አሁን ግን ናቅኸው፤ ጣልኸውም፤ የቀባኸውንም እጅግ ተቈጣኸው። ከባሪያህ ጋራ የገባኸውን ኪዳን አፈረስህ፤ የክብር ዘውዱን ትቢያ ላይ ጥለህ አቃለልኸው። ቅጥሩን ሁሉ አፈራረስህ፤ ምሽጉንም ደመሰስህ። ዐላፊ አግዳሚው ሁሉ ዘረፈው፤ ለጎረቤቶቹ መዘባበቻ ሆነ። የጠላቶቹን ቀኝ እጅ ከፍ ከፍ አደረግህ፤ ባላንጣዎቹም ሁሉ ደስ አላቸው። የሰይፉን ስለት አጠፍህ፤ በጦርነትም ጊዜ አልረዳኸውም። ግርማዊነቱን አጠፋህበት፤ ዙፋኑንም ከዐፈር ደባለቅኸው። የወጣትነት ዘመኑን አሳጠርኸው፤ ዕፍረትንም አከናነብኸው። ሴላ እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህ እስከ መቼ ይሆናል? ራስህንስ ለዘላለም ትሰውራለህን? ቍጣህስ እንደ እሳት የሚነድደው እስከ መቼ ነው? ዘመኔ ምን ያህል ዐጭር እንደ ሆነች ዐስብ፤ የሰውን ልጆች እንዲያው ለከንቱ ፈጠርሃቸው! ሞትን ሳያይ ሕያው ሆኖ የሚቀር ሰው አለን? ራሱን ከሲኦል እጅ ማዳን የሚችል ማን ነው? ሴላ ጌታ ሆይ፤ ለዳዊት በታማኝነትህ የማልህለት፣ የቀድሞው ምሕረትህ የት አለ? ጌታ ሆይ፤ ባሪያህ እንዴት እንደ ተፌዘበት፣ የብዙ ሰዎችንም ነቀፋ እንደ ታቀፍሁ ዐስብ። እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላቶችህ የተሣለቁበትን፣ የቀባኸውን ሰው ርምጃ የነቀፉበትን ሁኔታ ዐስብ። እግዚአብሔር ለዘላለም ይባረክ፤ አሜን፤ አሜን።
መዝሙር 89 ያንብቡ
ያዳምጡ መዝሙር 89
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መዝሙር 89:38-52
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች