መዝሙረ ዳዊት 89:38-52

መዝሙረ ዳዊት 89:38-52 መቅካእኤ

ለዘለዓለም እንደ ጨረቃ ይጸናል፥ ምስክርነቱ በደመና የታመነ ነው። አንተ ግን ናቅኸው ጣልኸውም፥ በቀባኸውም ላይ በቁጣ ተነሣህ። የአገልጋይህን ኪዳን አፈረስህ፥ ዘውዱንም በምድር አረከስህ። ቅጥሩን ሁሉ አፈራረስህ፥ አምባዎቹንም አጠፋህ። መንገድ አላፊም ሁሉ ዘረፈው፥ ለጎረቤቶቹም ስድብ ሆነ። የተቃዋሚዎቹን ቀኝ ከፍ ከፍ አደረግህ፥ ጠላቶቹንም ሁሉ ደስ አሰኘህ። የሰይፉንም ረድኤት መለስህ፥ በጦርነትም ውስጥ አልደገፍኸውም። በትረ መንግሥትን ሻርህ፥ ዙፋኑንም በምድር ላይ ጣልህ። ዕድሜውንም አሳጠርህ፥ በእፍረትም ሸፈንኸው። አቤቱ፥ እስከ መቼ ለዘለዓለም ፊትህን ትሰውራለህ? እስከ መቼስ ቁጣህ እንደ እሳት ይነድዳል? ጊዜዬ ምን ያህል ውስን መሆኑን አስታውስ፥ በውኑ የሰውን ልጅ ሁሉ ለከንቱ ፈጠርኸውን? ሕያው ሆኖ የሚኖር፥ ሞትንስ የማያይ ማን ነው? ነፍሱንስ ከሲኦል እጅ የሚያድን ማን ነው? ለዳዊት በእውነት የማልህ፥ አቤቱ፥ የቀድሞ ጽኑ ፍቅርህ ወዴት ነው? አቤቱ፥ የአገልጋዮችህን ስድብ፥ በእቅፌ ብዙ አሕዛብን የተቀበልሁትን፥ አቤቱ፥ ጠላቶችህን የሰደቡትን አንተ የቀባኸውን የሰደቡትን አስታውስ።