መዝሙረ ዳዊት 137
137
1 #
ሕዝ. 3፥15፤ ሰቆ.ኤ. 3፥48። በባቢሎን ወንዞች አጠገብ በዚያ ተቀመጥን፥
ጽዮንንም ባሰብናት ጊዜ አለቀስን።
2 #
ኢሳ. 24፥8፤ ሰቆ.ኤ. 5፥14። በአኻያ ዛፎች ላይ መሰንቆቻችንን ሰቀልን።
3የማረኩን በዚያ የዝማሬን ቃል ፈለጉብን፥
የወሰዱንም፦ የጽዮንን ዝማሬ ዘምሩልን አሉን።
4የጌታን ዝማሬ በባዕድ ምድር እንዴት እንዘምራለን?
5 #
ኤር. 51፥50። ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ብረሳሽ፥ ቀኜ ትርሳኝ#137፥5 ትስለል።።
6ባላስታውስሽ፥ ምላሴ በጉሮሮዬ ይጣበቅ፥
ከደስታዬ ሁሉ በላይ ኢየሩሳሌምን ባልወድድ።
7 #
ኤር. 49፥7፤ ሰቆ.ኤ. 4፥21-22፤ ሕዝ. 25፥12-14። አቤቱ፥ በኢየሩሳሌም ቀን የኤዶምን ልጆች አስብ፦
እስከ መሠረትዋ ድረስ አፍርሱ አፍርሱ ያሉአትን።
8 #
ኢሳ. 47፥1-3፤ ኤር. 50—51። አንቺ ፈራሽ የባቢሎን ልጅ ሆይ፥
ስለ ተበቀልሽን የሚበቀልሽ የተመሰገነ ነው።
9 #
ሆሴዕ 14፥1። ሕፃኖችሽን ይዞ በዓለት ላይ የሚፈጠፍጣቸው የተመሰገነ ነው።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 137: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ