንድ መከርሁ። 17እንግዲህ ይህን የመከርሁ በውኑ የሠራሁት እንደ አላዋቂ ሰው ሆኜ ነውን? ወይስ በእኔ በኩል አዎን አዎን፥ አይደለም አይደለም ማለት እንዲሆን ያን የምመክረው ለሰው ይምሰል ነውን? 18እግዚአብሔር የታመነ ነው፤ ለእናንተም የሚነገረው ቃላችን እውነትና ሐሰት አልተቀላቀለበትም። 19#የሐዋ. 18፥5። እኛ ማለት እኔ ጳውሎስ፥ ስልዋኖስና ጢሞቴዎስ የሰበክንላችሁ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ እውነትና ሐሰት አይደለም፤ ነገር ግን ስለ እርሱ ያስተማርነው እውነት ነው። 20እግዚአብሔር የሰጠው ተስፋ ሁሉ በክርስቶስ እውነት ሆኖአልና፤ ስለዚህም በእርሱ ለእግዚአብሔር ክብር አሜን እንላለን። 21ከእናንተ ጋር በክርስቶስ ስም የሚያጸናንና የቀባን እግዚአብሔር ነው። 22ደግሞም ያተመንና የመንፈስ ቅዱስን ፈለማ በልቡናችን የሰጠን እርሱ ነው።
23እኔ ለእናንተ በመራራት ወደ ቆሮንቶስ እንዳልመጣሁ፥ ስለ ራሴ እግዚአብሔርን ምስክር አደርገዋለሁ። 24ደስ የሚላችሁን እንድታደርጉ እንረዳችኋለን እንጂ እንድታምኑ ግድ የምንላችሁ አይደለም፤ በእምነት ቆማችኋልና።
Currently Selected:
ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2 1: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ