የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 41

41
1ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር።
2 # ጦቢ. 4፥7-11። ለችግረኛና ለምስኪን የሚያስብ ምስጉን ነው፥
ጌታ በክፉ ቀን ያድነዋል።
3ጌታ ይጠብቀዋል፥ ሕያውም ያደርገዋል፥
በምድር ላይም ብፁዕ ያደርጋቸዋል፥
ለጠላቶቹም አሳልፈህ አትሰጠውም።
4ጌታ በደዌው አልጋ ሳለ ይረዳዋል፥
መኝታውን ሁሉ በበሽታው ጊዜ ያነጥፍለታል።
5እኔስ፦ “አቤቱ፥ ማረኝ፥
አንተን በድያለሁና ነፍሴን ፈውሳት” አልሁ።
6ጠላቶቼም በላዬ ክፋትን ይናገራሉ፦
መቼ ይሞታል ስሙስ መቼ ይሻራል? ይላሉ።
7 # መዝ. 31፥12፤ 38፥12-13፤ 88፥8፤ ኢዮብ 19፥13-19፤ ኤር. 20፥10። እኔን ለመጠየቅ የሚገባ ከንቱን ይናገራል፥
ልቡ ኃጢአትን ሰበሰበለት፥
ወደ ውጭ ይወጣል ይናገራልም።
8በላዬ በመተባበር ጠላቶቼ ሁሉ ያንሾካሽካሉ፥
በእኔ ላይም ክፋትን ያስባሉ።
9ክፉ ነገር መጣበት፥
ከተኛበት ከእንግዲህ ወዲህ አይነሣም ይላሉ።
10 # መዝ. 55፥14-15፤ ማቴ. 26፥23፤ ማር. 14፥18፤ ሉቃ. 22፥21፤ ዮሐ. 13፥18። ደግሞ የሰላሜ#41፥10 ታላቅ ወዳጄ ሰው፥ የታመንሁበት
እንጀራዬን የበላ በእኔ ላይ ተረከዙን አነሣ።
11አንተ ግን አቤቱ፥ ማረኝ፥
እመልስላቸውም ዘንድ አቁመኝ።
12ጠላቴ እልል አይልብኝምና
በዚህም በእኔ እንደ ተደሰትክ አወቅሁ።
13እኔንም ስለ ቅንነቴ ደገፍከኝ፥
በፊትህም ለዘለዓለም አጸናኸኝ።
14 # መዝ. 106፥48፤ ነህ. 9፥5። ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም
የእስራኤል አምላክ ጌታ ይባረክ።
አሜን አሜን።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ