መዝሙረ ዳዊት 43
43
1 #
መዝ. 119፥154። አቤቱ፥ ፍረድልኝ፥
ከጽድቅ በራቁም ሕዝብ ዘንድ ተሟገትልኝ፥
ከሸንጋይና ከግፈኛ ሰው አድነኝ።
2አንተ አምላኬ ኃይሌም፥ ለምን ትተወኛለህ?
ጠላቶቼ ሲያስጨንቁኝ ለምን አዝኜ እመላለሳለሁ?
3 #
መዝ. 18፥29፤ 27፥1፤ 36፥10፤ ሚክ. 7፥8። ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፥
እነርሱ ይምሩኝ፥
ወደ ቅድስናህ ተራራና ወደ ማደሪያህ ይውሰዱኝ።
4ወደ እግዚአብሔር መሠዊያ፥
ጉልማስነቴንም ደስ ወዳሰኛት ወደ አምላኬ እገባለሁ፥
አቤቱ አምላኬ፥ በበገና አመሰግንሃለሁ።
5ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ ታውኪኛለሽ?
የፊቴን መድኃኒት አምላኬን አመሰግነው ዘንድ
በእግዚአብሔር ታመኚ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 43: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ