መዝሙረ ዳዊት 88
88
1የቆሬ ልጆች የምስጋና መዝሙር። ለመዘምራን አለቃ በማኸላት ለመዘመር፥ የይዝራኤላዊው የኤማን ትምህርት።
2 #
መዝ. 77፥3። አቤቱ፥ የመድኃኒቴ አምላክ፥
በቀንና በሌሊት በፊትህ ጮኽሁ፥
3 #
መዝ. 119፥170። ጸሎቴ ወደ ፊትህ ትግባ፥
ጆሮህንም ወደ ጩኸቴ አዘንብል፥
4 #
መዝ. 28፥1፤ 30፥4፤ 40፥3፤ 86፥13፤ 143፥7፤ ዘኍ. 16፥33፤ ኢዮብ 17፥1፤ ዮናስ 2፥7። ነፍሴ መከራን ጠግባለችና፥
ሕይወቴም ወደ ሲኦል ቀርባለችና።
5ወደ ጉድጓድ ከሚወርዱ ጋር ተቈጠርሁ፥
ረዳትም እንደሌለው ሰው ሆንሁ።
6ለዘለዓለም እንደማታስባቸው፥
እንደ ተገደሉና በመቃብር ውስጥ እንደ ተጣሉ፥
በሙታን ውስጥ እንዳሉ የተጣልሁ ሆንሁ፥
እነርሱም ከእጅህ ተለዩ።
7በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ፥
በታችኛው ጉድጓድ አስቀመጥኸኝ።
8 #
መዝ. 18፥5፤ 32፥6፤ 42፥8፤ 69፥2፤ ዮናስ 2፥4። በእኔ ላይ ቁጣህ ጸና፥
ማዕበልህንም#88፥8 የቁጣ ሁሉ በእኔ ላይ አመጣህ።
9 #
መዝ. 38፥12፤ 79፥4፤ 80፥7፤ 123፥3-4፤ 142፥8፤ ኢዮብ 12፥4፤ 19፥13፤ ሰቆ.ኤ. 3፥7፤ ዳን. 9፥16። የሚያውቁኝን ከእኔ አራቅህ፥
በእነርሱ ዘንድ አጸያፊ አደረግኸኝ፥
ተዘግቶብኛል፥ መውጫም የለኝም።
10ዐይኖቼም በመከራ ፈዘዙ፥
አቤቱ፥ ሁልጊዜ ወደ አንተ ጮኽሁ፥
እጆቼንም ወደ አንተ ዘረጋሁ።
11 #
መዝ. 6፥6፤ 30፥10፤ 38፥18፤ 115፥17። በውኑ ለሙታን ድንቅ ነገሮችን ታደርጋለህን?
ጥላዎችስ#88፥11 የሞቱ ሰዎች ተነሥተው ያመሰግኑሃልን?
12በመቃብርስ ውስጥ ጽኑ ፍቅርህን፥
እውነትህንስ በጥፋት ስፍራ ይነገራሉን?
13ድንቅ ሥራህ በጨለማ፥
ጽድቅህም በሚረሳበት ምድር ትታወቃለችን?
14አቤቱ፥ እኔ ግን ወደ አንተ ጮኽሁ፥
በጥዋት ጸሎቴ ወደ ፊትህ ትደርሳለች።
15አቤቱ፥ ነፍሴን ለምን ትጥላለህ?
ፊትህንስ ከእኔ ለምን ትሰውራለህ?
16እኔ ከታናሽነቴ ችግረኛ ለሞትም የቀረብሁ ነኝ፥
በአስደንጋጭ ነገሮችህ ተሰቃየሁ፤ ምንም አቅም የለኝም።
17 #
ኢዮብ 6፥4፤ 20፥25። ቁጣህ በላዬ አለፈ፥
አስፈሪ ድርጊቶችህ አደቀቁኝ።
18ሁልጊዜ እንደ ውኃ ከበቡኝ፥
በአንድ ላይም አጥለቀለቁኝ።
19 #
ኢዮብ 19፥13። ወዳጄንና ባልንጀራዬን ከእኔ አራቅህ፤
ጨለማም ዘመዴ ሆነ።#88፥19 ዘመዶቼም ራቁኝ፤ ብቻዬን ቀረሁኝ
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 88: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ