መዝሙረ ዳዊት 73:13-15

መዝሙረ ዳዊት 73:13-15 መቅካእኤ

እንዲህም አልሁ፦ በውኑ ልቤን በከንቱ አጸደቅሁ፥ እጆቼንም በንጽሕና በከንቱ አጠብሁ። ሁልጊዜም የተገረፍሁ ሆንሁ፥ መሰደቤም በማለዳ ነው። “እንደዚህ እናገራለሁ” ብል ኖሮ፥ እነሆ፥ የልጆችህን ትውልድ በበደልሁ ነበር።