መዝሙረ ዳዊት 136
136
1 #
መዝ. 100፥5፤ 118፥1። ጌታን አመስግኑ፥ ቸር ነውና፥
ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና።
2የአማልክትን አምላክ አመስግኑ፥
ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና።
3የጌቶችን ጌታ አመስግኑ፥
ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥
4 #
መዝ. 72፥18። ብቻውን ታላቅ ተኣምራትን ያደረገውን፥
ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥
5 #
ዘፍ. 1፥9-19። ሰማያትን በጥበቡ የሠራውን፥
ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥
6 #
መዝ. 24፥2። ምድርን በውኃ ላይ ያጸናውን፥
ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥
7ብቻውን ታላላቅ ብርሃናትን የሠራውን፥
ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥
8ፀሐይን በቀን ላይ እንድትሠለጥን፥
ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥
9 #
ኤር. 31፥35። ጨረቃንና ከዋክብትን በሌሊት እንዲሠለጥኑ ያደረገ፥
ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥
10 #
ዘፀ. 12፥29፤51፤ 14፥22፤ 27፤ 15፥22፤ መዝ. 78፥51-52፤ 135፥8። ከበኩራቸው ጋር ግብጽን የመታውን፥
ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥
11እስራኤልንም ከመካከላቸው ያወጣውን፥
ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥
12 #
ዘዳ. 4፥34። በጸናች እጅ በተዘረጋችም ክንድ፥
ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥
13የኤርትራን ባሕር በየክፍሉ የከፈለውን፥
ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥
14እስራኤልን በመካከሉ ያሳለፈውን፥
ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥
15 #
ዘፀ. 14፥21። ፈርዖንንና ሠራዊቱን በኤርትራ ባሕር የጣለውን፥
ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥
16 #
ዘዳ. 8፥2፤15። ሕዝቡን በምድረ በዳ የመራውን፥
ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥
17 #
መዝ. 135፥10-12። ታላላቅ ነገሥታትን የመታውን፥
ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥
18ብርቱዎችንም ነገሥታት የገደለውን፥
ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥
19የአሞራውያንን ንጉሥ ሴዎንን፥
ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥
20የባሳንን ንጉሥ ዐግን፥
ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥
21ምድራቸውን ርስት አድርጎ የሰጠውን፥
ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥
22ለባርያው ለእስራኤል ርስት፥
ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና።
23እኛን በመዋረዳችን አስቦናልና፥
ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥
24ከጠላቶቻችንም እጅ አድኖናልና፥
ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥
25ለሥጋ ሁሉ ምግብን የሚሰጥ፥
ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና።
26የሰማይን አምላክ አመስግኑ፥
ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 136: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ