2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 4
4
1በእግዚአብሔር ፊት፥ በሕያዋንና በሙታንም ላይ በሚፈርደው በጌታ በክርስቶስ ኢየሱስ ፊት፥ በመገለጡና በመንግሥቱም አጥብቄ አዝዝሃለሁ፤ 2ቃሉን ስበክ፤ ጊዜው ቢመችም ባይመችም ተግተህ ሥራ፤ ፈጽመህ እየታገሥህና እያስተማርህ ዝለፍና ገሥጽ፤ ምከርም። 3ሰዎች እውነተኛውን ትምህርት የማይታገሱበት፤ ይልቁንም ጆሮዎቻቸውን የሚኮረኩራቸውን ነገር በመሻት ለራሳቸው ምኞት የሚመቹ አስተማሪዎችን የሚሰበስቡበት ጊዜ ይመጣልና።
ጳውሎስ የጽድቅን አክሊል ለመቀዳጀት ተስፋ እንዳደረገ
4ከቶም እውነትን ከመስማት ጆሮዎቻቸውን ይመልሳሉ፤ መንገድንም ስተው ወደ ተረት ፈቀቅ ይላሉ። 5አንተ ግን ነገርን ሁሉ በልክ አድርግ፤ መከራን በትዕግስት ተቀበል፤ የወንጌል ሰባኪነትን ሥራ አከናውን፤ አገልግሎትህን ሙሉ ለሙሉ ፈጽም።
6እንደ መጠጥ ቁርባን በመፍሰስ እኔም መሥዋዕት የምሆንበት ጊዜ አሁን ደርሶአል፤ የምሄድበትም ጊዜ ቀርቡዋል። 7መልካሙን ውጊያ ተዋግቻለሁ፤ የሩጫውን ውድድር ጨርሼአለሁ፤ እምነትን ጠብቄአለሁ፤ 8ከእንግዲህም ወዲህ ጻድቅ ፈራጅ የሆነ ጌታ በዚያ ቀን ሊሸልመኝ የጽድቅ አክሊል አዘጋጅቶ ይጠብቀኛል፤ ደግሞም ለእኔ ብቻ ሳይሆን መገለጡን በፍቅር ለናፈቁት ሁሉ ነው።
ስለ ግል ጉዳዮች
9በቶሎ ወደ እኔ እንድትመጣ የተቻለህን ሁሉ ጣር፤ 10#ቈላ. 4፥14፤ ፊልሞ. 1፥24፤ 2ቆሮ. 8፥23፤ ገላ. 2፥3፤ ቲቶ 1፥4።ዴማስ የአሁንዋን ይህችን ዓለም ወድዶ ትቶኛል፤ ወደ ተሰሎንቄም ሄዶአል። ቀርቂስም ወደ ገላትያ ቲቶም ወደ ድልማጥያ ሄደዋል። 11#ቈላ. 4፥14፤ ፊልሞ. 1፥24፤ የሐዋ. 12፥12፤25፤ 13፥13፤ 15፥37-39፤ ቈላ. 4፥10፤ ፊልሞ. 1፥24።ከእኔ ጋር ያለው ሉቃስ ብቻ ነው፤ ማርቆስን ከአንተ ጋር ይዘኸው ና፥ ለአገልግሎት ብዙ ይጠቅመኛልና። 12#የሐዋ. 20፥4፤ ኤፌ. 6፥21፤22፤ ቈላ. 4፥7፤8።ቲኪቆስን ግን ወደ ኤፌሶን ላክሁት። 13#የሐዋ. 20፥6።ስትመጣ በጢሮአዳ ከአክርጳ ዘንድ የተውሁትን በርኖሱን እንዲሁም መጻሕፍቱን በተለይም በብራና የተጻፉትን አምጣልኝ። 14#1ጢሞ. 1፥20፤ መዝ. 62፥12፤ ሮሜ 2፥6።የናስ አንጥረኛው እስክንድሮስ ብዙ ክፉ ነገሮችን አድርጎብኛል፤ ጌታ እንደ ሥራው ብድራቱን ይከፍለዋል። 15አንተም ደግሞ ከእርሱ ነቅተህ ራስህን ጠብቅ፤ የምንናገረውን እጅግ ተቃውሞአልና። 16በመጀመሪያው ሙግቴ አንድም ሰው እንኳ ከጎኔ አልቆመም፤ ሁሉም ግን ከዱኝ፤ ይህንንም በደል በእነርሱ ላይ አይቁጠርባቸው፤ 17ዳሩ ግን የስብከቱ ሥራ በእኔ እንዲፈጸም አሕዛብም ሁሉ እንዲሰሙት፥ ከእኔ ጎን ጌታ ቆመ አበረታኝም፤ ከአንበሳም አፍ ዳንሁ። 18ጌታም ከክፉ ነገር ሁሉ ያድነኛል፤ እርሱም ለሰማያዊው መንግሥቱ እንድሆን ይጠብቀኛል፤ ለእርሱ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ክብር ይሁን፤ አሜን።
የመጨረሻ ሰላምታ
19 #
የሐዋ. 18፥2፤ 2ጢሞ. 1፥16፤17። ለጵርስቅላና ለአቂላ ለሄኔሲፎሩም ቤተሰቦች ሰላምታ አቅርብልኝ። 20#የሐዋ. 19፥22፤ ሮሜ 16፥23፤ የሐዋ. 20፥4፤ 21፥29።ኤርስጦስ በቆሮንቶስ ቀረ፤ ጥሮፊሞስን ግን ታሞ በሚሊጢን ተውኩት። 21ከክረምት በፊት እንድትመጣ የተቻለህን ሁሉ ጣር። ኤውግሎስና ጱዴስ ሊኖስም ቅላውዲያም ወንድሞችም ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡልሃል።
22ጌታ ከመንፈስህ ጋር ይሁን። ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን፤ አሜን።
Currently Selected:
2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 4: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ