የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 1 12

12
ከመ​ን​ፈስ ቅዱስ ስለ​ሚ​ገኙ ሀብ​ታት
1ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ስለ መን​ፈስ ቅዱስ ስጦ​ታም ታውቁ ዘንድ እንጂ አላ​ዋ​ቆች ልት​ሆኑ አን​ወ​ድ​ድም። 2ቀድ​ሞም እና​ንተ አሕ​ዛብ በነ​በ​ራ​ችሁ ጊዜ ዲዳ​ዎች ጣዖ​ታ​ትን ታመ​ልኩ እንደ ነበር፥ ጣዖ​ትም በማ​ም​ለክ ረክ​ሳ​ችሁ እንደ ነበር፥#“ጣዖ​ትም በማ​ም​ለክ ረክ​ሳ​ችሁ እንደ ነበረ” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። ወደ ወሰ​ዱ​አ​ች​ሁም ትሄዱ እንደ ነበር ታው​ቃ​ላ​ችሁ። 3ስለ​ዚ​ህም ማንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ሲና​ገር፥ “ኢየ​ሱስ ውጉዝ ነው” የሚል እን​ደ​ሌለ፥ በመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስም ካል​ሆነ በቀር “ኢየ​ሱስ ጌታ ነው” ሊል አን​ድስ እን​ኳን እን​ዳ​ይ​ችል አስ​ታ​ው​ቃ​ች​ኋ​ለሁ።
4መን​ፈስ ቅዱስ አንድ ሲሆን ስጦ​ታው ልዩ ልዩ ነው። 5ጌታም አንድ ሲሆን ልዩ ልዩ አገ​ል​ግ​ሎ​ቶች አሉ። 6ሁሉን በሁሉ የሚ​ያ​ደ​ርግ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አንድ ሲሆን ልዩ ልዩ አሠ​ራር አለ። 7ለሁ​ሉም ጌታ እየ​ረዳ በየ​ዕ​ድሉ እን​ደ​ሚ​ገ​ባ​ውና እን​ደ​ሚ​ጠ​ቅ​መው ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ በግ​ልጥ ይሰ​ጠ​ዋል፤ 8በመ​ን​ፈስ ቅዱስ የጥ​በብ ቃል የሚ​ሰ​ጠው አለ፤ በመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስም የዕ​ው​ቀት ቃል የሚ​ሰ​ጠው አለ። 9ለአ​ን​ዱም በዚ​ያው መን​ፈስ እም​ነት፥ ለአ​ን​ዱም በአ​ንዱ መን​ፈስ የመ​ፈ​ወስ ስጦታ፥ 10ለአ​ን​ዱም ተአ​ም​ራ​ትን ማድ​ረግ፥ ለአ​ን​ዱም ትን​ቢ​ትን መና​ገር፥ ለአ​ን​ዱም መና​ፍ​ስ​ትን መለ​የት፥ ለአ​ን​ዱም በልዩ ዓይ​ነት ልሳን መና​ገር፥ ለአ​ን​ዱም በል​ሳ​ኖች የተ​ነ​ገ​ረ​ውን መተ​ር​ጐም ይሰ​ጠ​ዋል። 11#ሮሜ 12፥6-8። በዚ​ህም ሁሉ ያው አንዱ መን​ፈስ ቅዱስ ሁሉን ይረ​ዳል፤ ለሁ​ሉም እንደ ወደደ ያድ​ላ​ቸ​ዋል።
12 # ሮሜ 12፥4-5። አካል አንድ እንደ ሆነ ብዙ የአ​ካል ክፍ​ሎ​ችም እንደ አሉ​በት፥ ነገር ግን የአ​ካል ክፍ​ሎች ሁሉ ብዙ​ዎች ሳሉ አንድ አካል እንደ ሆኑ ክር​ስ​ቶስ ደግሞ እን​ዲሁ ነው፤ 13እኛ ሁላ​ች​ንም በአ​ንድ መን​ፈስ አንድ አካል ለመ​ሆን ተጠ​ም​ቀ​ናል፤ አይ​ሁድ ብን​ሆን፥ አረ​ማ​ው​ያ​ንም ብን​ሆን፥ ባሪ​ያ​ዎ​ችም ብን​ሆን፥ ነጻ​ዎ​ችም ብን​ሆን ሁላ​ችን አንድ መን​ፈስ ጠጥ​ተ​ና​ልና። 14የአ​ካ​ላ​ች​ንም ክፍሉ ብዙ ነው እንጂ አንድ አይ​ደ​ለም። 15እግ​ርም፥ “እኔ እጅ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምና የአ​ካል ክፍል አይ​ደ​ለ​ሁም” ብትል ይህን በማ​ለቷ የአ​ካል ክፍል መሆ​ንዋ ይቀ​ራ​ልን? 16ጆሮም፥ “እኔ ዐይን አይ​ደ​ለ​ሁ​ምና የአ​ካል ክፍል አይ​ደ​ለ​ሁም” ብትል ይህን በማ​ለቷ የአ​ካል ክፍል መሆ​ንዋ ይቀ​ራ​ልን? 17አካል ሁሉ ዐይን ቢሆን ኖሮ መስ​ማት ከየት በተ​ገኘ ነበር፤ አካ​ልስ ሁሉ ጆሮ ቢሆን ኖሮ ማሽ​ተት ከየት በተ​ገኘ ነበር? 18አሁን ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ካ​ላ​ች​ንን ክፍል በሰ​ው​ነ​ታ​ችን ውስጥ እርሱ እንደ ወደደ እየ​ራሱ አከ​ና​ውኖ መደ​በው። 19የአ​ካል ክፍሉ አንድ ቢሆን ኖሮ አካል የት በተ​ገኘ ነበር? 20አሁ​ንም የአ​ካል ክፍ​ሎች ብዙ​ዎች ናቸው ፤ አካሉ ግን አንድ ነው። 21ዐይን እጅን፥ “አል​ፈ​ል​ግ​ሽም” ልት​ላት አት​ች​ልም፤ ራስም፥ “እግ​ሮ​ችን አል​ፈ​ል​ጋ​ች​ሁም” ልት​ላ​ቸው አት​ች​ልም። 22ደካ​ሞች የሚ​መ​ስ​ሉህ የአ​ካል ክፍ​ሎች ይል​ቁን የሚ​ያ​ስ​ፈ​ል​ጉህ ናቸው። 23ከአ​ካ​ልም ክፍ​ሎች የተ​ናቁ ለሚ​መ​ስ​ሉን ክብ​ርን እን​ጨ​ም​ር​ላ​ቸ​ዋ​ለን፤ ለም​ና​ፍ​ር​ባ​ቸ​ውም የአ​ካል ክፍ​ሎች ክብር ይጨ​መ​ር​ላ​ቸ​ዋል። 24ለከ​በ​ረው የአ​ካ​ላ​ችን ክፍል ክብ​ርን አን​ሻ​ለ​ትም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ሰው​ነ​ታ​ች​ንን አስ​ማ​ም​ቶ​ታል፤ ይል​ቁ​ንም ታና​ሹን የአ​ካል ክፍል አክ​ብ​ሮ​ታል። 25የአ​ካ​ላ​ችን ክፍ​ሎች እርስ በር​ሳ​ቸው እን​ዳ​ይ​ለ​ያዩ፥ አካ​ላ​ችን ሳይ​ነ​ጣ​ጠል በክ​ብር እን​ዲ​ተ​ካ​ከል አስ​ማ​ማው። 26አንዱ የአ​ካል ክፍል ቢታ​መም ከእ​ርሱ ጋር የአ​ካል ክፍ​ሎች ሁሉ ይታ​መ​ማሉ፤ አንዱ የአ​ካል ክፍል ደስ ቢለ​ውም#በግ​ሪኩ “ቢከ​ብ​ርም” ይላል። የአ​ካል ክፍ​ሎች ሁሉ ከእ​ርሱ ጋር ደስ ይላ​ቸ​ዋል። 27እን​ግ​ዲህ እና​ንተ የክ​ር​ስ​ቶስ አካሉ ናችሁ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ች​ሁም የአ​ካሉ ክፍ​ሎች ናችሁ። 28#ኤፌ. 4፥11። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን የሾ​ማ​ቸው አስ​ቀ​ድሞ ሐዋ​ር​ያ​ትን፥ ሁለ​ተ​ኛም ነቢ​ያ​ትን፥ ሦስ​ተ​ኛም መም​ህ​ራ​ንን፥ ከዚ​ህም በኋላ ተአ​ም​ራ​ትና ኀይል ማድ​ረግ የተ​ሰ​ጣ​ቸ​ውን፥ ቀጥ​ሎም የመ​ፈ​ወስ ሀብት የተ​ሰ​ጣ​ቸ​ውን፥ የመ​ር​ዳ​ትም ሀብት የተ​ሰ​ጣ​ቸ​ውን፥ የመ​ም​ራ​ትና ቋን​ቋን የመ​ና​ገር ሀብት የተ​ሰ​ጣ​ቸ​ውን ነው። 29በውኑ ሁሉ ሐዋ​ር​ያ​ትን ይሆ​ና​ሉን? ሁሉስ ነቢ​ያ​ትን ይሆ​ና​ሉን? ሁሉስ መም​ህ​ራ​ንን ይሆ​ና​ሉን? ለሁ​ሉስ ተአ​ም​ራ​ትን የማ​ድ​ረግ ኀይል ይሰ​ጣ​ልን? 30ለሁ​ሉስ የመ​ፈ​ወስ ሀብት ይሰ​ጣ​ልን? ሁሉስ በቋ​ንቋ ይና​ገ​ራ​ሉን? ሁሉስ ይተ​ረ​ጕ​ማ​ሉን? 31ነገር ግን ለም​ት​በ​ል​ጠው ጸጋ ቅኑ፤ ደግ​ሞም የም​ት​ሻ​ለ​ውን መን​ገድ አስ​ተ​ም​ራ​ች​ኋ​ለሁ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ