መዝሙረ ዳዊት 145
145
1የዳዊት የምስጋና መዝሙር።
አምላኬ ንጉሤ ሆይ፥ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፥
ስምህንም ለዘለዓለም ዓለምም እባርካለሁ።
2 #
መዝ. 34፥2። በየቀኑ ሁሉ እባርክሃለሁ፥
ስምህንም ለዘለዓለም ዓለምም አመሰግናለሁ።
3 #
መዝ. 48፥2፤ 95፥3፤ 96፥4፤ ኢዮብ 36፥26። ጌታ ታላቅ ነው እጅግም የተመሰገነ ነው፥
ታላቅነቱም የማይመረመር ነው።
4 #
መዝ. 22፥31-32፤ 48፥14-15፤ 71፥18፤ 78፥4፤ ዘፀ. 10፥2፤ ዘዳ. 4፥9። ትውልደ ትውልድ ሥራህን ያመሰግናሉ፥
ኃይልህንም ያወራሉ።
5 #
መዝ. 96፥3፤ 105፥2። የቅድስናህን ግርማ ክብር ይናገራሉ፥
ተኣምራትህንም ይነጋገራሉ።
6 #
መዝ. 66፥3። የግርማህንም ኃይል ይናገራሉ፥
ታላቅነትህንም ይነጋገራሉ፥
ብርታትህንም ይነጋገራሉ።
7የቸርነትህን ብዛት መታሰብ ያወጣሉ፥
በጽድቅህም ሐሤትን ያደርጋሉ።
8 #
መዝ. 86፥5፤ 15፤ 103፥8፤ ዘፀ. 34፥6፤ ሲራ. 2፥11። ጌታ ርኅሩኅና መሓሪ ነው፥
ከቁጣ የራቀ፥ ጽኑ ፍቅሩም ብዙ ነው፥
9 #
መዝ. 103፥13፤ ጥበ. 11፥24። ጌታ ለሁሉም ቸር ነው።
ምሕረቱም በሥራው ሁሉ ላይ ነው።
10 #
ዳን. 3፥57። አቤቱ፥ ሥራህ ሁሉ ያመሰግኑሃል፥
ቅዱሳንህም ይባርኩሃል።
11የመንግሥትህን ክብር ይናገራሉ፥
ኃይልህንም ይነጋገራሉ፥
12ለሰው ልጆች ኃይልህን
የመንግሥትህንም ግርማ ክብር ያስታውቁ ዘንድ
13 #
መዝ. 10፥16፤ 102፥13፤ 146፥10፤ ሰቆ.ኤ. 5፥19፤ ዳን. 3፥33፤ ራእ. 11፥15። መንግሥትህ የዘለዓለም መንግሥት ናት፥
ግዛትህም ለልጅ ልጅ ነው።
14 #
መዝ. 94፥18፤ 146፥8። ጌታ በቃሎቹ የታመነ ነው፥
በሥራውም ሁሉ ጻድቅ ነው፥
ጌታ የሚወድቁትን ሁሉ ይደግፋቸዋል፥
ያጎነበሱትንም ያነሣቸዋል።
15 #
መዝ. 136፥25፤ 104፥27-28፤ ማቴ. 6፥25-26። የሁሉ ዐይን አንተን ተስፋ ያደርጋል፥
አንተም ምግባቸውን በየጊዜው ትሰጣቸዋለህ።
16አንተ እጅህን ትከፍታለህ፥
ሕይወት ላለውም ሁሉ መልካምን ታጠግባለህ።
17 #
ዘዳ. 32፥4። ጌታ በመንገዱ ሁሉ ጻድቅ ነው
በሥራውም ሁሉ ቸር ነው።
18 #
ዘዳ. 4፥7፤ ኢሳ. 55፥6፤ 58፥9። ጌታ ለሚጠሩት ሁሉ፥
በእውነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው።
19 #
መዝ. 34፥18። ለሚፈሩት ምኞታቸውን ያሳካል፥
ጩኸታቸውንም ይሰማል ያድናቸዋልም።
20 #
መሳ. 5፥31። ጌታ የሚወድዱትን ሁሉ ይጠብቃል፥
ክፉዎችንም ሁሉ ያጠፋል።
21አፌ የጌታን ምስጋና ይናገራል፥
ሥጋም ሁሉ ለዘለዓለም ዓለም የተቀደሰውን ስሙን ይባርክ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 145: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ