የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 148:1-5

መዝሙረ ዳዊት 148:1-5 መቅካእኤ

ሃሌ ሉያ። ጌታን ከሰማያት አመስግኑት፥ በአርያም አመስግኑት። መላእክቱ ሁሉ፥ አመስግኑት፥ ሠራዊቱ ሁሉ፥ አመስግኑት። ፀሐይና ጨረቃ፥ አመስግኑት፥ የምታበሩ ከዋክብት ሁሉ፥ አመስግኑት። ሰማየ ሰማያት፥ አመስግኑት፥ ከሰማያት በላይ ያላችሁም ውኃዎችም እንዲሁ። የጌታን ስም ያመስግኑት፥ እርሱም አዝዞአልና፥ ተፈጠሩ።