የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 38

38
1ለሰንበት መታሰቢያ፥ የዳዊት መዝሙር።
2 # መዝ. 6፥2። አቤቱ፥ በቁጣህ አትቅሠፈኝ፥
በመዓትህም አትገሥጸኝ።
3 # ኢዮብ 6፥4፤ ሰቆ.ኤ. 3፥12፤ መዝ. 31፥11፤ 64፥7። ፍላጾችህ ወግተውኛልና፥
እጅህንም በላዬ ላይ አክብደህብኛልና።
4 # ኢሳ. 1፥5-6። ከቁጣህ የተነሣ ሥጋዬ ጤና የለውም፥
ከኃጢአቴም የተነሣ አጥንቶቼ ሰላም የላቸውም።
5 # መዝ. 40፥13፤ ዕዝ. 9፥6። ዐመፃዎቼ በራሴ ላይ ከፍ ከፍ ብለዋልና፥
እንደ ከባድ ሸክምም በላዬ ከብደዋልና።
6ከአላዋቂነቴ የተነሣ ቁስሌ ሸተተ በሰበሰም፥
7 # መዝ. 35፥14። እጅግ ጐሰቈልሁ ተዋረድሁም፥
ሁልጊዜም በትካዜ እመላለሳለሁ።
8ወገቤ በትኩሳት ተሞልቷልና፥
ሥጋዬም ጤና የለውምና።
9 # መዝ. 102፥4-6። ዛልኩኝ እጅግም ደቀቅሁ፥
ከልቤ መጠበብ የተነሣ ጮኽሁ።
10አቤቱ፥ ፈቃዴ ሁሉ በፊትህ ነው፥
ጭንቀቴም ከአንተ አይሰወርም።
11 # መዝ. 6፥8፤ 31፥10። ልቤ ደነገጠብኝ፥ ኃይሌም ተወችኝ፥
የዐይኖቼም ብርሃን ፈዘዘ።
12ወዳጆቼም ባልንጀሮቼም ከቁስሌ ገለል ብለው ቆሙ፥
ዘመዶቼም ርቀው ቆሙ።
13ነፍሴንም የሚሹአት በረቱብኝ፥
መከራዬንም የሚፈልጉ ከንቱን ተናገሩ፥
ሁልጊዜም በሽንገላ ይመክራሉ።
14እኔ ግን እንደማይሰማ ደንቆሮ
አፉንም እንደማይከፍት ዲዳ ሆንሁ።
15እንደማይሰማ ሰው
በአፉም ተግሣጽ እንደሌለው ሰው ሆንሁ።
16 # መዝ. 13፥4። አቤቱ፥ በአንተ ታምኛለሁና፥
አቤቱ አምላኬ፥ አንተ ትሰማኛለህ።
17ጠላቶቼ በእኔ ላይ ደስ እንዳይላቸው ብያለሁና፥
እግሮቼም ቢሰናከሉ ራሳቸውን በእኔ ላይ ከፍ ከፍ ያደርጋሉ።
18እኔስ ለመውደቅ ተቃርቤአለሁና፥
ቁስሌም ሁልጊዜ በፊቴ ነውና።
19 # መዝ. 32፥5፤ 51፥5። በደሌን እናገራለሁና፥
ስለ ኃጢአቴም እተክዛለሁ።
20ጠላቶቼ ሕያዋን ናቸው ይበረቱብኝማል፥
በጠማማነትም የሚጠሉኝ በዙ።
21 # መዝ. 109፥5። ጽድቅን ስለ ተከተልሁ፥
በበጎ ፋንታ ክፉን የሚመልሱልኝ ይጠሉኛል።
22 # መዝ. 22፥2፤12፤20፤ 35፥22። አቤቱ፥ አንተ አትጣለኝ፥
አምላኬ፥ ከኔ አትራቅ።
23 # መዝ. 40፥14። አቤቱ መድኃኒቴ፥ እኔን ለመርዳት ፍጠን።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ