የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 39:9-13

መዝሙረ ዳዊት 39:9-13 መቅካእኤ

ከመተላለፌ ሁሉ አድነኝ፥ የሞኞች መሳለቂያ አታድርገኝ። አንተ ሠርተኸኛልና ዝም አልሁ አፌንም አልከፈትሁም። መቅሠፍትህን ከእኔ አርቅ፥ ከእጅህ ብርታት የተነሣ አልቄአለሁና። በተግሣጽህ ስለ ኃጢአቱ ሰውን ዘለፍኸው፥ የሚመኘውንም እንደ ብል ታጠፋበታለህ፥ በእውነት ሰው ሁሉ ከንቱ ነው። አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማ፥ ጩኸቴንም አድምጥ፥ ልቅሶዬንም ቸል አትበለኝ፥ እኔ በምድር ላይ መጻተኛ ነኝና፥ እንደ አባቶቼም እንግዳ ነኝና።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}