መዝሙረ ዳዊት 147
147
1 #
መዝ. 33፥1፤ 92፥2። ጌታን አመስግኑ፥ መዝሙር መልካም ነውና።
ለአምላካችን ምስጋና ያማረ ነው።
2 #
ኢሳ. 11፥12፤ 56፥8፤ ኤር. 31፥10። ጌታ ኢየሩሳሌምን ይሠራል፥
ከእስራኤልም የተበተኑትን ይሰበስባል።
3 #
ኢዮብ 5፥18፤ ኢሳ. 30፥26፤ 61፥1፤ ኤር. 33፥6። ልባቸው የተሰበረባቸውን ይፈውሳል፥
ሕማማቸውንም ይጠግናል።
4 #
ኢሳ. 40፥26። የከዋክብትንም ብዛት ይቈጥራል፥
ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል።
5 #
ዮዲ. 16፥13፤ ኤር. 51፥15። ጌታችን ታላቅ ነው፥ ኃይሉም ታላቅ ነው፥
ለጥበቡም ቍጥር ስፍር የለውም።
6 #
መዝ. 146፥9፤ 1ሳሙ. 2፥7-8። ጌታ የተዋረዱትን ያነሣል፥
ክፉዎችን ግን እስከ ምድር ድረስ ያዋርዳል።
7 #
መዝ. 71፥22። ለጌታ በምስጋና ዘምሩ፥
ለአምላካችንም በመሰንቆ ዘምሩ፥
8 #
መዝ. 104፥13፤ ኢዮብ 5፥10፤ ኤር. 14፥22፤ ኢዩ. 2፥23። ሰማዩን በደመናት ይሸፍናል
ለምድርም ዝናብን ያዘጋጃል፥
ሣርን በተራሮች ላይ ያበቅላል።
9 #
ኢዮብ 38፥41፤ ማቴ. 6፥26። ለእንስሶችም ምግባቸውን ይሰጣል
ለሚጠሩት ለቁራዎች ጫጩቶችም እንዲሁ።
10 #
መዝ. 20፥8፤ 33፥16-18። በፈረስ ኃይል አይደሰትም፥
በሰውም ጡንቻ ሐሴት አያደርግም።
11ጌታ በሚፈሩት፥
በጽኑ ፍቅሩ በሚታመኑት ይደሰታል።
12ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ጌታን አመስግኚ፥
ጽዮንም ሆይ፥ ለአምላክሽ እልል በዪ
13 #
መዝ. 48፥14። የደጆችሽን መወርወሪያ አጽንቶአልና፥
ልጆችንም በውስጥሽ ባርኮአልና።
14በወሰንሽም ሰላምን አደረገ፥
የስንዴንም ስብ አጠገበሽ።
15መልእክቱን ወደ ምድር ይልካል፥
ቃሉም እጅግ ፈጥኖ ይሮጣል።
16አመዳዩን እንደ ባዘቶ ይሰጣል፥
ጉሙን እንደ አመድ ይበትነዋል፥
17በረዶውን እንደ ፍርፋሪ ያወርዳል፥
በቁሩ ፊት ማን ይቆማል?
18ቃሉን ልኮ ያቀልጠዋል፥
ነፋሱን ያነፍሳል፥ ውኆችንም ያፈስሳል።
19ቃሉን ለያዕቆብ፥
ሥርዓቱንና ፍርዱን ለእስራኤል ይናገራል።
20ለሌሎች አሕዛብ ሁሉ እንዲህ አላደረገም፥
ፍርዱንም አልገለጠላቸውም።
ሃሌ ሉያ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 147: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ