የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 145

145
1የዳዊት የምስጋና መዝሙር።
አምላኬ ንጉሤ ሆይ፥ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፥
ስምህንም ለዘለዓለም ዓለምም እባርካለሁ።
2 # መዝ. 34፥2። በየቀኑ ሁሉ እባርክሃለሁ፥
ስምህንም ለዘለዓለም ዓለምም አመሰግናለሁ።
3 # መዝ. 48፥2፤ 95፥3፤ 96፥4፤ ኢዮብ 36፥26። ጌታ ታላቅ ነው እጅግም የተመሰገነ ነው፥
ታላቅነቱም የማይመረመር ነው።
4 # መዝ. 22፥31-32፤ 48፥14-15፤ 71፥18፤ 78፥4፤ ዘፀ. 10፥2፤ ዘዳ. 4፥9። ትውልደ ትውልድ ሥራህን ያመሰግናሉ፥
ኃይልህንም ያወራሉ።
5 # መዝ. 96፥3፤ 105፥2። የቅድስናህን ግርማ ክብር ይናገራሉ፥
ተኣምራትህንም ይነጋገራሉ።
6 # መዝ. 66፥3። የግርማህንም ኃይል ይናገራሉ፥
ታላቅነትህንም ይነጋገራሉ፥
ብርታትህንም ይነጋገራሉ።
7የቸርነትህን ብዛት መታሰብ ያወጣሉ፥
በጽድቅህም ሐሤትን ያደርጋሉ።
8 # መዝ. 86፥5፤ 15፤ 103፥8፤ ዘፀ. 34፥6፤ ሲራ. 2፥11። ጌታ ርኅሩኅና መሓሪ ነው፥
ከቁጣ የራቀ፥ ጽኑ ፍቅሩም ብዙ ነው፥
9 # መዝ. 103፥13፤ ጥበ. 11፥24። ጌታ ለሁሉም ቸር ነው።
ምሕረቱም በሥራው ሁሉ ላይ ነው።
10 # ዳን. 3፥57። አቤቱ፥ ሥራህ ሁሉ ያመሰግኑሃል፥
ቅዱሳንህም ይባርኩሃል።
11የመንግሥትህን ክብር ይናገራሉ፥
ኃይልህንም ይነጋገራሉ፥
12ለሰው ልጆች ኃይልህን
የመንግሥትህንም ግርማ ክብር ያስታውቁ ዘንድ
13 # መዝ. 10፥16፤ 102፥13፤ 146፥10፤ ሰቆ.ኤ. 5፥19፤ ዳን. 3፥33፤ ራእ. 11፥15። መንግሥትህ የዘለዓለም መንግሥት ናት፥
ግዛትህም ለልጅ ልጅ ነው።
14 # መዝ. 94፥18፤ 146፥8። ጌታ በቃሎቹ የታመነ ነው፥
በሥራውም ሁሉ ጻድቅ ነው፥
ጌታ የሚወድቁትን ሁሉ ይደግፋቸዋል፥
ያጎነበሱትንም ያነሣቸዋል።
15 # መዝ. 136፥25፤ 104፥27-28፤ ማቴ. 6፥25-26። የሁሉ ዐይን አንተን ተስፋ ያደርጋል፥
አንተም ምግባቸውን በየጊዜው ትሰጣቸዋለህ።
16አንተ እጅህን ትከፍታለህ፥
ሕይወት ላለውም ሁሉ መልካምን ታጠግባለህ።
17 # ዘዳ. 32፥4። ጌታ በመንገዱ ሁሉ ጻድቅ ነው
በሥራውም ሁሉ ቸር ነው።
18 # ዘዳ. 4፥7፤ ኢሳ. 55፥6፤ 58፥9። ጌታ ለሚጠሩት ሁሉ፥
በእውነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው።
19 # መዝ. 34፥18። ለሚፈሩት ምኞታቸውን ያሳካል፥
ጩኸታቸውንም ይሰማል ያድናቸዋልም።
20 # መሳ. 5፥31። ጌታ የሚወድዱትን ሁሉ ይጠብቃል፥
ክፉዎችንም ሁሉ ያጠፋል።
21አፌ የጌታን ምስጋና ይናገራል፥
ሥጋም ሁሉ ለዘለዓለም ዓለም የተቀደሰውን ስሙን ይባርክ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ