መዝሙረ ዳዊት 143
143
1ልጁ ባሳደደው ጊዜ፥ የዳዊት መዝሙር።
አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማ፥
ልመናዬን አድምጥ፥
በታማኝነትህ፥ በጽድቅህም መልስልኝ።
2 #
መክ. 7፥20፤ ኢዮብ 4፥17፤ ሮሜ 3፥20። ሕያው ሁሉ በፊትህ ጻድቅ አይደለምና
ከባርያህ#143፥2 ከእኔ ጋር። ጋር ወደ ፍርድ አትግባ።
3 #
መዝ. 7፥6፤ ሰቆ.ኤ. 3፥6። ጠላት ነፍሴን አሳድዶአታል፥
ሕይወቴንም በምድር ላይ አጐስቁሎአታል፥
ቀድሞ እንደ ሞተ ሰው በጨለማ አኑሮኛል።
4 #
መዝ. 142፥4፤ ኢዮብ 17፥1። ነፍሴ በውስጤ አለቀችብኝ፥
ልቤም በውስጤ ደነገጠብኝ።
5 #
መዝ. 77፥6፤12። የቀድሞውን ዘመን አሰብሁ፥
ሥራህንም ሁሉ አሰላሰልሁ፥
የእጅህንም ሥራ አስተዋልሁ።
6 #
መዝ. 42፥2፤ 63፥2። እጆቼን ወደ አንተ ዘረጋሁ፥
ነፍሴም እንደ ምድረ በዳ አንተን ተጠማች።
7 #
መዝ. 28፥1፤ 30፥4፤ 88፥5፤ ምሳ. 1፥12። አቤቱ፥ ፈጥነህ ስማኝ፥ መንፈሴ ዛለ፥
ፊትህን ከኔ አትሰውር፥
ወደ ጉድጓድም እንደሚወርዱ እንዳልሆን።
8 #
መዝ. 25፥4፤ 27፥11፤ 86፥11፤ 119፥12፤35። አንተን ታምኛለሁና
በማለዳ ጽኑ ፍቅርህን አሰማኝ፥
አቤቱ፥ ነፍሴን ወደ አንተ አንሥቻለሁና
የምሄድበትን መንገድ አሳውቀኝ።
9አቤቱ፥ ወደ አንተ ተማፅኛለሁና
ከጠላቶቼ አድነኝ።
10አንተ አምላኬ ነህና ፈቃድህን ለማድረግ አስተምረኝ፥
ቅዱስ መንፈስህም በጽድቅ ምድር ይምራኝ።
11አቤቱ፥ ስለ ስምህ ሕያው አድርገኝ፥
በጽድቅህም ነፍሴን ከመከራዋ አውጣት።
12 #
መዝ. 116፥16። በጽኑ ፍቅርህ ጠላቶቼን ደምስሳቸው፥
እኔ ባርያህ ነኝና
ነፍሴን የሚያስጨንቁአትን ሁሉ አጥፋቸው።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 143: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ