መዝሙረ ዳዊት 135
135
1 #
መዝ. 113፥1። ሃሌ ሉያ!
የጌታን ስም አመስግኑ፥
እናንተ የጌታ ባርያዎች ሆይ፥ አመስግኑት፥
2 #
መዝ. 134፥1። በጌታ ቤት ውስጥ፥
በአምላካችን ቤት አደባባይ የምትቆሙ።
3ጌታ ቸር ነውና ጌታን አመስግኑ፥
ለስሙ ዘምሩ፥ መልካም ነውና፥
4 #
መዝ. 33፥12፤ 144፥15፤ ዘፀ. 19፥6፤ ዘዳ. 7፥6። ጌታ ያዕቆብን ለራሱ፥
እስራኤልንም ግዛቱ አድርጎ መርጦታልና፥
5 #
መዝ. 95፥3፤ ዘፀ. 18፥11። ጌታ ታላቅ እንደሆነ፥
ጌታችንም ከአማልክት ሁሉ እንደሚበልጥ አውቄአለሁና።
6 #
መዝ. 115፥3። በሰማይና በምድር በባሕርና በጥልቆች ሁሉ፥
ጌታ የወደደውን ሁሉ አደረገ።
7 #
መዝ. 148፥8፤ ኤር. 10፥13፤ 51፥16፤ ኢዮብ 37፥9። ከምድር ዳርቻ ደመናትን ያወጣል፥
በዝናብ ጊዜ መብረቅን ያደርጋል፥
ነፋሳትንም ከመዛግብቱ ያወጣል።
8 #
መዝ. 78፥51፤ 105፥27፤ 36፤ 136፥10፤ ዘፀ. 12፥29። የግብጽን በኩር ልጆች
ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ መታ።
9ግብጽ ሆይ፥ በመካከልሽ በፈርዖንና በባርያዎቹ ሁሉ ላይ
ተኣምራትንና ድንቅን ሰደደ።
10 #
መዝ. 136፥17-22፤ ዘኍ. 21፥21-35፤ ዘዳ. 2፥24—3፥17። ብዙ አሕዛብን መታ፥ ብርቱዎችንም ነገሥታት ገደለ።
11የአሞራውያንን ንጉሥ ሴዎንን፥ የባሳንንም ንጉሥ ዐግን፥
የከነዓንን መንግሥታት ሁሉ ገደለ፥
12ምድራቸውንም ርስት አድርጎ
ለእስራኤል ለሕዝቡ ርስት ሰጠ።
13 #
መዝ. 102፥13፤ ዘፀ. 3፥15። አቤቱ፥ ስምህ ለዘለዓለም ነው፥
ዝክርህም ለልጅ ልጅ ነው፥
14ጌታ ለሕዝቡ ይፈርዳልና፥
ባርያዎቹንም ይረዳልና።
15 #
መዝ. 115፥4-8፤ ራእ. 9፥20። የአሕዛብ ጣዖታት የብርና የወርቅ፥
የሰው እጅ ሥራ ናቸው።
16አፍ አላቸው፥ አይናገሩምም፥
ዐይን አላቸው፥ አያዩምም፥
17ጆሮ አላቸው፥ አይሰሙምም፥
እስትንፋስም በአፋቸው የለም።
18የሚሠሩአቸው ሁሉ
የሚታመኑባቸውም ሁሉ እንደ እነርሱ ይሁኑ።
19የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ጌታን ባርኩት፥
የአሮን ቤት ሆይ፥ ጌታን ባርኩት፥
20የሌዊ ቤት ሆይ፥ ጌታን ባርኩት፥
ጌታን የምትፈሩት ሆይ፥ ጌታን ባርኩት።
21በኢየሩሳሌም የሚያድር ጌታ ከጽዮን ይባረክ፥
ሃሌ ሉያ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 135: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ