የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 42

42
1ለመዘምራን አለቃ፥ የቆሬ ልጆች ትምህርት።
2 # መዝ. 63፥2፤ 84፥3፤ 143፥6፤ ኢሳ. 26፥9። ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ፥
አቤቱ፥ እንዲሁ ነፍሴ አንተን ትናፍቃለች።
3 # መዝ. 27፥4። ነፍሴ እግዚአብሔርን፥ ሕያው አምላክን ተጠማች፥
መቼ እደርሳለሁ? የአምላክንስ ፊት መቼ አያለሁ?
4 # መዝ. 79፥10፤ ኢዩ. 2፥17፤ መዝ. 80፥6፤ 102፥10። ዘወትር፦ አምላክህ ወዴት ነው? ሲሉኝ
እንባዬ በቀንና በሌሊት ምግብ ሆነኝ።
5 # መዝ. 122፥5፤ ሰቆ.ኤ. 3፥20። ይህን ሳስብ ነፍሴ በእኔ ውስጥ ፈሰሰች፥
ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ምስጋና መኖሪያ ስፍራ እገባለሁና፥
በዓል የሚያከብሩ ሰዎች የደስታና ምስጋና ቃል አሰሙ።
6ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ ታውኪኛለሽ?
የፊቴን መድኃኒት አምላኬን አመሰግነው ዘንድ
በእግዚአብሔር ታመኚ።
7 # መዝ. 43፥3። አምላኬ ሆይ፥ ነፍሴ በእኔ ውስጥ ታወከች፥
ስለዚህ በዮርዳኖስ ምድር
በአርሞንኤምም በታናሹ ተራራ አስታውስሃለሁ።
8 # መዝ. 18፥5፤ 32፥6፤ 69፥2፤ 88፥8፤ ዮናስ 2፥4። በፏፏቴህ ድምፅ ቀላይ ቀላይን ትጠራታለች፥
ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ በላዬ አለፈ።
9ጌታ በቀን ቸርነቱን ያዝዛል፥
በሌሊትም ዝማሬው በእኔ ዘንድ ይሆናል፥
የእኔ ስእለት ለሕይወቴ አምላክ ነው።
10 # መዝ. 18፥2፤ 31፥3-4። እግዚአብሔርን፦ አንተ መጠጊያዬ ነህ፥
ለምን ረሳኸኝ?
ጠላቶቼ ሲያስጨንቁኝ ለምን አዝኜ እመላለሳለሁ? እለዋለሁ።
11ጠላቶቼ ሁልጊዜ፦ አምላክህ ወዴት ነው? ባሉኝ ጊዜ
አጥንቶቼን እየቀለጣጠሙ ሰደቡኝ።
12ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ ታውኪኛለሽ?
የፊቴን መድኃኒት አምላኬን አመሰግነው ዘንድ
በእግዚአብሔር ታመኚ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ

Free Reading Plans and Devotionals related to መዝሙረ ዳዊት 42

YouVersion የእርስዎን ተሞክሮ ግላዊ ለማድረግ ኩኪዎችን ይጠቀማል። የእኛን ድረ ገጽ በመጠቀም፣ በግለሰብነት መመሪያችን ላይ እንደተገለጸው የእኛን የኩኪዎች አጠቃቀም ተቀብለዋል