የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ቲቶ መግቢያ

መግቢያ
ቲቶ ወደ ክርስትና እምነት ከመጣ በኋላ ጳውሎስን በወንጌል ተልእኮው በቅርብ የሚረዳ ሰው ነበር። ጳውሎስ ይህን መልእክት የጻፈው በዕድሜ አነስተኛ ለሆነው ለዚሁ ለሥራ ባልደረባው ነው። ቲቶ በዚያን ጊዜ የቤተ ክርስቲያንን ሥራ በመቈጣጠር በቀርጤስ ይገኝ ነበር። መልእክቱ የሚያተኲረው በሦስት ዋና ዋና ነገሮች ላይ ነው፦
አንደኛ፥ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ለሥነ ምግባር ሊሰጡት የሚገባውን ትኩረት ማሳሰብ ነው፤ በተለይ በቀርጤስ ተከስቶ ለነበረው የሥነ ምግባር ብሉሽነት ወቅታዊ የሆነ መልእክት የማስተላለፍ ዓላማ ነበረው። ሁለተኛ፥ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚገኙትን የተለያዩ ቡድኖች ማለትም በዕድሜ የገፉ ወንዶችንና ሴቶችን፥ እንዲሁም ወጣቶች ወንዶችንና አገልጋዮችን እንዴት ማስተማር እንደሚገባው ቲቶን ለመምከር ነው። በመጨረሻም ስለ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር በተለይም በሰላምና በወዳጅነት ስለ መኖር፥ እንዲሁም ከቤተ ክርስቲያን ውስጥ ጥላቻን፥ ክርክርንና መለያየትን ስለ ማስወገድ፥ ለቲቶ ምክርና መመሪያ ለመስጠት ነው።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
መግቢያ (1፥1-4)
የቤተ ክርስቲያን መሪዎች (1፥5-16)
በቤተ ክርስቲያን የተለያዩ ቡድኖች የሥራ ድርሻ (2፥1-15)
ምክርና ማስጠንቀቂያ (3፥1-11)
ማጠቃለያ (3፥12-15)
ምዕራፍ

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ