መኃልየ መኃልይ 1
1
1ከመዝሙር ሁሉ የሚበልጥ የሰሎሞን መዝሙር።
2በአፉ መሳም ይሳመኝ፥
ፍቅርህ ከወይን ጠጅ ይልቅ መልካም ነውና።
3ዘይትህ መልካም መዓዛ አለው፥
ስምህ እንደሚፈስስ ዘይት ነው፥
ስለዚህ ደናግል ወደዱህ።
4ሳበኝ፥ ከአንተም በኋላ እንሮጣለን፥
ንጉሥ ወደ ቤቱ አገባኝ፥
በአንተ ደስ ይለናል፥ ሐሤትም እናደርጋለን፥
ከወይን ጠጅ ይልቅ ፍቅርህን እናስባለን፥
በቅንነት ይወድዱሃል።
5እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ እኔ ጥቁር ነኝ፥
ውብም ነኝ፥ እንደ ቄዳር ድንኳኖች እንደ ሰሎሞንም መጋረጃዎች።
6ፀሐይ መልኬን አክስሎታልና
ጥቁር ስለ ሆንኩ አትዩኝ፥
የእናቴ ልጆች ተጣሉኝ፥
የወይን ቦታዎችንም ጠባቂ አደረጉኝ፥
ነገር ግን የእኔን ወይን ቦታ አልጠበቅሁም።
7ነፍሴ የወደደችህ አንተ ንገረኝ፥
ወዴት ታሰማራለህ? በቀትርስ ጊዜ ወዴት ትመስጋለህ?
ስለ ምንስ ከባልንጀሮችህ መንጎች በኋላ እቅበዘበዛለሁ?
8አንቺ በሴቶች ዘንድ የተዋብሽ ሆይ፥
ያላወቅሽ እንደሆነ የመንጎችን ፍለጋ ተከትለሽ ውጪ፥
የፍየል ግልገሎችሽንም በእረኞች ድንኳኖች አጠገብ አሰማሪ።
9ወዳጄ ሆይ፥ በፈርዖን ሰረገሎች እንዳለ ፈረስ መሰልሁሽ።
10የጉንጭሽ ውበት በከበረ ሉል፥
አንገትሽም በዕንቁ ድሪ ያማረ ነው።
11ባለ ብር ጉብጉብ የሆነ የወርቅ ጠልሰም እናደርግልሻለን።
12ንጉሡ በማዕዱ ሳለ፥
የእኔ ናርዶስ መዓዛውን ሰጠ።
13ውዴ ለእኔ በጡቶቼ መካከል እንደሚያርፍ
እንደ ተቋጠረ ከርቤ ነው።
14ውዴ ለእኔ በዓይንጋዲ ወይን ቦታ እንዳለ
እንደ አበባ እቅፍ ነው።
15ወዳጄ ሆይ፥ እነሆ፥ ውብ ነሽ፥
እነሆ፥ አንቺ ውብ ነሽ፥
ዐይኖችሽም እርግቦች ናቸው።
16ውዴ ሆይ፥ እነሆ፥ አንተ ውብ ነህ፥
መልከ መልካምም ነህ፥
አልጋችንም ለምለም ነው።
17የቤታችን ሠረገላ የዝግባ ዛፍ ነው፥
የጣሪያችንም ማዋቀሪያ የጥድ ዛፍ ነው።
Currently Selected:
መኃልየ መኃልይ 1: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ