የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 39

39
1 # 1ዜ.መ. 16፥41፤ መዝ. 62፥1፤ 77፥1። ለመዘምራን አለቃ፥ ለኤዶታም፥ የዳዊት መዝሙር።
2በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፥
ክፉ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ ሁሉ
በአፌ ላይ ልጓም አኖራለሁ አልሁ።
3ከዝምታ የተነሣ እንደ ዲዳ ሆንሁ፥
ለበጎ እንኳ ዝም አልሁ፥
ሥቃዬም ተቀሰቀሰብኝ።
4 # ኤር. 20፥9። ልቤም በውስጤ ሞቀብኝ፥
ከማሰቤም የተነሣ እሳት ነደደ፥
በአንደበቴም ተናገርሁ፦
5አቤቱ፥ ፍጻሜዬን አስታውቀኝ፥
የዘመኔ ቁጥሮች ምን ያህል እንደ ሆኑ፥
እኔ ምን ያህል ረጋፊ እንደሆንኩ አውቅ ዘንድ።
6 # መዝ. 62፥10፤ 90፥9-10፤ 144፥4፤ ኢዮብ 7፥6፤ 16፤ 14፥1፤ 5፤ መክ. 6፥12፤ ጥበ. 2፥5። እነሆ፥ ዘመኖቼን ከእጅ መዳፍ አሳጠርካቸው፥
አካሌም በፊትህ እንደ ኢምንት ነው።
ሰው ሁሉ በእውነት ከንቱ ነው።
7በእውነት ሰው እንደ ጥላ ይመላለሳል፥
በእውነት በከንቱ ይታወካል።
ያከማቻል የሚሰበስብለትንም አያውቅም።
8አቤቱ አሁንስ ማንን እጠብቃለሁ?
ተስፋዬ በአንተ ነው።።
9ከመተላለፌ ሁሉ አድነኝ፥
የሞኞች መሳለቂያ አታድርገኝ።
10አንተ ሠርተኸኛልና
ዝም አልሁ አፌንም አልከፈትሁም።
11መቅሠፍትህን ከእኔ አርቅ፥
ከእጅህ ብርታት የተነሣ አልቄአለሁና።
12በተግሣጽህ ስለ ኃጢአቱ ሰውን ዘለፍኸው፥
የሚመኘውንም እንደ ብል ታጠፋበታለህ፥
በእውነት ሰው ሁሉ ከንቱ ነው።
13 # መዝ. 119፥19፤ ዘፍ. 23፥4፤ ዕብ. 11፥13፤ 1ጴጥ. 2፥11። አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማ፥ ጩኸቴንም አድምጥ፥
ልቅሶዬንም ቸል አትበለኝ፥
እኔ በምድር ላይ መጻተኛ ነኝና፥
እንደ አባቶቼም እንግዳ ነኝና።
14ወደማልመለስበት ሳልሄድ ዐርፍ ዘንድ ተወኝ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}