መዝሙረ ዳዊት 86
86
1የዳዊት ጸሎት
አቤቱ፥ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል አድምጠኝም፥
ደሃና ችግረኛ ነኝና።
2ታማኝ ነኝና ነፍሴን ጠብቅ፥
አምላኬ ሆይ፥ በአንተ የታመነውን አገልጋይህን አድነው።
3አቤቱ፥ ቀኑን ሁሉ ወደ አንተ እጮኻለሁና ማረኝ።
4 #
መዝ. 25፥1፤ 143፥8። የአገልጋይህን ነፍስ ደስ አሰኛት፥
አቤቱ፥ ነፍሴን ወደ አንተ አነሣለሁና።
5 #
ኢዩ. 2፥13። አቤቱ፥ አንተ መልካምና ይቅር ባይ ነህና፥
ጽኑ ፍቅርህም ለሚጠሩህ ሁሉ ብዙ ነውና።
6 #
መዝ. 5፥2፤ 130፥1-2። አቤቱ፥ ጸሎቴን አድምጥ፥
የልመናዬንም ድምፅ ስማ።
7ትመልስልኛለህና በመከራዬ ቀን ወደ አንተ እጠራለሁ።
8 #
መዝ. 35፥10፤ 89፥9፤ ዘፀ. 15፥11፤ ዘዳ. 3፥24፤ ኤር. 10፥6። አቤቱ፥ ከአማልክት የሚመስልህ የለም፥
ሥራህንም የሚመስል የለም።
9 #
መዝ. 22፥28፤ ዘካ. 14፥16፤ ራእ. 15፥4። ያደረግሃቸው አሕዛብ ሁሉ ይመጣሉ፥
አቤቱ፥ በፊትህም ይሰግዳሉ፥
ስምህንም ያከብራሉ፥
10አቤቱ፥ ድንቅ የምታደርግ አንተ ታላቅ ነህና፥
አንተም ብቻህን ታላቅ አምላክ ነህና።
11 #
መዝ. 25፥4፤ 26፥3፤ 27፥11፤ 119፥12፤35፤ 143፥8፤ 10። አቤቱ፥ መንገድህን ምራኝ፥
በእውነትህም እሄዳለሁ፥
ስምህን ለመፍራት ልቤ ደስ ይለዋል።
12አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ በልቤ ሁሉ አመሰግንሃለሁ፥
ለዘለዓለምም ስምህን አከብራለሁ፥
13 #
መዝ. 30፥4፤ 40፥3፤ ዮናስ 2፥7። ጽኑ ፍቅርህ በእኔ ላይ ታላቅ ናትና፥
ነፍሴንም ከታችኛይቱ ሲኦል አድነሃታልና።
14አቤቱ፥ ትዕቢተኞች በእኔ ላይ ተነሥተዋል፥
የክፉዎችም ማኅበር ነፍሴን ፈለጉአት፥
ላንተም ምንም ቦታ የላቸውም።
15 #
መዝ. 103፥8፤ 130፥7፤ 145፥8፤ ዘፀ. 34፥6። አቤቱ፥ አንተ ግን መሓሪና ርኅሩኅ አምላክ ነህ፥
ለቁጣ የዘገየህ፥ ጽኑ ፍቅርህና እውነትህ የበዛ፥
16 #
መዝ. 25፥16፤ 116፥16፤ ጥበ. 9፥5። ወደ እኔ ተመልከት፥ ራራልኝ፥
ኃይልህን ለአገልጋይህ፥ ማዳንህንም ለአግልጋይቱ ልጅ ለእኔ ስጥ።
17ለመልካም የሚሆን ምልክትን ከእኔ ጋር አድርግ፥
የሚጠሉኝ ይዩ ይፈሩም፥
አቤቱ፥ አንተ ረድተኸኛልና፥ አጽናንተኸኛልምና።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 86: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ