እኔ ክርስቶስን እንደምመስለው እኔን ምሰሉ። ወንድሞች ሆይ፥ አመሰግናችኋለሁ፤ ዘወትር ታስቡኛላችሁና፤ ያስተማርኋችሁንም ትምህርት ጠብቃችኋልና። ነገር ግን የወንድ ሁሉ ራሱ ክርስቶስ፥ የሴትም ራስዋ ወንድ፤ የክርስቶስም ራሱ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ልታውቁ እወድዳለሁ። ራሱን ተከናንቦ የሚጸልይ ወይም የሚያስተምር ወንድ ሁሉ ራሱን ያዋርዳል። ራስዋን ሳትከናነብ የምትጸልይ ወይም የምታስተምር ሴት ሁላ ራስዋን ታዋርዳለች፤ ራስዋን እንደ ተላጨች መሆንዋ ነውና። ሴት ካልተከናነበች ትላጭ ወይም ጠጕርዋን ትቈረጥ፤ ለሴት ጠጕርዋን መቈረጥ ወይም መላጨት ውርደት ከሆነ ትከናነብ። ወንድ በሚጸልይበት ጊዜ ሊከናነብ አይገባውም፤ የእግዚአብሔር አርአያውና አምሳሉ ነውና፤ ሴትም ለባልዋ ክብር ናት። ሴት ከወንድ ተገኝታለችና፤ ወንድ ግን ከሴት የተገኘ አይደለም። ወንድ ስለ ሴት አልተፈጠረም፤ ሴት ስለ ወንድ ተፈጠረች እንጂ። ስለዚህም ሴት ስለ መላእክት፥ ሥልጣን ለራስዋ ሊሆን ይገባል፤ ነገር ግን አሁን ሴት ከባሏ አትለይ፤ ወንድም ከሚስቱ አይለይ፤ ሁላችሁም በጌታችን ኑሩ። ሴት ከወንድ እንደ ተገኘች እንዲሁ ወንድ ከሴት ተገኘ፤ ነገር ግን ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው። እስኪ እናንተ ራሳችሁ ፍረዱ፤ ሴት ወደ እግዚአብሔር በምትጸልይበት ጊዜ ልትከናነብ አይገባምን? ተፈጥሮዋስ አያስረዳችሁምን? ወንድ ግን ጠጕሩን ቢያሳድግ ነውር ነው። ለሴት ግን ጠጕርዋን ብታሳድግ ክብርዋ ነው፤ ለሴት ጠጕርዋ እንደ ቀጸላ ሆኖ ተሰጥቶአታልና። ነገር ግን የሚጠራጠር ቢኖር እኛ ወይም የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን እንዲህ ያለ ልማድ የለንም።
ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 11 ያንብቡ
ያዳምጡ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 11
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 11:1-16
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos