መኃልየ መኃልይ መግቢያ
መግቢያ
መኃልየ መኃልይ የፍቅር ቅኔዎች ስብስብ ነው። ስለ ጾታ መልካምነት፥ የጾታዊ ፍቅርን ዐቢይነትና የዐቢይነትን ጣራ ያሳያል። ግጥሞቹ በምልልስ መልክ ሲቀርቡ፥ የመፈላለግ፥ የመነፋፈቅ፥ የመደናነቅ ጉዞ ነው የሚያሳዩት። አይሁድና ክርስቲያኖች መኃልየ መኃልይ ከጾታዊ ፍቅር ባሻገር የሚከበር ምሥጢር እንዳለው ያስተምራሉ። ምሳሌያዊ ትርጉሞችንም ይሰጣሉ። አይሁድ በዚህ ማኅሌት አማካይነት በእግዚአብሔርና በእስራኤል ሕዝብ መከከል ስለነበረውና ስላለው የፍቅር ታሪክ ያስተምራሉ። (ኢሳ 5፥1-7፤ 54፥4-8፤ 62፥5፤ ኤር. 2፥2፤ 3፤ 32፤ ሕዝ. 16፤ 23፤ ሆሴ. 1-3 ተመልከቱ።)
በነቢያት መጻሕፍት ውስጥ አፍቃሪና ታማኝ ለሆነው እግዚአብሔር ሕዝቡ ተገቢ ያልሆነ ምላሽ መስጠቱን የሚገልጹ ምሳሌዎች ይገኛሉ። መኃልየ መኃልይ ግን ስለ መልካም ግንኙነትና ስለ ፍቅር ያስተምራል። ይህ ሐሳብ በኢሳ. 62፥3-5 ላይም ይገኛል።
ክርስቲያኖች ደግሞ ይህ ማኅሌት ክርስቶስ ስለ ቤተ ክርስቲያን ያለውን ፍቅር ያስተምራል ይላሉ። ይህ ሐሳብ በማቴዎስ 9፥15 ላይ ይገኛል። ኢየሱስም እንዲህ አላቸው “ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉን? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፤ በዚያ ጊዜም ይጾማሉ።” በማቴዎስ 25፥1-13 የእግዚአብሔር መንግሥት በሙላት መምጣት በሰርግ ምሳሌ ተተርኳል። ዮሐ. 3፥29፤ ኤፌ. 5፥23-32፤ ራእ. 19፥7-9፤ 21፥9-11 ተመልከቱ።
ምዕራፍ
Currently Selected:
መኃልየ መኃልይ መግቢያ: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ